መከላከያ በጎጃም ልዩ ኦፕሬሽን ዋናውን የፋኖ የኦንክሪት ምሽና ማዘዣ ተቆጣጠረ፤ ሕዝብ” ጥቆማ እየሰጠ ነው”

Date:

አዲ ሪፖርተር – ምሥራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው የጎጃም ቀጣናዎች ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን 364 የታጠቁ አባላትን መደምሰሱንና በአግቢኝ ልዩ ስሙ አዲስ ዓለም ከመሬት በታች የተገነባ ኮንክሪትና የማዘዣ ጣብይና እና ለቁስለኛ ህክምና መስጫ ሲገለገልበት የነበረውን ባንከር መቆጣጠሩ ይፋ ሆነ፤ “ምሬት ያንገፈገፈው የጎጃም ሕዝብ ከአገር መከላከያ ጋር በመሆኑ ጥቆማ ሰጥቷል” ሲል የሕዝቡን ተነሳሽነት አድንቋል።

ሠራዊቱ ከታህሳስ 01 እስከ ታሕሳስ 13/2018 ዓ.ም በወሰደው ርምጃ 162 ታጣቂ ኀይሎችን በመደምሰስ፣ 39 በማቁሰል፣ 19 ማርኳል፡፡ 62 እጅ የሰጡ ሲሆን ፣ 85 ወዶ ገቦች ሰላምን መርጠው ገብተዋል፡፡  ከተደመሰሱት ውስጥ በቡድኑ አጠራር 11 ክ/ጦር አመራሮች እና 4 ሻለቃ መሪዎች እንደሚገኙበት የምሥራቅ ዕዝ ሚዲያ ዘግቧል፡፡ ከስር እናለ ቀርቧል።

ታህሳስ 11 ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ በተባለ ቦታ ታጣቂው ኀይል አለኝ የሚለውን ኀይል ከተለያየ ቦታ በማሰባሰብ በሶስት አቅጣጫ ለማጥቃት ሙከራ ቢያደርግም፣ በደረሰ መረጃ ከፍተኛ ሽንፈት አድርሶበታል፡፡ በዚህ ውጊያ 30 ጽንፈኛ ተደምስሷል፤  15 ቆስሏል ነው ያለው ዕዙ፡፡

ቡድኑ በሠራዊታችን በመመታቱ በአሁኑ ሰዓት እንደ አንድ አሀድ ተቀናጅቶ መዋጋት የማይችልበት ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ አለሁ ለማለት ከተለያዩ ቦታዎች ሀይል በማሰባሰብ ለሚዲያ ፍጆታ የሚሆን የድል ሽታ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ለሊማ ደደና ቀበሌ ከምሽቱ 4 ሰዓት በተወሰደ ኦፕሬሽን ጽንፈኛው ከዚህም ከዚያም ለቃቅሞ አዊ ዞንን ፣ ሰከላን ፣ አጎትን እና ሌሎች ቦታዎችን ለማሸበር ያዘጋጃቸው 58 ታጣቂዎች ተደምስሰዋል፡፡

ምሥራቅ ዕዝ ባለፉት 13 ቀናት ባካሄደው  ኦፕሬሽን ኤ ኬ ኤም/ክላሽ 119   ፣ ፒ ኬ ኤም/መትረየስ 2 ፣ ስናይፐር 1 ፣  የቃታ መሣሪያ 231 ፣ ቺቺ 1 ፣ ሽጉጥ 11 ፣ አር ፒ ጂ/ላውንቸር 1 ፡ ቦንብ 12 ፣ የፖሊስ መገናኛ ሬድዮ 3 ፣ የተለያዩ ጥይቶች ተተኳሽ 1ሺ481 ተማርከዋል፡፡ 3 መትረየስ ወድሟል፡፡

ቡድኑ ለጥፋት ተልዕኮ ሲጠቀምባቸው የነበሩ 1 ዘመናዊ ጀኔሬተር ፣ የህክምና መርጃ እቃዎች ፣ ጀነሬተር እና ሌሎች ንብረቶች በሠራዊቱ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሠራዊቱ በአግቢኝ ልዩ ስሙ አዲስ ዓለም የተባለ ቦታ ጽንፈኛው ኢንጅነር ቀጥሮ ከመሬት በታች ያሰራው ኮንክሪትና እንደ ማዘዣ እና ለቁስለኛ ህክምና መስጫ ሲገለገልበት የነበረውን ባንከር ጀግኖቹ ከፍተኛ ወታደራዊ ስልት በመጠቀም እና ቦታውን አነፍንፎ በማግኘት በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ችለዋል ብሏል የምሥራቅ ዕዝ ሚዲያ፡፡

እዙ በጠላት ላይ በተወሰደው ጠንካራ ምት ካሳሁን በላይነህ የተባለ የብርጌድ ሎጀስቲክስ የነበረ እና ደጉ መሸሻ የተባለ የቢትወደድ ብርጌድ ሎጀስቲክስ ኀላፊ የነበረ በሊበን በተደረገ ደፈጣ ከነ አጃቢው የተደመሰሱ ተደምስሰዋል፣ ይርጋ ጌትነት የተባለ የታጣቂ ቡድኑ ሻለቃ አዛዥ የነበረ፣ ባቤ ማናለኝ ሸርበው የተባለ የ3ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ በርጌድ አመራር ፣ ጋሻው ጥላሁን የተባለ ብዝራ ቀበሌ የሲቢል መሥተዳደር ሁኖ በጠላት ተሽሞ እየሠራ የነበረ እጃቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከነዚህ በተጨማሪም አንሙት መንጋው የሻለቃ ዘመቻ የነበረ ፣ መልካሙ አለምኔ መትረየስ ተኳሽ ፣ አጉማስ ሻንበል መሪ ፣ ብርሃኑ ወይም ሳተላይት የተባለ እንዲሁም 77ኛ ያሉት ክፍለ ጦር መረጃ በቅፅል ስሙ ንስር ተብሎ ሚጠራው የዘንገና ብርጌድ ም/የስው ሃይል ጭምር ተደምስሰዋል። ከተገደሉት ውስጥ ክ/ጦር አመራር ብሎ የሰየማቸው አራት አዛዦች እና ሰባት የሻለቃ አመራር ብሎ የሰየማቸው ይገኙበታል፡፡

አሁን ላይ የፀጥታ አካላት እና ኅብረተሰቡ ተናበው በመስራታቸው ጽንፈኛው መግቢያና መውጫ በማጣቱ 62 እጅ የሰጡ ሲሆን ፣ 85 ደግሞ ከመሞት መሰንበት ብለው ሰላምን መርጠው ገብተዋል፡፡  

ታጣቂ ቡድን ኀይሉ ተመናምኖ እና ከሕዝብ ተነጥሎ ጭንቅ ውስጥ በገባበት በዚህ ሰዓት የጎጃም ሕዝብ ከመሪዎቹ ጋር ውይይት በማካሔድ ዘራፊውን ቡድን እያወገዘው ይገኛል፡፡

ምሥራቅ ዕዝም ከሕዝቡ እና ከክልሉ የፀጥታ ኀይል ጋር በመቀኛጀት የጀመረውን ሕግ የማስከበር ግዳጅ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያለው የምሥራቅ ዕዝ ሚዲያ፡፡

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...