ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ ኢዜማ እንደሚሳተፍ ይፋ አደረገ

Date:

ኢዜማ በዛሬው ዕለት 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ÷ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በሚያካሂድባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሕዝብ ይሁንታን ለማግኘት እሳተፋለሁ ብሏል።

የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ኢዮብ መሳፍንት በዚህ ወቅት ምርጫ የፖሊሲ አማራጮችን ማቅረቢያ፣ የተረጋጋ መንግሥት መመስረቻና የዴሞክራሲ ባህል መገንቢያ መሳሪያ መሆኑን ገልጸው÷ ምርጫውን ለዚህ ዓላማ ብቻ ለመጠቀም እንደሚሳተፍ ጠቁመዋል።

ፓርቲው ላለፉት አራት ዓመታት በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሕዝብን ድምጽ ለማግኘት የዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንና በቀጣይ 7 ወራት ውጤቱ የሚታይበት እንደሆነ አመልክተዋል።

የኢዜማ ፓርቲ ሊቀመንበር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ፓርቲያቸው በሰላማዊ መንገድ ብቻ መንግሥት ለመሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ፓርቲው መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻዎች ምርጫው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

መንግሥት ምርጫውን ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አንስተው÷ ገዥው ፓርቲ የሕዝብ ሃብትን ለምርጫ መቀስቀሻነት እንዳይጠቀም እንዲሁም በክርክርና ውይይት መድረኮች እንዲሳተፍ ጠይቋል።

መራጩ ሕዝብ ሃሳብን አመዛዝኖ እንዲመርጥ፣ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን አማራጭ አድርጎ እንዲመርጥ እና ዝግጅት እንዲያደርግ ፓርቲው በመግለጫው ላይ አስገንዝቧል፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከስሜት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ታቅበው የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ምርጫውን ለምርጫ ዓላማ ብቻ እንዲጠቀሙም ነው የገለጸው።

ኢዜማ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ከፍ በሚያደርጉ ተግባራት ላይ እንዲያተኩርና ባለፈው ምርጫ የታየውን የሎጂስቲክስ እጥረት ቀድሞ መፍታት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

በመራኦል ከድር

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተበተነ

አዲስ ሪፓርተር— በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት...

ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ እንቅፋት ገጠመው፤ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያ አማራጭ ሆነ፤

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን...

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ የብሉይ ምሁር አመራር ሽግግር ሚስጢር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...

ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ...