በግብጽ የሚመራው ሻዕቢያ ትህነግንና ፋኖን ይዞ ጦርነት ከፈተ፤ የትግራይ ወጣቶች በመሸሽ ራሳቸውን እንዲያድኑ ተመከሩ፤

Date:

በራማና ዛላንበሳ መሳሪያ የጫኑ ካሚዮኖች ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች እየገቡ ነው – ጦርነቱ የግብጽና የሻዕቢያ አጀንዳ ሲሆን፣ ዓላማው ትግራይን የጦርነት አውድማ ማድረግ ነው እንደ አገር ኢትዮጵያን ማተራመስና ከልማት ተግባሯ ማስቆም

አዲስ ሪፖርተር – አክራሪ የትግራይ ታጣቂዎችና የህወሃት አመራሮች ሰሞኑን የጀመሩትን ትንኮሳ በማስቀጠል ወደ ሙሉ ጦርነት መግባት መጀመራቸውን ተሰምቷል። ከትግራይ የአይን እማኞችን በመጠቀስ መረጃውን ያደረሱንና ራሳቸው ያስተዋሉትን ያጋሩን እንዳሉት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሳሪያና ሰራዊት ከኤርትራ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች እየተጓጓዘ ነው።

ከየአቅጣጫው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት ትግራይን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ቡድኑ በአሁኑ ወቅት ያለውን ኃይል በሙሉ ወደ ግጭት ቀጣናዎች በማሰማራት ላይ ይገኛል። ለዚሁ ይመስላል አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ወጣቶች ራሳቸውን ከጦርነት እንዲያቅቡ ዛሬ አመሻሽ ላይ ጥሪ አቅርበዋል።

ግብጽና የሻዕቢያ በቀጥታ ተሳታፊ በሆኑበት በዚህ ጦርነት ሻዕቢያ ከግብጽ የተላከለትን መሳሪያ ገሚሱን ለራሱ አስቀርቶ፣ ከአስር በላይ በሚቆጠሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጭኖ በራማና ዛላምበሳ አቅጣጫ ወደ ትግራይ እየገባ መሆኑን የምስል ማስረጃ በማስደገፍ ከተላኩ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።

“በግጨቱ ዋና አትራፊ ሻዕቢያ ነው። የተመኘው ትግራይን የማድቀቅ ፣ ኢትዮጵያን የማዳከም ቅዠቱን ለማሳካት አጋጣሚውን ይፈልገዋል” ያሉ በግጭቱ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ የትግራይ ሕዝብ ጦርነት በቃኝ ሊል እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው።

የጦርነቱ ዋና ዓላማ ትርምስ መፍጠር እንደሆነ የሚያመልክቱትና በቅርብ ዓመታት በትግራይ የሆነውን የሚያስታውሱ ክፍሎች፣ ጦርነቱ ሲቀጣጠል ዋናው ተጎጂ በግድ የተሰለፈው የትግራይ ታጣቂ ወጣት እንደሆነ አመልክተዋል።

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሳቢያ “ለምን ትግራይና ህዝቧ አልጠፉም?” በሚል ንዴት “ተኮሊፍና” ያለው ሻዕቢያ አሁን ላይ በግብጽ ድጋፍ በትግራይ ምድር ላይ እንዲለኮስ ያደረገው ጦርነት፣ በግንባር ቀደምትነት የትግራይን ማህበረሰብ የሚያደቅ ሲሆን፣ በጥቅሉ ኢትዮጵያዊያን የሚጎዳና የሚያተራምስ እንደሆነ የሚያስረዱ፣ ሁሉም ዜጋ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ይህን አፍራሽ ሴራ ሊያከሽፍ ይገባል ብለዋል።

“ጽንፈኛ” የሚባለው ትህነግ አመራሮቹ ልጆቻቸውን አሜሪካና አውሮፓ አንደላቀው እያኖሩ በትግራይ ላለው ምስኪን ሕዝብ ምንም ደንታ እንደሌላቸው የሚገልጹት የትግራይ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ የትግራይ ወጣቶች “እምቢ” እንዲሉ ደጋግመው ሲያሳስቡ እንደነበር ይታወሳል።

“ስልጣን ላይ ሙጭጭ ብለው ያረጁ፣ ያፈጁ፣ በዘረፋ የተካኑ ወንጀለኞችን በመከተል መሞትም ሆነ ማናቸውንም ዋጋ መክፈል አሳዛኝ ነው” የሚሉት ክፍሎች ልክ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት “ራሳቸው የለኮሱትን እሳት ራሳቸው ይሙቁት”  የሚል ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ አመልክተዋል።  የትግራይ ህዝብ ለውጥና ዕረፍት እንደሚያስፈልገውም አመልክተዋል።

የአዲስ ሪፖርተር መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጦርነቱ ያሳዘናቸው ወገኖች፣ እንዲሁም ጦርነቱን የሚቃወሙ ኃይሎች ለትግራይ ታጣቂዎች ጥሪ ማቅረባቸውን አመልክተዋል።

ከወገን በኩል እንዲተኮስባቸው የሚፈልግ አካል እንደሌለ የገለጹት እነዚሁ ወገኖች፣ ታጣቂዎች በግዴታ ከተሰማሩና የሚገጥማቸውን መጋፈጥ ካልቻሉ፣ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ወደ አገር መከላከያ ፣ ወደ ትግራይ ሰላም ኃይል ወይም ወደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በማምለጥ ራሳቸውን እንዲያተርፉ መክረዋል።

“ከወንጀለኛ ቡድን አመራሮቹ ውጭ ሌላ ጠላት ስለሌለ ያላችሁን ጥይት መተኮስም ካለባችሁ  ወደዚሁ የትርምስ ኃይል አድርጉ” ሲሉ ያሳሰቡት ክፍሎች ከዚህ ውጭ ወደ የተኛውም ወገን መተኮስ አግባብ እንደማይህን መክረዋል።

አቶ ጌታቸው  ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ፣ በተለይ ከሰሞኑ በጠለምት በኩል የተቀሰቀሰው ግጭት የአመራር ብቃት ማነስና ለሥልጣን የመቆያ ስልት መሆኑን አመላክተው በዚሁ ጽንፈኛ ኃይሉ በለኮሰው እሳት ራሱ ሊቃጠለበት እንደሚገባ በማሳሰብ ንጹሃን ራሳቸውን እንዲያቅቡ ጥሪ አቅርበው ነበር።

የትግራይ እናቶችን የወላድ መካን ባደረገው ጦርነት፣ ያስከተለው ውድመትና ሰብአዊ ቀውስ ስያሽር ዳግም፣ ያለምንም ከባድ መሳሪያ ወጣቱን ክላሽ አሸክመው ሊያስፈጁት እንደሆነ አመልክተዋል።

በአሁኑ ሰዓት ትግራይን ለማውደም ዕቅድ የተያዘለት ጦርነት በተለያዩ አቅጣጫዎች ለመጀመር ከኤርትራ እየገባ ስላለው መሳሪያና የሰው ኃይል ዝርዝር መረጃ ይዘን እንቀርባለን። ይህ እስከ ተጻፈ ድረስ ከኢትዮጵያ ወገን የተባለ ነገር የለም።

በተለያዩ መድረኮች የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች የኢትዮጵያን አየር ኃይል የማድረግ አቅምና የመዘመን ምክንያት ሲያስረዱ፣ ጦርነትን ማሳጠር፣ በአንሰተኛ መስዋዕት ድል መጨበጥና የማያዳግም እርምጃ መውሰደ የኢትዮጵያ መከላከያ ውና ዓላማ መሆኑን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...