ከኢትዮጵያዊቷ ሞዴል ገሊላ በቀለ ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት የነበረውና የአንድ ልጅ አባት የሆነው ታዋቂው የሆሊውድ ፊልም አዘጋጅ ታይለር ፔሪ፣ ለሁለተኛ ጊዜ በጾታዊ ጥቃት የፍትሐ ብሔር ክስ እንደቀረበበት ‘ዘ ራፕ’ (TheWrap) ዘግቧል።
ክሱ የቀረበው እ.ኤ.አ Dec 26 ቀን 2025 ሲሆን ከሳሹ በ2016 “Boo! A Madea Halloween” በተሰኘው የፔሪ ፊልም ላይ የተሳተፈው ተዋናይ እና ሞዴል ማሪዮ ሮድሪጌዝ ነው።
ሮድሪጌዝ “ታይለር ፔሪ በተደጋጋሚ ያልተገቡ የጾታ ጥያቄዎችን አቅርቦብኛል እንዲሁም የሥራ አካባቢውን አስቸጋሪ አድርጎታል” በሚል ቢያንስ 77 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ እየጠየቀ ይገኛል።
የክስ ማመልከቻው እንደሚለው ፔሪ በሆሊውድ ያለውን ተፅዕኖ ተጠቅሞ በሮድሪጌዝ ላይ ጫና አሳድሯል፤ እንዲሁም ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ ገንዘብ እንደሰጠው ተገልጿል።
ክሱ የፊልሙ አከፋፋይ የሆነው ‘ላዮንስጌት’ (Lionsgate) ተገቢውን ክትትል ባለማድረጉ በተባባሪነት ከሷል።
ይህ በ2025 (እ.ኤ.አ) ውስጥ በታይለር ፔሪ ላይ የቀረበ ሁለተኛው ትልቅ ክስ ነው።
ቀደም ሲል በሰባተኛው ወር ተዋናይ ዴሬክ ዲክሰን “The Oval” በተሰኘው የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ሲሰራ የጾታ ትንኮሳ እንደደረሰበት በመግለጽ ክስ መስርቶ ነበር።
የፔሪ የሕግ አማካሪዎች ግን ክሱ መሰረተ ቢስ እና ለገንዘብ ተብሎ የቀረበ ነው በማለት የቀረቡትን ክሶች በሙሉ አስተባብለዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






