የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ

Date:

በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው ‘ምድር አንቀጥቅጥ’ ሰላማዊ ሰልፍ በስጋት እንዲቀር አሳብ ቀረበ

አዲስ ሪፖርተር ባለፈው ቅዳሜ ሚሊዮኖች እንደሚሳተፉበትና “አየር አንቀጥቅጥ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በተካሄደው የኢንተርኔት የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅ ከነበሩት መካከል በግምገማ ተባረሩ። በግምገማው ላይ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ የተባሉ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ጀርባቸውን እንደሰጡ ተሰማ። አቶ ነዓምን “ስማቸውን አትጥሩ፤ ያቀረቡትንም ምክንያት አትናገሩ” በማለት አቶ ልደቱን እንዳቋረጧቸው የስብሰባው ተሳታዊዎች ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል።

በቀጥጥታ ስርጭት “አገዛዝ ያብቃ። ጦርነት ይቁም” የሚሉ መፈልሮችን ከፍ በማድረግ የተካሄደውን የኢንተርኔት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ግምገማ ተካሂዶ ነበር። የ”ኦሮሙማ” አገዛዝ መነቀል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጦ የጀመረው እንቅስቃሴ አሁን ላይ መልኩን ቀይሮ በኢትዮጵያ ብልጽግና የማይሳተፍበት የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ለማድረግ የተዘጋጀው ይህ የኢንተርኔት ላይ የንግግር ሰልፍ፣ እንደተባለው ተሳታፊ አለማግኘቱ በራሳቸው ሚዲያ ሳይቀር ተትችቷል።

ወጣቶች፣ አዲስ ፊት፣ ሙስሊሞችንና ሴቶችን ባለማካተቱና ባረጀ እሳቤ የተያዙ አዛውንቶች የበዙበት ይህ የኢንተርኔት ላይ ስብሰባ በአዘጋጆቹ የአመጽ አመቻች ቲክኒክ ኮሚቴ ሲገመገም አቶ ልደቱ የታሰበውን ያህል ተከታታይ አመገኘቱ ሪፖርት አድርገዋል። አቶ ነዓምን በበኩላቸው |የመጀመሪያ ቀን ትንሽ ነበር። በቀጣይ ቀናት ግን የተሻለ ነበር” በማለት አቶ ልደቱን ለማረም ሞክረዋል።

አቶ ደምስ “ከአዲስ አበባ ስድስት የሚሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን አነጋግሬ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም” ሲሉ አቶ ልደቱ ስማቸውንና ፈቃደኛ ያልሆኑበትን ምክንያት ሊዘረዝሩ ሲሉ፣ አቶ ነዓምን ጣልቃ በመግባት ስማቸውና ምክነያታቸውን መናገር እንደማያስፈልግ በተግሳጽ መልክ የማስተካከያ መመሪያ እንደሰጡ ከስብሰባው ተሳታፊዎች ለመረዳት ተችሏል።

“የሻዕቢያ አጀንዳ ነው” የሚባለውን የሽግግር መንግስት “ልንፈጽመው የሚገባ ትልቁ ፕሮጀክት ነው” የሚሉት አቶ ነዓምን ማስተካከያ እየሰጡ በተካሄደው ግምገማ ተጋብዘው ፈቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች ሽሽት መምረጣቸውን ያስረዱት አቶ ልደቱ የሚዲያዎቹን ስም አላነሱም። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ መረጃ አሰባስቦ እንዳለው የኦሮሚኛና የትግርኛ ቋንቋ ሚዲያዎች ጥሪውን አልተቀበሉም። አማርኛ ፕሮግራም የሚሰሩ የትግሬና የኦሮሞ ተወላጆች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጀርባቸውን ሰጥተዋል። አቶ ልደቱ ” ሚዲያዎቹ ጥሪያችንን አለመቀበላቸው ብቻ ሳይሆን፣ እኛ አየር ላይ እያለን ሌላ ፕሮግራም ሲሰሩ ነበር። አሳዛኙ ጉዳይ እሱ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ኮሚቴው ግምገማውን ካካሄደ በኋላ ቀደም ሲል በቲክኒክ ኮሚቴ ውስጥ የነበሩትን አባሮ አዳዲስ ሰዎችን አስገብቷል። በዚሁ መሰረት አቶ ደምስ፣ ዶክተር ሚኒሊክ፣ ኢንጂነር ዘርዓጽዮን፣ አቶ ገለታው እና አቶ አባይ ሲጭመሩ የጋምቤላ፣ የአፋርና ብቸኛዋ የደቡብ ተወካይ ሴት ከተባረሩት መካከል ናቸው። ዶክተር ሚኒሊክ አማራን ወክለው በተገኙበት የመጀመሪያና ሁለተኛ ስብሰባ “ስብስቡ በመርህ የሚመራ አይደለም። ሸፍጥ ያነገበ ይመስላል” በማለታቸው በአቶ ነዓምን መመሪያ ተባረው እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም። የጃልመሮ አማካሪና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃል አቀባይ አቶ ጂሬኛ በተመሳሳይ ዶከተር ሚኒሊክን የደገፉ ቢሆንም እሳቸው ግን አልተባረሩም ነበር።

ይህን አስመክቶ አዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አቶ ጂረኛ “ውሸት ነው። ማን ናቸው ሚኒሊክ። መረጃችሁን መርምሩ” የሚል ምላሽ በመስጠት ቃለ ምልልሱ ሳይቋጭ “ጊዜ የለኝም” በማለት አቋርጠዋል። ተባባሪያችን ያናገራቸው አንዱ ተባባሪ የኮሚቴው አባል “ዝርዝር የምለው ነገር የለም። ግን ብዙ ብር ተለቋል። በቅርቡ ብሩ እርስ በርስ ያጣላቸዋል” ብለዋል።

ከአዲስ አበባ በዕለቱ ተናጋሪ በመሆን ሕዝብ እንዲቀሰቅሱ የተመረጡት እና ፈቃደኛ ያልሆኑት ግለሰቦች ዝርዝር ለአዲስ ሪፖርተር ደርሷል። ይሁን እንጂ ሰዎቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ስማቸውን ይፋ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም። አቶ ጅሬኛ ግን “ሰዎቹ እምቢ ያሉበት ምክንያት ለመረመር ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል።

በሌላ ዜና በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው ‘ምድር አንቀጥቅጥ’ ሰላማዊ ሰልፍ በስጋት እንዲቀር አሳብ መቅረቡን ከተሰብሳቢዎች ለመስማት ትችሏል። ከኢምግሬሽን ጉዳይና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ዲያስፖራው ተሰባስቦ ሊሰለፍ አለመቻሉ፣ በየብሄሩ ባሉ ፓርቲዎች የተለያዩ አቋም መያዙና፣ ከኤርትራው መሪ ጋር የተጀመረው ጥምረት በፈጠረው ቅሬታ መነሻነት እንደተባለው ሁሉም እጅ ለጅ ተያይዞ ሊወጣ እንደማይችል የገመገመው የቴክኒክ ኮሚቴው ስውር አለቆች፣ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እንዲካሄድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ተባባሪያችን እንዳለው በቀጣይ ተቀማጭነታቸው ኢትዮጵያ የሆኑ ፓርቲዎች በቅብብል ሰልፍ ይጠራሉ።

በፓርቲዎች ክርክር ጥምረትን የወከሉት የኢህአፓ አመራር “ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ የለም” በማለት መናጋራቸው ይታወሳል። ዛሬ ኢህአፓ በኢትዮጵያ ምርጫ ማድረግ የማይቻልበትን ነጥብ ዘርዝሮ ምርጫ ሊወዳደር እንደማይችል ፍንጭ በመስጠት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ኢህአፓ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱን አስመልክቶ “ያኔ ቅጽል ስሜ ሌኒን ነበር” ያሉ አስተያየት ሰጪ፣ “ምንም ሳናውቅ የዛኔ በእናሸንፋለንና እናቸንፋለን ተቧድነት ያለቅነው በኢህአፓ የተልዕኮ ጥምቀት ነው። ዛሬ የሚሸወድ ትውልድ የለም። ዘመኑ የመረጃ መሆኑን የዘነጉ ይመስላል” ብለዋል።

የትብብር መሪዎች ኢትዮ ኢንሳይደር ላይ ቀርበው “ያስቀመጥናቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በምርጫ መወዳደር ከአጃቢነት የዘለለ ትርጉም አይሰጠንም” በማለት ምርጫውን ጥለው እንደሚወጡ ይፋ አድርገዋል። ይህን ያነሱት አስተያየት ሰጪ “ኢህአፓ ከወደቀበት ተነስቶ በዚህ ደረጃ መንቀሳቀስ የቻለው በምን መነሻ ነው። በጎኞሽ የሚሰራው ከእነ ማን ጋር ነው? ነዳጅስ ከየት አገኘ? የትኛው የእምነት ተቋምን ተወዳጀ?” የሚለው ለዚህ ምርጫ ሳይሆን ለታሪክ ሊጠና እንደሚግባ ጠቁመዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የሱኒ ሃገራት ዓለም ፤ በስሜትና በተጨባጭ እውነታ መካከል ያለው ልዩነት፤ የአህመዲን ጀበል የግሉ ጂኦ-ፖለቲካ

በዘመናዊው ጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ትክክለኛው ሃይል የሚለካው በቴክኖሎጂ ልዕልና፣ በኢኮኖሚ...

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

የአገር አለኝታ ሠራዊታችን በሰለጠነ የሰው ኃይልና ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ...

ምርጫ ቦርድ በሚያስገድዱ ላይ የእግድ ዕርምጃ እወስዳለሁ አለ፤ ምዝገባ ሊጠናቅቅ ነው

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ...