በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት /አፋህግ/ መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙ ተበሰረ፤ በስነ ስራዓቱ ላይ ” ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር አያስፈልግም” ሲሉ ማስረሻ ሰጤ የክህደት ስምምነት ሲያደርጉ የነበሩና እያደረጉ ያሉ መኖራቸውን አመላከቱ። ቀደም ሲልም በርካታ መረጃዎች ሲወጡ እንደነበር ይታወሳል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙን ያስታወቀው የአማራ ክልል ነው። የክልሉ መሪ አገርጋ ከበደና ማሰረሻ ሰጤ የፊርማ ስነስርዓት ሲያከናውኑ የሚያሳይ ምስል አስደግፎ ክልሉ እንዳለው ስምምነቱ በአፍሪካ ሕብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ሲካሄድ ነው የቆየው።
ስምምነቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በፊርማቸው አጽንተውታል። በፊርማው ስነስርዓት ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋ ከበደ “ዛሬ ለክልላችን ሕዝብ የመጀመያው ትልቅ የሰላም ኩነት የተካሄደበት ቀን ነው” ሲሉ የተደረሰውን ስምምነት ታላቅነት አብስረዋል። በበርካታ መከራ እየተሰቃየ ላለው የክልሉ ሕዝብ ታላቅ ብስራት የሆነው ስምምነት ከጦርነትና ከቀውስ ለሚያተርፉ አካላት መርዶ እንደሚሆን በስምምነቱ የተደሰቱ እየገለጹ ነው።

“ከግጭት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፣ ከሰላም ሁሉም ያተርፋል፣ ስምምነቱ ለሰላም ወዳድ ሕዝባችን ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ነው ያሉት” ሲሉ ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አረጋ አስታውቅውዋል። የጫካ ቆይታቸውን የዘጉትና ወደ ስለማዊው መንገድ የመጣው ማስረሻ ሰጤ የነበረበትን የፋኖ ትግል “ውሻዬን ሸጬ ቀበሮ ገዛሁ” እንደማለት መሆኑ መናገሩ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
“የሕዝብና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ ወንድሞቻችን እንደ መንግስት አድናቆትና ክብር አለኝ” በማለት አቶ አረጋ ከበደ ሌሎች በጫካ ያሉ አገር ቤት ለመግባት እንዲነሳሱ የሚያደርግ ማነሳሻ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ፣ ማንኛውም ግጭት በመጨረሻ የሚፈታው በውይይትና በድርድር መሆኑን አመልክቶ፣ “ችግሮችና የሀሳብ ልዩነትን በንግግር መፍታት ፖለቲካዊ ሽንፈት ሳይሆን ጥበብና ብልጠት” ነው ሲል ተደምጧል። አክሎም “ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ተገቢ አይደለም” ሲል ምንም ሆነ ምን በአገር ክህደት መስለፍ አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሰው ሲተቹ እንደነበሩት ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁትን ፅብታቸውን አኑረዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ አዳዲ በበኩላቸው፣ ስምምነቱ የሀገሪቱን ቀጣይ መዳረሻ የሚያቃና ነው ብለዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






