“ውሻዬን ሸጬ ቀበሮ ገዛሁ” እጅ የሰጠው ማስረሻ ሰጤ፤ ገዱ አንዳርጋቸው አገር ቤት እንዲገቡ ወዳጆቻቸው ሽምግልና ሊጀምሩላቸው ነው

Date:

አዲስ ሪፓርተር ባህርዳር፡በአማራ ክልል ከመንግስት ጋር መሳሪያ አንስተው ግጭት ውስጥ ከገቡት የተለያዩፋኖ አደረጃጀት መሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ማስረሻ ሰጤ ከጀሌዎቹ ጋር ለመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እጁን መሰጠቱ ታውቋል። የነበረበትን የጫካ ቆይታውሻዬን ሸጬ ቀበሮ ገዛሁእንደማለት መሆኑ መናገሩ ተሰምቷል።  አህፋድ በይፋዊ መግለጫው ማስረሻ ሰጤን እና መሥፍን አባተን (መስፍን ከፈለኝን) ከአመራርነት ማገዱን በመግለጽ ዜናውን አረጋግጧል።

ማስረሻ ከባልደረቦቹ ጋር ከለላ ወረዳ ከሃያ የሚልቁ አጃቢዎቹ ጋር ነው እጁን የሰጠው። ጋስጫ አባ ጊዮርጊስ ሕንጻ ማረፊያ ተዘጋጅቶላቸው የቆዩ ሲሆን ዛሬ ወደ ባህር ዳር ይጓጓዛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።

ሁለቱ አመራሮች ለመንግስት እጃቸውን ከሰጡ በሁዋላ አፋህድ በይፋዊ መግለጫው እንዳለው ገምግሞና መርምሮ ዕግድ ጥሎባቸዋል፣ አክሎም ድርጅቱን ወክለው ምንም ዓይነት ንግግር እንዲያደርጉ ውክልና እንዳልሰጠ ማስታወቁ እጃቸውን የሰጡት አመራሮቹ እንደሚከዱት አስቀድሞ የተረዳና፣ እነዚሁ አመራሮች ወደፊት ይፋ የሚያደርጓቸው በረካታ ጉዳዮች ስለሚኖሩ ከወዲሁ ለመከላከል በማቀድ እንደሆነ ተመልክቷል።

ማስረሻ ሰጤና ግብር አበሮቹ እጁን የሰጠው በተስፋ መቆረጥ ይሁን በአሸማጋዮች ግልጽ ባይወጣም፣ ዜናው የመንግስትን የፀረ ሽምቅ ውጊያ ጥረት (counter insurgency effort) በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አንድምታ እንዳለው ተመልክቷ። በአማራ ክልል የሚካሄደውን የሽመቅ ውጊያ በቅርበት የሚከታተሉ ለአዲስ ሪፓርተር እንዳሉት የማስረሻ እጅ መስጠት የፋኖን የህቡዕ ድርድር በራሳቸው አመራር አንደበት ይፋ ማውጣት ነው። ድርጅቱም አስቀድሞ መግለጫ ለማውጣት የተገደደው ይህንኑ ፍርሃቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

ማስረሻ ሰጤ የፋኖ ትግል ውስጥ ራሱን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) ብሎ በሚጠራው አደረጃጀት ውስጥ አመራር ነበር።

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ሶስት አመት ሊሆነው ወራት የቀሩት ሲሆን፣ በዚህ ግጭት ምክንያት በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ህይወታቸውን፣ ኃብትና ንብረታቸውን አጥተዋል። በተጨማሪም ጉዳቱ በትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ከፍተኛ ኪሳራን ማድረሱ በራሳቸው በተማሪዎች ሳይቀር በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ ነው።

ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እጅ በሚሰጥበት ወቅት በትግሉን ላይ እጅግ ከባድ የሆኑ ወቀሳዎችን አቅርቧል። እሱ ሲመራው የነበረው የፋኖ ትጥቅ ትግልውሻዬን ሸጬ ቀበሮ ገዛሁየሚል ሆኗል በማለት ገልጸዋል። በተናካሽ ውሻ ተማረርኩ ያለውን ህዝብ፣ እርጉም ቀበሮ እንደሆኑበት ገልጿ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ትግሉ የጠራ ዓላማ፣ የዕዝ ሰንሰለት እና ዲሲፒሊን እንደሌለው በመጥቀስ፣ከዚህትግል ይልቅ የአማራ ህዝብ ከእኔ ነፍጥ ማውረድ ያተርፋል ባይ ነኝብሏል።

ትግሉ በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሳቸውን ጉዳቶች በተመለከተ ገበሬው ምርቱን መረን በለቀቁ ታጣቂዎች መዘረፉ፣ ሴቶች መደፈራቸው፣ ህጻናት ከትምህርት ቤት መቅረታቸው፣ እንዲሁም ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ከሱቅ በደረቴ ጀምሮ ታግተው ገንዘብ እንዲያመጡ ተደገደው እየተጠየቁ እንደሆነ እና እየሆነ ያለውን እና በህዝብ ላይ የሚደርሰውን መከራ ዘርዝሮ ለመናገር እንደሚከብድ አመልክቷል። ይህ ቅንጭብ አስተያየት በቀጣይ የሚያቀርባቸውንና ይፋ የሚያደርጋቸውን ሚስጢሮች ክብደት ከወዲሁ አመላክች ሆኗል።

በተመሳሳይ የፋኖ ዜና በአሜሪካን አገር የሚገኙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሽምግሌ መላካቸው ተሰምቷል። አቶ ገዱ ወደ አገር ቤት ለመግባት ፍላጎት በማሳየታቸው የተነሳ ምህረት እንዲደረግላቸው እየተነቀሳቀሱ ያሉት የቅርብ ጓደኞቻቸው ናቸው። የአዲስ ሪፖርተር የአሜሪካ ተባባሪ ከዲሲ ባገኘው መረጃ እንዳለው ሽማግሌዎቹ በኤምባሲ በኩል ጉዳዩን ለማቀረብ ጫፍ ደርሰዋል።

ለሽምግልናው ሲባል የሰዎቹን ስም ያልዘረዘረው ተባባሪያችን፣ አቶ ገዱ የትጥቅ ትግል አቀንቃኝ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ያላሰቡት ተግዳሮት አጋጥሟቸዋል። በተለይም በውጭ አገር ያለው ኃይል መከፋፈልና እሳቸው በወልቃይት ሕዝብ ላይ የፈጸሙት “ክህደት” ዕምነት አሳጥቷቸዋል። አቶ ገዱ የማራ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የደህንነት አማካሪ ሆነው ማገለገላቸው የሚታወስ ነው። በአሁኑ ሰዓት በሚኖሩበት አሜሪካ በመኪና ፓርኪንግ ስራ ተሰማርተው በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ዜናው እንደተሰማ ይህንኑ ስራቸውን የሚደግፏቸው ሲያደንቁላቸው፣ ሌሎች አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረ ከፍተኛ ዲፕሎማት በዚህ ስራ መሰማራቱ የብቃት ጉዳይን የሚያመላክት እንደሆነ ጠቅሰው ሲተቹ ተሰምተው ነበር።

በአሜሪካ የኢትዮጵያን ኤምባሲ ለማነጋገር ቢሞከርም አልተሳካም። መንግስት ወደ ሰላም ለሚመጡ ሁሉ በሩ ክፍት መሆኑን ከሳምንት በፊት በሌላ ዜና አስተያየት የሰጡን ባለስልጣን ጠቅሰን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...