እንደ ህወሃት አቆጣጠር ጦርነት ታውጇል፤ የፌደራል መንግስት ዝምታን መርጧል

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ባለሙያ ነኝ። ጥሩ ገቢ ነበረኝ። ጥሩ እሰራ በነበረበት ወቅት ያፈራሁትን ንብረት ሸጬ ጨርሻለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ለዕለት ጉርስ ንብረታቸውን የሚሸጡ ብዙ ናቸው። ምክንያቱም ስራ የለንም። ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ሳስብ ይጨንቀኛል። ምን ዓይነት አለመታደል ነው” የሚለው የመቀለ ነዋሪ ነው።

“በነገሩን ዕቅዳቸው መሰረት ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በህገወጥ ምርጫ የተመረጠውንና እነሱ ራሳቸው ‘ህገወጥ ነበር’ ብለው ያመኑትን መንግስት በጉልበት መልሰዋል። ይህ በህወሃት አቆጣጠር ጦርነትን ማወጅ ነው። የሚጠበቀው የፌደራል መንግስት፣ የለውጥ ኃይሎችና የትግራይ ሰላም ኋይሎች ምላሽ ነው” ሲል አስተያየቱን የሰጠን ሌላ የከተማ ነዋሪ ነው።

ሁለቱን አስተያየት ሰጪዎች ጨምሮ በርካቶች እንደሚሉት የዶክተር ደብረ ፂዮን ቡድነ ወደ ቅድመ ጦርነቱ ወቅት ተመልሰዋል። ይህ ማለት ደግሞ ህወሃት ራሱ ጦርነቱን ቀስቅሷል ማለት ነው”

አሁን በመቀለም ሆነ በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ዘንዳ ያነጋገረው እና ስጋት ያስከተለው ጉዳይ ዛሬ ዶክተር ደብረጽዮን ፕሬዝዳንት ተደርገው ሲሾሙ፣ የፕሪቶሪያን የሰላም አማራጭ ስምምነት ህወሃት በራሱ ፍቃድ አፍርሷል ማለት ነው። ራሱ አስቀድሞ እንዳለው ከፌዴራል መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት አቋርጧል። የፌደራል መንግስት በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ምላሽ ባይሰጥም መከላከያ ትግራይ መግባት የሚያስችለው ሁሉም ዓይነት ህገመንግስታዊ መብትና፣ የዲፕሎማቶች ድጋፍ አለው።

“ዛሬ በትግራይ መፈንቅለ መንግስት ተደርጓል። መፈንቅለ መንግስቱ መካሄዱ ብቻ ሳይሆን፣ እራሱን የሾመው ቡድን ህጋዊ ዕውቅናና  ህጋዊ ሰውነት የሌለው በመሆኑ ለሚደርሰው ኪሳራ በሙሉ ተጠያቂ ይሆናል” ሲሉ የትግራይ አንድ ተቀናቃኝ ፓርቲ ተናግረዋል። አክለውም “ጦርነት እንዳይነሳ የምንችለውን ሁሉ እያደርገን ነው። የትግራይ ህዝብም ከጎናችን ነው። ህወሃት ያተርፋል ብለን አናስብም” ብለዋል።

በትግራይ ተቀባይነት እንዳላገኘ ከየአቅጣጫው መረጃ የሚወጣበት መፈንቅለ መንግስት ከመደረጉ ቀደም ብሎ በርካታ ህዝብ ትግራይን ለቋል። ከፍተኛው ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ጦርነትን ሽሽት በቻሉት መንገድ ከተወለዱበትና ከኖሩበት ከተማ ወደ አዲስ አበባና አጎራባች አካባቢዎች ሄደዋል። ድንበር ጥሰው ወደ ጅቡቲ፣ የመን፣ ሳኡዲ ወዘተ ያቀኑም ጥቂት አይደሉም።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጦርነት እንዳይቀሰቀስና የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳይሸራረፍ በተማጸነበት ቅጽበት እንዲህ ያለ ውሳኔ መወሰን ፍጹም ስህተት መሆኑን የሚናገሩ፣ ህዝቡ፣ በታጣቂው መካከል ያለው ጫና፣ የስነ ልቦና ቀውስ እና የቅርብ ጊዜው ጦርነት ትራውማ፣ አንድ ላይ ተዳምረው ትግራይን የጭንቀት ማዕከል አድርጓታል።

ሰኞ ዕለት በመቀለ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ ውይይት ተሰብሳቢዎቹ “ዳግም ወደ ጦርነት ልታስገቡን ነው” በሚል ከፍተኛ ተቃውሞው ማሰማታቸውን በስፍራው የነበሩ አመልክተዋል። የትግራይ ተወላጅ የዲያስፖራ አባላትም፣ በተመሳሳይ ተቃውሞ ቢያሰሙም እነ ዶክተር ደብረጽዮን ሊቀበሉ እንዳልቻሉ ያመለከቱ፣ ከዚህ በኋላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት እንዳልቻሉ አስታውቀዋል።

የዶክተር ደብረጽዮን ቡድን ምርጫ ማድረጉን ከማስታወቁ በፊት የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “የአባይ ግድብ ጎርፍ ለሱዳን ሃያ ሚሊዮን ሕዝብ ስጋት ሆኗል” በማለት በርካታ የቴክኒክ ህጸጾችን ዘርዝሮ “በአስቸኳይ እንደራደር” የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። በማስከተል ሱዳን የኢትዮጵያን መንግስት ከሰሰች። የአርሚ ሰባን እና ሌሎች የሚታወቁ ታጣቂዎችን እያስታጠቀች ኢትዮጵያን የምታስወጋዋ ሱዳን “ኢትዮጵያን ከሰሰች” በሚል ለሽብር ቡድን ደግፈው የሻዕቢያ አገልጋይ ናቸው የሚባሉ ሚዲያዎች አገራቸውን ሲከሱ ዋሉ። ይህ እንዳበቃ በትግራይ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ህውሃት በፎቶ አስደግፎ አወጀ። ይህንን መገጣጠም እንደማይሉት ያስታወቁ ወገኖች “የታደሰ ወረደ ቤታቸው ተቀምጠው ድራማውን መኮምኮማቸው እንጂ ሌላው ሁሉ በዕቅድ የሚሰራ ስለሆነ አይገርምም” ብለዋል።

ይህ እስከተጻፈ ድረስ “ወደ ትግራይ መሬት የሚመጣውን የመከላከያ ኃይል ከኋላ እንሰፍርበታለን” ያሉት የፋኖ ሰራዊት መሪ ብ.ጄኔራል ተፈራ ማሞ በድርጅትም ይሁን በግል የተናገሩት ነገር የለም።

የዓለም አቀፍ የትግራይ ምሁራን እና ባለሙያዎች ማህበር (GSTS) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በትግራይና በኢትዮጵያ ለነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት መቆም መሠረት ቢሆንም፣ አሁን ላይ ስምምነቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች እየታዩ መሆኑን አመልክቷል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ወይንም በማስፈራራት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ክልሉን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ እና ግጭት ይከታል፣ የትግራይ ሠራዊትና የጸጥታ ኃይሎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ሥልጣን ለመያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴን በጥብቅ የሚኮነን ነው በማለት የአውሮፓ ህብረት እና የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ ያሳዩትን አቋም በማድነቅ፤ አሜሪካ እና የአፍሪካ ህብረትም ተመሳሳይ ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

የባለሙያዎቹ ማህበር “ልዩነቶች በውይይትና በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ብቻ መፈታት አለባቸው” በማለት አቋሙን ገልጾ

GSTS ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ “የመላው ትግራይ ጉባኤ” (All-Tigray Conference) ለመጥራት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ከመግለጫው ጋር አያይዞ ማስታወቁ አይዘነጋም።

የፕሬዚዳንት ኢሳያስን መመሪያ ለማስፈጸም ነብስ ያዳነውን የፕሪቶሪያውን ስምምነት አስቀድሞ ማፍረሱን ያስታወቀውና መፈንቅለ መንግስት ያካሄደው ህወሃት ኤርትራ ትዋጋለታለች ወይስ ድንበሯን አጥራ ትቀመጣለች የሚለው ወደፊት የሚታይ ቢሆንም በርካቶች ግን ወይዘሮ ኬሪያ “ስካር ላይ ነበርኩ። ህወሃት ስለነበርኩ ሃፍረት ይሰማናል” እንዳሉት የህወሃት አመራሮች ስካር ላይ እንደሆኑ ይናገራሉ። አሁንም ባለመርፈዱ ችግራቸውን ክረምት ሳይገባ በውይይት እንዲፈቱ መክረዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአመጽ አደራጅ ግብርኃይል በአብይ አህመድ ጉዳይ ተለያየ፤ “ግምት ውስጥ ገብተናል፤ ሚዛን እንጠብቅ”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - “በምንም ይሁን በምን ምርጫ መደረግ...

በረከት ገበሬዋን ጨምሮ ከነዳጅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የተያዙ ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ ሪፖርተር - የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል...

ህወሃት የተለያዩ የስምሪት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጀመረ ፤ ሰራዊቱን ወደ ሱዳንም እየላከ ነው

አዲስ ሪፖርተር ዜና - የህወሃት አመራሮች በዛሬው ዕለት...