ኢትዮጵያ “እንነጋገር” ስትል የሰላም አማራጭ ለኤርትራ አቀረበች፤ የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወጡም አሳሰበች

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኢትዮጵያ መንግስት ፍጹም ሰላማዊ በሆኑ አግባቦች ከኤርትራ መንግስት ጋር ለመነጋገርና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመልክቶ “ፍጹም ተቀባይነት የለውም” ሲል ከኤርትራ መንግስት በኩል አስቸኳይ አቋም የሚወሰድባቸውን ጉዳዮች ጠቅሶ ማሳሰቢያ ላከ።

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌድዮን ጢሞቴዎስ ለኤርትራ አቻቸው አቶ ኡስማን ሳላህ መሐመድ የካቲት 7 ቀን 2026 በአድራሻቸው የተጻፈው ደብዳቤ፣ የኤርትራ ኃይሎች ለረዥም ጊዜ የኢትዮጵያን ግዛት መያዝቸው ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ከአመጸኛ ቡድኖች ጋር የጋራ ወታደራዊ ስምሪት በመወሰድ ወረራ መፈጸሙን አመልክቷል። የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በማክበርና እየፈጸመ ካለው ተቀባይነት የሌለው ተግባሩ እንዲታቀብ ጠይቋል።

“የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ለምናቀርበው ህጋዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ የምናገኝ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በባህር ጉዳዮች እና በአሰብ ወደብ በኩል የባህር በር የማግኘት ጉዳይን ጨምሮ በሁሉም የጋራ ጉዳዮች ላይ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ በቅን ልቦና ለመደራደር ዝግጁ ነው” ያለው የጌድዮን ደብዳቤ፣ “ይህንን ደብዳቤ በተላከበት መንፈስ በመረዳት ለህዝቦቻችንና ቀጠናችን፣ ከግጭት እና ከሁከት ይልቅ ሰላምን እና ብልጽግናን እንድትመርጡ የሚገፋፋ የበጎ ፈቃድ መግለጫ አድርገው እንደሚቀበሉት ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ኢትዮጵያ ሰላም እንጂ ጦርነት እንደማትሻ ያስገነዝባል።

ለረጅም ጊዜ የኤርትራ ኃይሎች በጋራ ድንበራችን በኩል ያለውን የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጥረው የቆዩ ሲሆን፣ የኤርትራ መንግስትም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ቀጥተኛ ቁሳዊ ድጋፍና እገዛ ሲያደርግ መቆየቱን ደብዳቤው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያሳስባል።

ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመችውንና እየፈጸመች ያለውን የሉዓላዊነት ጥሰት እንዲታረም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጥሪ ስናቀርብ መቆየቷን ያብራሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያን ተደጋጋሚ ጉትጎታ ተገቢውን ምላሽ እንዳልሰጠች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያን ጥሪ ሰምቶ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በወረራ መልኩ በኤትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከህግ ውጭ የሚፈጸመው ተግባር መባባሱን አመልክተዋል።

“ባለፉት ጥቂት ቀናት የታዩት ክስተቶች የኤርትራ መንግስት የሁኔታውን መባባስ (escalation) እንደመረጠ ያመለክታሉ| የሚለው የጌድዩን ጢሞቴዎስ ደብዳቤ የኤርትራ ወታደሮች የወሯቸውን ስፍራዎችን በማመላከት “…ከዓመፀኛ ቡድኖች ጋር የሚያደርጉት የጋራ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ትንኮሳ ብቻ ሳይሆን ቀጥተኛ የወረራ ድርጊቶች ናቸው።” ሲል ከረዥን ዝምታ በሁዋላ ግልጽ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

“የኤርትራ ወታደሮች በሰሜን ምስራቅ ድንበራችን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው መግባታቸው እና በሰሜን ምዕራብ ድንበራችን ደግሞ ከዓመፀኛ ቡድኖች ጋር የሚያደርጉት የጋራ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ትንኮሳ ብቻ ሳይሆን ቀጥተኛ የወረራ ድርጊቶች ናቸው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው አመልክተዋል። አክለውም መንግስት የደረሰበትን የመጨረሻ ውሳኔ ነግረዋቸዋል።

ኢትዮጵያ ዘልቆ ከዓመጸኛ ቡድኖች ጋር የሚደረገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴና ይንኮሳ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ያመለከተው ደብዳቤው፣ “ይህ ሁኔታ እንዲያበቃ፣ የኤርትራ መንግስት ወታደሮቹን ባፋጣኝ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲያስወጣ እና ከዓመፀኛ ቡድኖች ጋር የሚያደርገውን ማንኛውንም ዓይነት ትብብር እንዲያቆም በይፋ እንጠይቃለን” ሲል አሳስቧል።

በሁለቱ አገራት መካከል ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል የነበረው ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ግጭት እንደሆነ ያመለከቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ “በውይይት እና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይህንን የጥል እና ያለመተማመን አዙሪት መስበር ይቻላል ብለን እናምናለን” ሲሉ ለኤርትራ አቻቸው ፊታቸውን ወደ ጠረጴዛ እንዲያዞሩ ሃሳብ አርበዋል።

ብዙ የጋራ እሴቶች ባሏቸው የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል አዲስ የሰላም እና የብልጽግና ዘመን እንዲሆን በጋራ መከባበር እና ትብብር ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን ለመገንባት ቁርጠኞች ነን” በማለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህንን ደብዳቤ ቅድሚያ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጉዳዮች አስታውሶ፣ አቶ ኡስማን ሳላህ መሐመድ መላኩን አምልክቷል። አክሎም፣   ደብዳቤውን በተላከበት መንፈስ በመረዳት ለህዝቦቻችን እና ለቀጠናችን ከግጭት እና ከሁከት ይልቅ ሰላምን እና ብልጽግና በመምረጥ የበጎ ፈቃድ መግለጫ አድርገው ይቀበሉታል ብለው እንደሚያምኑ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

ከኤርትራ በኩል ይህ እስከተጻፈ ድርሰ ምላሽ አልተሰማም። ይሁን እንጂ የኤርትራ መንግስት የሚመራው የትህነግና የፋኖ እንዲሁም የሱዳን ጥምረት ኃይል ኢትዮጵያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ለማጥቃት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው እየተሰማ በለበት በአሁኑ ሰዐት፣ ወልቃይትን ለመውረር በዋልድባ በኩል የሻዕቢያ ሰራዊት ድጋፍ ያለው ኦፕሬሽን መጀመሩ እየተሰማ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት የሰላምና የእንነጋገር ደብዳቤ መላኩ ጦርነት ቢነሳ ሊያደርስ የሚችለውን ጥፋት ከመቀነስ አኳያ፣ ለወደፊቱ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ጤናማ መሆን ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በርካቶች አስተያየት ሰጥተዋል።

በሌላ ጎኑ የተሰለፉ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን ሰላምን ያስቀደመ ጥሪ የፍርሃት አስመስለው እንደሚያቀርቡት የገለጹ አሉ።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የብሪክስ ሕብረት የዓለምን ግማሽ ያህል የወርቅ ምርት መሸመቱ ተሰማ

የዓለምን የፋይናንስ መልክ የሚቀይረው አዲሱ የብሪክስ መድረክ የዓለምን ግማሽ...

የጠቅላይ ሚኒስትሩ “የትግራይን ሕዝብ አትንኩ” መልዕክት እና የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው “የዕምነት ክህደት” ደብዳቤ ሰበዞች

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት...