የጃልመሮ አማካሪና የኦነሰ ቃለ አቀባይ “የሕዝባዊ እምቢተኛነት” አመቻች ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ሆኑ

Date:

የጃልመሮ አማካሪና የኦነሰ ቃለ አቀባይ የሕዝባዊ እምቢተኛነት አመቻች ስራ አስፈጻሚ ሆኑ

አዲስ ሪፖርተር – የአቶ ልደቱ አብሮነት አቶ ነዓምን ከሚመሩት ቡድን ጋር ተመሳሳይ ስራ ሰለሚሰራ እንዲዋሃዱ በቀረበው መመሪያ መሰረት መዋሃዳቸው ይታወዳል። ተዋህደው የሕዝባዊ እምቢተኛነት አመቻች ግብረኃይል አቋቁመው ነበር። እሁድ በተደረገ ስብሰባ ሰባት አባላት ይኖሩታል በተባለ የስራ አስፈጻሚ ምርጫ ላይ ነው ሁለቱ የጉዳይ ባለቤቶች “ከጀርባ ሆነን እንሰራለን” በማለት ከአመጽ አመቻቹ ኮሚቴ ራሳቸውን አግልለዋል። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ጉዳዩ ከስደት ማመልክቻ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

አቶ ነዓምን በስራ አስፈጻሚነት ኮሚቴውን ማገልገል እንደማይፈልጉ ይፋ ሲያደርጉ “ባልመረጥም ስራውን ከጀርባ ሆኜ እንደማሰራ ታውቃላችሁ” ብለዋል። የእሳቸውን ከስራ አስፈጻሚነት መውጣት አስመልክቶ ተሰብሳቢዎች ያሉት ነገር የለም።ከስብሰባው የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው አቶ ልደቱ “እኔም ስራ አስፈጻሚ ውስጥ መግባት የለብኝም። አልፈልግም። ስራ ይበዛብኛል። በዚህም ላይ ልቤን ያመኛል” በሚል ተናገረዋል።

ይህን ጊዜ ኢንጂነር ሙሉጌታ ተነስተው “ልደቱ የሙሉ ጊዜ ፖለቲከኛ ነው። እሱ ይህን ስራ አልሰራም ካለ ማን ይሰራዋል?” በማለት ተቃወሙ። በፍጹም አይሆንም የሚል አቋም ያዙ። በሳምንቱ መጨረሻ፣ የሁለት ኮሚቴ ሊቀነበር የሆኑትና ብዙውን ጊዜ በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸው የሚታወቁት አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም በሰብሳቢነታቸው አቶ ልደቱን እንደሚጫኑ ተናገሩ።

አቶ ልደቱ የከረረ አቋም ሲይዙ ጣልቃ በመግባት አቅጣጫ የሚሰጡት አቶ ነዓምን አራት ሰው ከአንድ ብሄር ከሚሆን ለስብጥሩም ጥሩ ስለሚሆን አቶ ልደቱ ወጥተው በአቶ ደምስ እንዲተኩ ጫን አድርገው ተናገሩ። አቶ ልደቱም “አማራ” ላለማለት አማርኛ ተናጋሪዎች ከሚበዙ ሌሎች ቢካተቱበት ለስራው የተሻለ እንደሚሆን ጠቁመው የአለቃቸውን ሃሳብ አጠናከሩ። ከአቶ ልደቱ አብሮነት ወደ አቶ ነዓምን ቡድን ዝውውር ካደረጉ በኋላ የልቀመንበርነት ስልጣን የበዛላቸው አቶ ያሬድም አቶ ነዓምንን አምስነው አቶ ልደቱን ከምርጫው አስወጡ።

በምርጫው ወቅት “እኔ ሶማሌ ስለሆንኩ ነው የማልመረጠው” በማለት ፈገግታ የዘሩት ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ፣ ጨምሮ ሰባት አባላት ያሉበት አመጽ የሚያመቻች ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ተሰይሞለታል።

በስብሰባው መጀመሪያ ላይ አቶ ደምስ “ከፋኖዎች ጋር ስብሰባ አካሂደን ነበር፤ ጥሩ ስብሰባ ነው ያደረግነው፤ ለዚህ ነው የዘገየሁት” በማለት ሲናገሩ አቶ ያሬድ ቀበል አድርገው፣ “እኛም አድርገን ነበር። ሌሎችም ነበሩበት” ካሉ በኋላ “ስርዓቱ ርዷል። ልክ ኢህአዴግ ሲወድቅ እንደነበረው እየተደነባበረ ነው” በማለት የሰሙትን አወድሰዋል። በሁሉም አቅጣጫ መተባበር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

ከሰባቱ የስራ አስፈጻሚዎች መካከል በሌሉበት አንዱ ሆነው የተመረጡት የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት መሩ ጃልመሮ አማካሪና ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጂሬኛ ሶስት ተከታታይ ስብሰባዎችን መቅረታቸው ታውቋል። መጨረሻ በተገኙበት ስብሰባ ላይ አቶ  ጂሬኛ “ አካታች አይደላችሁም፣ ለብሄር ብሄረሰቦች እኩል ውክልና አትሰጡም” በማለት ተቃውሞ አንስተው እንደነበር የስበሰባው ተሳታፊዎች ተናግረው ነበር።

የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት / ኦነሰ ተወካይ አቶ ጂሬኛ ጉደታና የትህነግ ወኪል አቶ አባይ ለሁለት ስብሰባዎች ቀርተው ሰለነበር አቶ ነዓምን ሁለቱን የግብረኃይሉ አባላት “ቁልፍና አስፈላጊ” በማለት እነሱ የሌሉበት ምርጫ ጥቅም እንደሌለው አስታውቀው ነበር። ረቡዕ በንትርክ ያለስምምነት የተበተነው የዚሁ የአምጽ አመቻቹ ግብረኃይል በቅዳሜ ስበሰባው ነበር ዕሁድ በሚደረግ ስብሰባ ምርጫ እንዲደረግ አቋም የተያዘው።

አቶ ነዓምን በከፍተኛ የረብሻና ብጥብጥ ሪኮርድ ስላለባቸው፣ አቶ ልደቱ ውሳኔ ያላገኘ የስደት ማመልከቻ ስላላቸው በዚህ የአመጽ ማነሳሳቱ ተግባር ላይ መካፈላቸው አሁን ላይ አሜሪካ ከያዘችው አቋም አንጻር አስጊ በመሆኑ ከጀርባ መሆንን ሊመርጡ እንደቻሉ ግምት መኖሩን ዜናውን ያካፈሉን ይገልጻሉ።

የፋኖ ደረጃ ሶስት የሽብር ቡድን ውስጥ መመደብ የፈጠረውን ስጋት ተከትሎ በርካታ ሰዎች እርስ በርስ እየተወናጃጀሉ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ዲያስፖራው በጅምላ ሰልፍ የሚወጣበት አግባብ ዝቅተኛ መሆኑን ስለተረዱ አስቀድመው ለእነ አቶ ያሬድ ሰጥተው ሽሽት መምረጣቸው እንደሆነም ያስታወቁ አሉ’፣

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

አዲስ ሪፖርተር ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር...

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

አዲስ ሪፖርተር - በአዲስ መልክ እየተሳለ ያለው የዓለም የንግድ...

ዲያቆን ዳንዔል ክብረት ዕምነታቸውን ቀይረው “ጴንጤ ሆነዋል” የሚል የሚዲያ ዘመቻ እንዲከፈትባቸው ዕቅድ መያዙ ተሰማ

አዲስ ሪፖርተር - “ሙዓለ ጥበባት ዲያቆን ዳንዔል ክብረት እምነታቸው...

Official Statement Regarding the Human Rights Watch Report on the WTSH Zone

Prioritizing Sovereign Legal Frameworks and Evidence-Based Assessment Over Unverified...