ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

Date:

የአገር አለኝታ ሠራዊታችን በሰለጠነ የሰው ኃይልና ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች መታጠቁ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኃይል ሚዛን ልዩነት ንጽጽር የሚባለውን ስሌት በፍጹም እንዳይታሰብ አድርጎታል። ። በመሆኑም፣ በራሱ በኢትዮጵያ ዜጎች አንደበት ሠራዊቱን ማንቋሸሽ፣ ማጥላላትና ማዋረድ የዚህ ስብሰባ አንደኛውና ዋነኛው ተልዕኮ ተደረገ። “የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳሰበን” እያሉ የአዞ እንባ እያነቡ፣  የሀገሩ ዘብ የሆነውን ሠራዊት በዚህ መልኩ ማጥላላት፣ የጠላት ፍላጎት አስፈጻሚነትን እንጂ ሀገራዊ ተቆርቋሪነትን ሊያሳይ አይችልም።
(የግል ትዝብት)

ሳልወድ በጓደኛዬ ጉትጓታ የአመጽ አደራጅ ግብረ ኃይሉ የጠራውን የበይነ-መረብ ሕዝባዊ ስብሰባ ተከታተልኩ። እወነት ለመናገር የጠበቅኩትን ነበር የሆነው። በአጭር ቋንቋ የከሸፈ ነበር። ወይም በእነሱ ቋንቋ “ትዕይንተ ውድቀት” ብዬ ሰይሜዋለሁ።

በመድረኩ ላይ የታዩት አጋፋሪዎቹ ንግግር አቅራቢዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ባለፉት ሰባ አመታት ሲንከባለሉ የኖሩ፣ በየጊዜው የተሸነፉ “የያ ትውልድ” እርዝራዥ ቅሪቶች መሆናቸውን ለተመለከተ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ብዙም ማስላት አይጠበቅበትም።  

እነዚህ ግለሰቦች ያንኑ የለመዱትን የጭቆና ፖለቲካ ትርክት፣ እርስ በርሱ በሚጋጭና ግራ በሚያጋባ አቀራረብ ለታዳሚው ለመጋት ሲሞክሩ እያመመኝ ተከታትያለሁ። በንግግራቸው ሁሉ “እነዚህ ሰዎች አገሪቱ የተሰራችበት ኪሚስትሪ ዛሬ ድረስ ያልገባቸው፣ የማይረጥቡ አሳዎች” እያልኩ እገረመ ነበር።

ይህ ስብሰባ እንኳን በሥልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ ሊያንቀጠቅጥ ቀርቶ፣ ለታዳሚው ትኩረት የሚስብ አንድም ጠንካራ ነጥብ ያልነበረው፣ የተንዛዛና እጅግ አሰልቺ ነበር። ከመካከላቸው ለአቅመ-መንግሥት ምስረታ የሚሆኑ ብቁ ሰዎችን ለማግኘት ማንነታቸውን ለማጣራት ብሞክርም፣ በሕዝብ አስተዳደርና በመንግሥት አመራር ረገድ ገቢራዊ ልምድ ያለው አንድም ሰው ማየት አልቻልኩም። ይልቁንም ያየሁት በጨበጣ በትረ-ሥልጣን የሚሹ ግለሰቦችን፣ የሥራ ዘመናቸውን የጨረሱ ጡረተኞችንና እንደ ፔፕሲ ማስታወቂያ “ተጨማሪ ይጠይቁ” አይነቶች ነበሩ። እነዚህ ከሀገር እንደወጡ የከዱ የቀድሞ አምባሳደሮችን ያካተተው ስብስብ የተረጋጋ መንግስት ቢኖር ህግ ፊት ቀርበው በአገር ክህደት፣ በባንዳነት፣ በለኤብነት፣ እንዲሁም ወዘተ የሚጠየቁ ነበሩ።

የዚህ ጥርቅም ዋና የጥቃት ዒላማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ነበሩ። አጀንዳው ከየት እንደተሰፈረ አስቀድሜ መረጃ ስለነበረኝ ይህን ስሰማ የሃገራችንን የግዛት፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማክበርና ለመጠበቅ የሚችል ጠንካራ ኃይል መገንባቱ ገባኝ።

ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ መጠንከሯ ስጋት የሆነበት ሻዕቢያ ያደራጀው ይህ ስብስብ የላኪውን ሻዕቢያን ተልዕኮ ለመፈጸም የቆመ መሆኑ ግልጥ አለለኝ። የሻዕቢያ ዋነኛ የሥጋት ማዕከል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሆናቸው እነዚሁ ሁለት የአገሪቱ ምሰሶዎች ላይ ያነጣጠረው በምክንያት ነበር።

የአገር አለኝታ ሠራዊታችን በሰለጠነ የሰው ኃይልና ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች መታጠቁ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኃይል ሚዛን ልዩነት ንጽጽር የሚባለውን ስሌት በፍጹም እንዳይታሰብ አድርጎታል። ። በመሆኑም፣ በራሱ በኢትዮጵያ ዜጎች አንደበት ሠራዊቱን ማንቋሸሽ፣ ማጥላላትና ማዋረድ የዚህ ስብሰባ አንደኛውና ዋነኛው ተልዕኮ ተደረገ። “የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳሰበን” እያሉ የአዞ እንባ እያነቡ፣  የሀገሩ ዘብ የሆነውን ሠራዊት በዚህ መልኩ ማጥላላት፣ የጠላት ፍላጎት አስፈጻሚነትን እንጂ ሀገራዊ ተቆርቋሪነትን ሊያሳይ አይችልም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያን በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ እንዲገነባ ያደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለተቃዋሚዎቹ ትልቅ ስጋት መሆኑም አልቀረም። እስከ ግንባር ድረስ ወርደው ሠራዊቱን የማዋጋትና የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ቁርጠኝነት እንዳላቸው በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በተግባር ታይቷል። ለሀገራቸው ሲሉ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ያላቸውን ዝግጁነት ጠላቶቻቸው በሚገባ ስለተረዱ፣ ይህ ስብሰባ እርሳቸውን ዋና የጥቃት አጀንዳ አድርጎ መነሳቱ የሚጠበቅ ነበር። አገሪቱን ለመበተን ተልዕኮ የተቀበሉት ያረጡ ፖለቲከኞች በብሄራዊ ስጋት ለውሰው ሊሰብኩን ያሰቡት ይህን ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳካት ነው።

ሌላው የታዘብኩት ነጥብ የቀጣዩ ሥራቸው አካል የሆነው የአደባባይ ሰልፍ ዝግጅት ነው። ይህን ኃላፊነት የወሰዱት በዲሲ አካባቢ የሚገኙት እነ ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን ሲሆኑ፣ ጊዜያቸውን በእግረ-መንገድ ለቅስቀሳ ሲጠቀሙበት ታይተዋል። የዲሲ ግብረ-ኃይል ዛሬም በአሮጌው አመለካከታቸው እንደቀጠሉ ናቸው። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ስደተኛ እንደ ድሮው ለሰነድ ማስረጃ (process) ይጠቅመኛል ብሎ በየሰልፉ የሚወጣበት ጊዜ ማለቁንና የሚያስከትለውን መዘዝ በሚገባ የሚያውቁት ይመስለኛል።

በተለይም ፋኖ በአሜሪካ ዜግነትና በስደተኛ አስተዳደር ሕግ መሠረት በ”ምድብ ሦስት” (Tier 3) የአሸባሪነት ጎራ ሊፈረጅ እንደሚችልና ይህም የሚያስከትለውን ከባድ መዘዝ ሁሉም ጠንቅቆ ያውቀዋል። እንዲህ ባለ ሁኔታ ሕዝብን ለአመጽና ለሰልፍ መቀስቀስ፣ ዜጎችን ካልታሰበ የሕግ አደጋ ውስጥ ከመጣል ውጭ ፋይዳ የለውም። ሰልፉን የሚጠሩት አካላትም ይህንኑ ስጋት እያወቁ ዜጎችን ለራሳቸው የፖለቲካ ትርፍ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከራቸው ሌላው የታዘብኩት ግብዝነት ነው። አንድ ነገር ቢከሰት እነሱ ሩዋንዳ፣ ላኪዎቻቸው ግብጽና ኤርትራ ይሸሻሉ ሊሎቹ ምስኪኖች ይማገዳሉ።

በአጠለቃ ይህ “የበይነ-መረብ ትዕይንተ-ሕዝብ” እንደተፎከረበት ሳይሆን፣ ትዕይንተ ውድቀት ነበር። ስሙን የማይመጥን፣ መግባባት የሌለበትና ጊዜዬን በከንቱ ያባከንኩበት አሰልቺ ኩነት ሆኖ ነው ያገኘሁት። በሀገሪቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ከማምጣት ይልቅ፣ በቆየ ጥላቻና በተልዕኮ ላይ የተመሰረተ መሆኑ የክሸፈቱን ጥልቀት ያሳያል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተበተነ

አዲስ ሪፓርተር— በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት...

ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ እንቅፋት ገጠመው፤ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያ አማራጭ ሆነ፤

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን...

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ የብሉይ ምሁር አመራር ሽግግር ሚስጢር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...

ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ...