አዲስ ሪፖርተር – የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳር መሪ የሆኑትን ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደን ከስልጣን ለማውረድ “ጽንፈኛ” የሚባለው ትህነግ ታጠቂዎች ቢሯቸውን መክበባቸውን ተገለፀ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የሜያዟቸው ታጣቂዎችም ጽህፈት ቤቱን ወረዋል።
ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደን በሀይል ከስልጣናቸው ለማውረድ “ጽንፈኛ” የሚባሉት የትህነግ ኃይሎች የፕሬዚዳንቱን ቢሮ እንደከበቡት የመቀሌ ነዋሪዎች ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል። ለአስተዳደሩ ቅርብ የሆኑ አነጋገረን የፕሬዚዳንቱ ሰራዊትም ጽህፈት ቤቱን በመውረር ግልበጣውን ማክሸፉን አመልክተዋል። እነዚህ ወገኖች እንዳሉት ለጊዜው በኃይል ታደሰ ወረደን ለማውረድ የተሞከረው ሙከራ ባይሳካም ሙሉ በሙሉ ከሽፍፏል ለማለት ገና ነው።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ ፣ታጣቂዎች ከዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የፕሬዝዳንቱን ቢሮ ከበዋል። ታጣቂዎች ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን መልቀቅ እንዳለባቸው በጩኸት ድምጽ እያሰሙ መሆኑን አመልክተዋል። ለዳግም ጦርነት ሕዝቡ ፊት ያዞረበት ትህነግ በሀይል ስልጣን በመቆናጠጥ የፈለገው በስልጣን ላይ ያሉት አመራር ዳግም ጦርነት እንዲካሄድ ከማይደግፉት አካል በመሆናቸውና ጥምበትግራይ እንዲካሄድ አስቦ ይሕንን ማድረጉን ምንጮች ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።
እስካሁን ድረስ ከከበባ ውጭ ታጣቂዎች ያደረጉት ነገር እንደሌለ የሚሆነውን የሚከታተሉ አመልክተዋል። ስብሰባ የተቀመጡት የሁለቱም ቡድን ሰራዊት አመራሮች ከስምምነት ላይ ካልደረሱ ሁኔታው ውደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ስጋት የገባቸው ጠቁመዋል።
በክልሉ ጊዜያዊ መንግስት በኩል ይህ እስከተጻፈ ድረስ የተባለ ነገር የለም። የፌደራል መንግስትም ጉዳዩን በቅርብ ከመከታተል ውጭ ያለው ነገር የለም። ታደሰ ወረደ አዲስ በተፈጠረው የሻዕቢያና የትህነግ አዲስ ወዳጅነት በሚፈለገው መልኩ የሚመሩት አስተዳደር ድጋፍ ስለማይሰጥ እንዳልተወደዱ ሲዘገብ ሰንብቷል።
“ጽንፈኛ” የሚባለው የትህነግ አንድ ክፋይ ቀደም ሲል የጊዜያዊ አስተዳደሩን መሪ አቶ ጌታቸው ረዳን በኃይል ማስወገዱ አይዘነጋም። ታደሰ ሲሾሙም ራሱ ይኸው ቡድን እንዳቀረባቸው ማስታወቁ አይዘነጋም።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






