አገራዊ ምክክሩን ለማሰናከል ስምሪት ተሰጠ፤ ኮሚሽኑ በአንድም አጀንዳ የመወሰን ስልጣን እንደሌለው አስታወቀ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – አገራዊ ምክክሩ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት በአገሪቱ ለረዥም ዓመታት ለግጭት መነሻ ሆነው አሁን ድረስ የቆዩ የማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በመምከር ዘላቂ እልባት ለማበጀት እንደሆነ በተደጋጋሚ የተገለጸ ጉዳይ ነው። “ስምምነት ቢኖር ኖሮ ምክክሩ አያስፈልግም” የሚሉ ወገኖች “ክርክር ተነሳ” በሚል የሚወጡ ዜናዎች እንደሚያስገርሟቸው ይገልጻሉ። አክለውም ዜና ሊሆን የሚችለው አለምግባባት ሳይሆን “መግባባት ላይ ተደረሱ” ሲባል እንደሆነ ይናገራሉ።

በአሜሪካ ህዝባዊ እንቢተኛነትን እንዳእራጃለን የሚሉት ስብሰቦች ባለፈው እሁድ “ብልጽግና አዲስ አበባን ለኦሮሚያ እንድጸጥ፣ ድሬደዋ እና ጅግጅጋ ላይ ልዩ ዕቅድ ለማስወሰን ተዘግጅቷል፤ ተሰብሳቢዎች ባለመስማማት ስብሰባረግጠው ወጡ…” የሚሉትን ወሬዎች በማጉላት ኮሚሽኑ እየሰራ ያለውን ስራ ለማጣጣል ሚዲያና ተናጋሪዎች መመደባቸውን አዲስ ሪፖርተር ለአባላት ከተሰራጭ የምደባ ዶክመንት አረጋግጣለች።

ምደባው ሲከናውን ባለፈው ሳምንት በተደረገ ስብሰባ ጃዋር በዚህ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ላይ እንደማይሳተፍ አቶ ነዓምን ሲናገሩ አቶ ጅሬኛ ምን “ምን አገባህ” በማለት ጽብ አንስተው ስብሰባው መበተኑን መዘገባችን አይዘነጋም።

በተቋቋመ እለት፣ “እናፈርሰዋለን አሉ” በማለት አፍራሽ ዜና የተሰራበት ኮሚሽን ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ድርጅቶች፣ እንዲሁም በህዝብ መካከል ይሁንታ ባላገኙ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ያሰባሰባቸው አጀንዳዎች “ጥያቄዎቻችን በሙሉ በብልጽግና ተወስደዋል” በሚል በዚሁ ስብሰባ ላይ ተነስቶ እንደነበርም ይታወሳል።

“የሀገራዊ ምክክሩ ምንም ዓይነት ውሳኔ አላስተላለፈም” በማለት የኢትዮዺያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ፣ እንዳረጋግጠው ከሆነ አንድም ውሳኔ በኮሚሽኑ አይወሰንም።

“በአንድም አጀንዳ ላይ የተላለፈ ውሳኔ የለም” ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሲናገሩ፣ ኮሚሽኑ ውሳኔ የማሳለፍ ሥልጣን የሌለው ሲሆን፣ ከምክክሩ የሚገኙ የጋራ ምክረ ሀሳቦችን ለሕግ አውጪው፣ ለሕግ አስፈጻሚው እና ለሕግ ተርጓሚው አካላት ማቅረብ ዋነኛ ተግባሩ እንደህነ አመልክተዋል። የተቃዋሚ ሚዲያዎች ኮሚሽኑ ውሳኔ ላይ እንደሚደርስና ውሳኔውም የጸና እንደሚሆን፣ በዚህም የተነሳ አገር ሊተራመስ እንደሚችል ማስረጃ ሳይዙ እየዛቱ ነው።

በሀገራዊ ምክክሩ ላይ “ውሳኔ ተላልፏል ወይም በቅርቡ ውሳኔ ሊተላለፍ ነው” በሚል እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች ከእውነታው የራቁ መሆናቸውን ፕሮፌሰር መስፍን ገልጸው፣ ሕዝቡ ከተሳሳተ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፣ ሀገራዊ ምክክር በአንድ ጀምበር የሚጀመርና የሚጠናቀቅ ሂደት አይደለም። በመሆኑም ስምንቱም አጀንዳዎች በአሁኑ የምክክር ምዕራፍ የግድ ሙሉ እልባት እንደማያገኙ ጠቁመዋል። አንዳንድ ጉዳዮች ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስዱና የቀጣዩን ትውልድ ተሳትፎ ሊጠይቁ እንደሚችሉም አስረድተዋል።

እስካሁን የተካሄደው ውይይት ወደ አንድ ወር የተጠጋ ሲሆን፣ የአሁኑን ምዕራፍ በቀጣዮቹ አንድ ወይም ሁለት ሳምንታት ለማጠናቀቅ መታቀዱን ገልጸዋል። ውይይቱ የሚጠናቀቀውም ከ4 ሺህ ተመካካሪዎች የተሰበሰቡ ሀሳቦችን በማጠናቀርና በማደራጀት ለተግባር አካላት በማቅረብ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ ምክረ ሀሳቦቹን ካቀረበ በኋላም ተግባራዊነታቸውን በቅርበት እንደሚከታተልና ለሕዝቡ ግብረ መልስ የሚሰጥ ሥርዓት እንደሚዘረጋ ዋና ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። በቀጣዮቹ ቀናት የሚካሄዱ ውይይቶችም ወደ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ምክረ ሀሳቦች እንደሚያመሩ ኮሚሽኑ ተስፋ እንዳለው ፕሮፌሰር መስፍን ገልጸዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ መሪነት ወደ አፍሪካ ኃያልነት እየተሸጋገረች ነው፤ ፈርስት ፖስት

አዲስ ሪፖርተር - ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)...

“ኤርትራ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ አረጋግጣለች” ኢንጂነር ግደይ የትህነግ መስራች

አዲስ ሪፖርተር - ኤርትራ ሙሉ በሙሉ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ...