ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ ወይስ የ “ሁለገብ ትግል” እንደራሴ፤ “ከፈጣሪ የለም” ወደ ብሉይ ምሁር የአመራር ሽግግር ሚስጢር

Date:

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት መግቢያ በር ላይ ቀይ ብጫቂ ጨርቅ ይታያል። በውቀቱ ከተገደለ የኢህአፓ ባል ላይ ልብስ ላይ ነዋሪዎች የተቀራመቱት የመሃል አራዳ እግር ኳስ ቡድን መለያ ነው፤ መሀል አራዳ የኢህአፓ መለያ ነበር። እያንዳንዱ እናት መዋጮ የሚከፍልለት ቡድን ነበር። ኢህአፓ በጀመረው የከተማ ውስጥ የትጥቅ ትግል ስለባ የሆነው ተጫዋች ሲገደል ህዝቡ ማሊያውን በታጥሶ ለትዝታ የመግቢያ ብሩ ላይ አንጠለጠለ። ያ “የሁለገብ ትግል” ከአራት አስርት ዓመታት በኋላ እያኮበኮበ ይመስላል። ያለፈው የሚጸጽተኝ የኢህአፓ አንጋፋ አባል ነኝ። ድሮ ለሚስጢር ሲባል ግልጽ አመራር አልነበረም። በድንግዝግዝ ወጣቱ አለቀ። እናት ያለ ጧሪ ቀረጭ ዛሬም ድንግዝግዝ እንዳለ እየታየ ነው። ወላድን ዳግም የሃዘን ማቅ እንዳታለብሱ!! “በውጭ የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ አሁን ላይ አያዋጣም። ሰሚ የለውም። እውስጥ አገር ቤት ያለውን አመጽ በብር እየደገፉ ማቀጣጠል አዋጪ ነው” ሲሉ በጆሮዬ ሰምቻለሁ። ማሳሰቢያ ቢሆን ይህን ጽፌያለሁ

ነጻ አስተያየት | በሰለሞን ብሩ | ዋሽንግቶን

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አወቃቀሩ ምስጢራዊ እና በጋራ አመራር (Collective Leadership) የሚመራ ድርጅት እንደነበር ይታወቃል። ይሁን እንጂ በድርጅቱ ታሪክ በተለያዩ ሰዎች ተመርቷል። ነሐሴ 1964 ዓ.ም. በርሊን፣ ጀርመን መመስረቱ የሚነገርለት ኢህአፓ በብርሃነመስቀል ረዳ፣ ጌታቸው ማሩ፣ ተስፋዬ ደበሳይ፣ ዘርዓይ ዕቁባዝጊ፣ ክፍሉ ታደሰ ወዘተ በመሳሰሉ እግዚአብሔርን በአደባባይ በሚክዱ ማርክሲስቶች ሲመራ ቆይቷል። ይህ ትግሉን በኪሳራ አወራዶ፣ በ“ያ ትውልድ” ማዕረግ በጥቁር መዝገብ ተመዝግቦ የተረሳ ድርጅት አሁን ላይ ኋይማኖታዊ ካባ ተላብሶ “ቅድመ ሁኔታ” በማስቀመጥ ስሙ እየተነሳ ነው።

“መጋቢ ብሉይ” የሚለው ማዕረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስርዐት በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ትርጓሜ ላይ ከፍተኛ እውቀትና የማስተማር ብቃት ላላቸው ምሁራን የሚሰጥ ልዩ ማዕረግ ነው። የዛሬው  የኢህአፓ ፕሬዚዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ተስፋ በዚህ ዘርፍ እጅግ አንቱ የተባሉና ለዓመታት መጽሐፍ ቅዱስን ሲያስተምሩ የቆዩ በመሆናቸው ነው ይህን ስም ያገኙት። እናም እሳቸው ኢህአፓን መምራት ከጀመሩ በኋላ ፓርቲው የ“ያ ትውልድ” ካባውን አውልቆ በዚህ ደረጃ ድፍረት ተላብሶ ህዝብ ፊት እንዴት ሊቆም ቻለ? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። ከዚህም በላይ የክርስትና እምነት ምንጭና ቁልፍ የሆነውን አምላክ የካደ ድርጅት፣ አንድ የብሉይ ኪዳን መመህር እንዲመሩት እንዴት ወሰነ? በርካቶችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው።

ኢህአፓ እንደ ሌላው [ሞዐ ተውሃዶ]

የፋኖ “መስራች ነኝ፣ ከእኛ ትዕዛዝ ውጪ እንሆናለን ካሉ ይሞክሩት” የሚሉት አቶ ፋንታሁን ዋቄ ከመዐዛ መሐመድ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ፋኖን ያደራጁት ብቻ ሳይሆን፣ አሁንም ፋኖ እየተመራ ያለው በሞዐ ተሐድሶ አስተሳሰብና እሴት እንደሆነ በይፋ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አቶ ፋንታሁን ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ስለ ሞዐ አደረጃጀትና ሃሳብ ሰምተው የሞዐ አደራጆችን ሲያነጋግሯቸው ሃሳቡን እርሳቸውም አምነው የተቀበሉት ብቻ ሳይሆን “የኔም ሃሳብ ነው፣ በሉ እኔና እናንተ አልተነጋገርንም” ብለው ሁለቱም በየፊናቸው እንዲሠሩ ተስማምተው እንደነበር ገልጽ ተናግረዋል።

በፋኖ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ በርካታ ባህታውያንና የሃይማኖት አባቶች በግልጽም ሆነ በስውር ድጋፍ ሲሰጡ የሚታዩት ከዚሁ አቶ ፋንታሁን ይፋ ካደረጉት የድርጅቱ አመሰራረት ጋር በተያያዘ እንደሆነ በግልጽ ይነገራል። ይህንኑ የሚያረጋግጡ የተለያዩ የቪዲዮ ማስረጃዎች በፋኖ ደጋፊዎች አማካይነት በማህበራዊ ሚዲያዎች መመልከትም የተለመደ ነው። በፋኖ ታጣቂዎች ደረትና መሳሪያ ላይ መስቀል ማየትም አዲስ አይደልም። ይህም ለትግሉ “ቅዱስ ጦርነት” (Just War) የሚል መልክ እንዲኖረውና ታጋዮቹ በሞራል እንዲጠነክሩ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ አደረጃጀቱን የሚያውቁ ይናገራሉ። በተቃራኒው የሌሎች እምነት ተከታዮችን በተለይም ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን ስጋት ላይ እንደጣለም ጎን ለጎን መረጃዎች ይወጣሉ።

በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ላይ ሳይቀር የፋኖ ታጣቂዎች ተናጋሪና ቡራኬ ተቀባይ ሆነው መታየታቸው ብቻ ሳይሆን፣ የ”ሞተዋህዶ” አርማዎችና የሃይማኖት መዝሙሮች በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ መዋላቸው የሁለቱን አካላት ስውርና ግልጽ ቁርኝት የሚያሳይ ተደርጎ እንደሚወሰድ በስፋት በሚነገርበት ወቅት ነበር አቶ ፋንታሁን ዋቄ “ፋኖን ያደራጀነው እኛ ነን” በማለት ጥምረቱን ገሃድ ያደረጉት።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢህአፓ መሪ ሆነው የመጡት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ከሞዐ ተዋህዶ አስተምሮት ጋር ያላቸው ትስስር፣ እንዲሁም ፓርቲው በገሃድና በጎንዮሽ የሚያሳያቸው እንቅስቀሴዎች “ኢህአፓ ሌላው የ ሞዐ ተውሃዶ? ክንፍ” ሆኖ እየሰራ እንደሆነ አመላካች ነው። የድርጅቱን የማህበራዊ ገጽ እንቅስቃሴዎች የሚቀባበሉትም ከዚህ መስመር ጋር የሚታውቁ ክፍሎች መሆናቸው እሳቤውን ያጎላዋል። ሚስጥረ ስላሴ የምትባለዋ ታዳጊ ድሮ በፎቶዎቿ የማትጠቀምበትን “የአንገት ማህተብ| አተልቃ ከመስቀል ጋር ማሳየቷም ከዚሁ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የሚገልጹ በማህበራዊ ሚዲያ ሳይቀር ሲጎነታትሏት ይታያል።

ማርች 5 ቀን 2026 የቨርቹዋል ስብሰባ

ይህንን ስብሰባ ተከታትያለሁ። በስብሰባው አርባ የሚሆኑ ሰዎች ታድመው ነበር። ከሚታወቁት “የዛ ዘመን” ኢህአፓ አመራሮች አቶ መርሻ፣ ክፍሉ ታደሰ፣ አቶ ብርሌን ጭምሮ ከተለያዩ ስብሰቦች፣ ማህበሮች፣ ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች የተውጣጡ ተሳታፊ ነበሩ። ከተሳታፊዎቹ መካከል በውክልና ወይም በቀጥታ አቶ ነዓምንና አቶ ልደቱ በሚመሩት የአመጽ አደራጅ ቲክኒክ ኮሚቴ ውስጥ የሚሳተፉ አሉበት።

በዚህ ስብሰባ ላይ ከአዲስ አበባ ስማቸውን ለጊዜው ልተወውና ሶስት የድርጅቱ አመራሮች ተገኝተው ነበር። በስብሰባው ላይ አቶ ብርሌ “ደጋግማችሁ አስቡበት” በማለት ምርጫው እንዴት እንደሚከሽፍ በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ መስራት እንደሚገባቸው ያሳስቡ ነበር።

ነገሩን ግልጽ ለማድረግ አቶ ብርሌ አመጽ ለማደረጃት በተቋቋመው ቡድን ውስጥ የቴክኒክ ኮሚቴው አባል ሲሆኑ፣ በቀጥታ ያስተላለፉት መልዕክት አቶ ነዓምን ደጋግመው የሚሰጡትን መመሪያ ነው። አቶ ነዓምን በአሜሪካ የሻዕቢያ መመሪያ አስፈጻሚ እንደሆኑ ይታወቃል። እሳቸው አሁን ላይ እንዲያስፈጽሙ የታዘዙት ወይም የወረደላቸው “መደብ” በማንኛውም አግባብ ምርጫ በኢትዮጵያ እንዳይካሄድ ማድረግ ነው። አቶ ብርሌም “ተከተል አለቃህን” እንዲሉ ይህንኑ ነበር “ደጋግማችሁ አስቡበት” በማለት ያሳሰቡት። አቶ ብርሌና አቶ ነዓምን በቅርቡ በኢኤምኤስ ላይ አብረው ቀርበው እየተጋጋዙ ኢትዮጵያን ሲያጠቁሩና ሕዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ ፕሮፓጋንዳ ሲረጩ እንደነበር ይታወሳል።

እነሱ ኢትዮጵያን ሲያጠቁሩ ፕሮፌሰር መሐመድ ሃሰን የሚባሉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ የፕሮፓጋንዳ አገልጋይ ወይም / “ የፖለቲካ አቃጣሪ” ይሏቸዋል/ በሌሎች ሚዲያዎች ቀርበው ኤርትራን ገነት፣ ኢሳያስን ሊተኩ የማይችሉ መሪ፣ በኤርትራ ለአንድ ቀን ቀርቶ ለደቂቃዎች መብራት የማይጠፋባት፣ መግብ የተነበሸበሸባት፣ ዜጎቿ እጅግ ደስተኛ የሆኑባትና ዩኒቨርስቲዎች የበዙባት ወዘተ እያሉ ኢሳያስ መለአክ፣ ኤርትራን የምድር ላይ ገነት እያደረጉ በንጽጽር ይናገሩ ነበር። እንደው ለመረጃ አነሳሁት እንጂ አሳቡ ዋናው ጉዳዬ ስብሰባው ነውና ወደዛው ልመለስ።

እናም በዚህ ስብሰባ አቶ ብርሌ ማስጠንቀቂያም፣ ማሳሰቢያም ሲሰጡ፣ ቀጥሎ የተነሳው የትጥቅ ትግል ከሚያደርገው ፋኖ ጋር እንዴት መስራት እንደሚቻል ነበር። ከዛም እንደ ፋኖ ባይሆንም ከኦነግና ከትህነግ ኃይሎችና ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ጋርም አብሮ መስራት እንደሚገባ ተነስቷል። ይህ እንግዲህ የሰማሁት ነው። ዝርዝሩ እንተወውና “የተዘረጋውን የሞአ ተዋህዶ መስመር የተጀመረው ስራ እንዲቀጥል” መባሉን ጠቆም ማድረግ እወዳለሁ።

“ኢህአፓ ሕዝባዊ እምቢተኛነትን እንዴት ያነሳሳል?” የሚለው ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባ የተወከላችሁት “ገንዘብ ያስፈልገናል” በሚል አክርራችሁ ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት ብር እንደሚሰባሰብ፣ ብር ለማሰባሰብ ቤተክርስቲያናት ሳይቀር እንዲጠየቅ፣ ይህንኑ ተግባር በውጭ ያሉት ደጋፊ የሃይማኖት አባቶች በተለመደው አግባብ ሊሰሩበት እንደሚገባ ምላሽ ተሰጥቷል። በስብሰባው ላይ ብሩን እንዴት እንደምትጠቀሙበት አልተዘርዘርም እንጂ ለተሰጣችሁ የቤት ስራ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ መተማመን ላይ መደረሱ በወቅቱ ፈገግ አሰኝቷችሁ ነበር። አቶ መርሻና አቶ ክፍሉም ድጋፍ ሰጪ ነበራችሁ። ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያም ጭምር።

የቀደመው ዓይነት የኦሮሞና አማራ ጥምረት ጥንቃቄ እንደሚያሻው በዚሁ ስብሰባ ተነስቷል። አንድም ኦሮሞ ባልተገኘበት በዚህ ስብሰባ ላይ “ጥምረት የሚባል ነገር ጥንቃቄ ያሻዋል። መጥለፍ እንዳይመጣ” በሚለው አሳብ ላይ ጥብቅ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ቀርቦ ነበር። ባልናገርም የገረመኝ ጉዳይ አንድም ኦሮሞ በሌለበት፣ አንድም የኦሮሞ ድርጅት ባልተወከለበት ስብሰባ ላይ “ጥንቃቄ” መባሉ ግራ አጋብቶኝ ነበር።

ከስብሰባው በኋላ እንደ እኔው ግራ የገባው አንድ ወዳጄ፣ “አገር ቤት ያሉት ታጣቂዎች ህብረት ፈጥረዋል” ብሎ አስረዳኝ። ማብራሪያው ብዙም ባያስኬደኝም፣ “ከተስማሙ ታዲያ መፍናቀል፣ በቅርቡ ኃይማኖትና ብሄር ላይ ያተኮረ ግድያ ለምን ይፈጸማል?” የሚል ጥያቄ አንሰተን ተወያየን። ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

እንደ ማጠቃለያ

የቤተክርስቲያን አደጋ ላይ ናት መባል ለፋኖ የትጥቅ ትግል ትልቅ ግብአት እንዲሆን ታስቦ የሚሰራበት አንድ አቅጣጫ ነው። በተለይ በአማራ ክልል ከዕምነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮች ህዝብ በቀላሉ የሚገዛቸው ናቸው። ይህ የኃይማኖት ወይም የእምነት ጉዳይ ችግር ወይም አደጋ ሆኖ በእምነቱ መሪዎች ሲቀርብ ሕዝብ እንዲቆጣ ያደርጋል። በዚህ መነሻ የፋኖ መጠናከር ለ”ሞተዋህዶ” ደጋፊዎች እንደ መከላከያ ጋሻ ተደርጎ እንዲወሰድ ተደርጓል። እናም ጫማ ሰቅሎ የነበረው ኢህአፓ ድጋሚ የተወለደው እዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ነው።

የትጥቅ ትግል በመሬት ላይ ያለውን የመንግስት መዋቅር በማዳከም እና የጸጥታ ኃይሉን ትኩረት በመበተን ለሰላማዊ ትግሉ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ስለሚታመን፣ ሰላማዊ ሰልፈኞች ወይም የሲቪል አንቅስቃሴዎች በመንግስት ሲታፈኑ ለትጥቅ ትግሉ አዳዲስ ታጋዮችንና የገንዘብ ድጋፍን ለማግኘት አመቺ ግብአት ወይም (Justification) ስለሚያገለግል፣ ኢህአፓ ይህን ሚና አብሮ ከተጣመራቸው ጋር ይሰራል። ሲከለከል “ድምጹን ያሰማል” የተደራጀው ሚዲያ በቅብብል መንግስት ላይ ይረባረባሉ።

የዚህ ስልት ዋና ዓላማ በሽግግር ስም መንግስትን መጣል ነው። ይህ አቅጣጫ አቶ ነዓምን በገሃድ ከሻዕቢያ ተቀብለው በአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ቡድኑ ስብሰባዎች ላይ ግልጽ እንዳደረጉት በሁሉም አግባቦች መንግስትን ማስጨነቅ። ሕዝብን ሆድ ማስባስ እና የተቀመጠውን ዓላማ ማሳካት ነው።

ኢህአፓ ከተቀናጃቸው ጋር ሆኖ በፓርቲዎች ክርክር በገሃድ “ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ የለም” በማለት የሽግግር መንግስት እስክስታ እየወረደ ነው። ከማርች አምስቶ ስብሰባ በኋላ /ማርች 30 የተደረገም አለ/ የኢህአፓ ዋና ፀሀፊ ምስጢረ ስላሴ ታምራት በውጭ ካሉ የሚታወቁ የሻዕቢያ ተከፋይ ሚዲያዎች ጋር፣ ከትግራይ እንዲሁም በአዲስ አበባ የተለያዩ መድረኮች ከአምክንዮ ያፈነገጡ ጮርቃ አሳቦችን እያነሳች ማገዶ ለመሆን ስትዳክር በማየቴ “ረጋ በይ እህቴ፣ ኢትዮጵያ የተሰራችበትን አሁናዎ የፖለቲካ ኬሚስትሪ ተረጂ፣ ለውጥ እንዴት ሊመጣ እንደሚችል መርምሪ፣ በማህበራዊ ሚዲያ የተቀሰሩ ጣቶች ጋጋታ አትመርቅኚ፣ ብዙዎች በልጅነታቸው እንደ አንቺ ስተው አስተዋል” ለማለት ነው። ከሁሉም በላይ ኢህአፓ ፈጣሪውን ከማካዱ በላይ በግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ሶሪያና ኬንያ ያለውን ታሪክ መርመሪ።

የብሉይ ልሂቁን አዲሱ መሪ የምመክረው ባይኖርም፣ አሁን የተጀመረው በተለያዩ ከተማዎች ሰልፍ የማድረጉን ጉዳይ ለድርጅታችሁ በመተው ሁለት ጥያቄ ላንሳልዎት፣

በዝግና ወይም በሚስጢር የሚያደርጉትን የተለያዩ ኝንኙነቶች እንተወውና እርስዎም እኔም በምናውቀው፣ ድርጅትዎ እየመከረ ያለው የትጥቅ ትግል ከሚያደርጉ ድርጅት አመራሮች ጋር ነው። ይህ ደግሞ በአገሪቱ ህግ ክልክል ነው። ይህ ማስረጃ ተጠቅሶ እርስዎም ሆኑ ሌሎች ህግ ፊት ብትቀርቡ እንዴት አድርገን መንግስትን እንወቅሳለን? እንዴት አድርገን እንቃወማለን? ይህን ጥያቄ በግልዎ፣ ለራስዎ ይመልሱ።

ሌላው የተዘነጋው ኢህአፓ የትኛውን ካባ አልብሰውት ነው በዚህ ደረጃ ድፍረት አግኝቶ አደባባይ የወጣው? እኔ አባል ስለነበርኩ የረገጥነውን ቀይ ምስመር ሁሉ ሰላማውቀው አይዋሹኝም። ከዋሹኝም የመረጃ እጥረት ሊሆን ስለሚችል በዝምታ አልፈዋለሁ። ግን እርስዎን አመራር ያደረገውው የድሮው፣ በሕይወት ያለው ሽማግሌው”እግዚአብሄር የለም” ባዩ ቡድን እንዴትና በምን ውል መደዎት? ለኢህአፓ አዲስ ሕይወት የዘራውን የኃይማኖት ክንፍ ሊያቀጣጥሉ?

የእርስዎ ፓርቲ ያለበት ጥምረት ባቅረባቸው እጩዎች ምርጫውን ሙሉ በሙሉ ቢያሸንፍ እንኳን መንግስት አይመስረትም። ወይም መንግስት መመስረት የሚያስችል ብዛት ያለው እጩ አላቀረባችሁም። ይህ የማን ስህተት እንደሆነ በመርመር መስራትና በኦሮሚያ፣ በፋር፣ በሶማሊ፣ በድሬደዋ፣ በቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ወዘተ ክልሎች መመርጥ የሚያስችል አቅምና ተፈላጊነት አለን? አዲስ አበባስ እንችላለን? በሚል ስሌት አስልቶ ለአሁኑ የተገኘውን በመያዝ፣ ለቀጣዩ ምርጫ መስራት ለምን ዳገት ሆነባችሁ? ለማንኛውም የመሐል አራዳን የሰራተኛ ሰፈር ታሪክ ለአብነት ማስታወስ አመጽን እንድንጠየፍ ያደርጋልና!!

ለመንግስት የማሳስበውና አስደራ የምለው ሆደ ሰፊ እንዲሆን ነው። በቃኝ። በቀጣይ አሁን “ሰልፍ ሰልፍ” የሚባልበት የኢህአፓ ጥሪ የገቢ ምንጭ፣ እንዴት ገንዘቡ እንደሚዘዋወር፣ በእነማን በኩል እንደሚላክ ዘርዘር አድርጌ እምለስበታለሁ። ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ ስገባ አባቶቼ ቅር እንደማይላችሁ አምናለሁ።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ

በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው 'ምድር አንቀጥቅጥ' ሰላማዊ...

የሱኒ ሃገራት ዓለም ፤ በስሜትና በተጨባጭ እውነታ መካከል ያለው ልዩነት፤ የአህመዲን ጀበል የግሉ ጂኦ-ፖለቲካ

በዘመናዊው ጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ትክክለኛው ሃይል የሚለካው በቴክኖሎጂ ልዕልና፣ በኢኮኖሚ...