ህወሃት የተለያዩ የስምሪት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጀመረ ፤ ሰራዊቱን ወደ ሱዳንም እየላከ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – የህወሃት አመራሮች በዛሬው ዕለት በአክሱም ከተማ አትራኖስ ሆቴል ዝግ ስብሰባ መጀመራቸው ተሰማ። ስብሰባው የተካሄደው የተለያዩ ወታደራዊ ስምሪቶችና የቦታ ለውጦች እየተደረጉ መሆኑ እየተሰማ ባለበት እና የሱዳን መንግስት ኢትዮጵያን እንደሚወጋ ባስጠነቀቀ ማግስት ነው።

በዶክተር ደብረጽዮን ሰብሳቢነት በአክሱም ከተማ አትራኖስ ሆቴል አስቸኳይ ሚስጥራዊ ስብሰባ እያካሄዱ መሆኑን ያመለከቱት የዜናው ምንጮች፣ ተሰብሳቢዎቹ የሚተኙት ኮንሱላር ሆቴል እንደሆነ መረጃ አስደግፈው ተናግረዋል።

አመራሮቹ ማለዳ ለስብሰባ ወደ አትራኖ ሆቴል ከማምራታቸው በፊት፣ ባረፉበት ኮንሱላር ሆቴል በሶስተኛ መወጣጫ ወለል ቁርስ መመገባቸው ከመረጃው ባለቤቶች ለማወቅ ተችሏል። ስብሰባው በሚስጢር እየተካሄደ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የህወሃት ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሱዳንና ወደ ወልቃይት የተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰማሩ መሆናቸው ታውቋል።

ከ22ኛ አርሚ እና  ጄ.ል ሕንፃ ከሚመሯቸው ሜኬናይዝድ ክፍሎች የተውጣጡ ታጣቂዎች በዛሬው ዕለት አርሚ 70 ወዳለበት ወደ ሱዳን ሸረሪና እየተጓዙ መሆናቸው ተመልክቷል። እንቅስቃሴውን ያዩ “መንግስት መስርተን መሬታችንን እናስመልሳለን፣ ፋኖም ከእኛ ጋር ነው” ያሉትን እየሞከሩ እንደሆነ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል። በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የአልቡርሃንን ጦር እያሸነፉና በርካታ ስፍራዎችን እየተቆጣጠሩ መሆኑ በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ የሚታወስ ነው። ሌተናል ጄኔራል አልቡርሃን በአሜሪካ በአሸባሪነት መፈርጃቸውም አይዘነጋም።

ከ60ኛ አርሚ ወደ ምዕራብ ግንባር ለልዩ ተልዕኮ የተላኩ ታጣቂ ሀይሎች ዛሬ ጧት ከዓቢይዓዲ ተነስተው ወደ ሽሬ ከተማ በመጓዝ ላይ እንደሆኑ እና ሽሬ ከተማ ሲደርሱ የምዕራብ ግንባር ተልዕኮ ተቀብለው ወደ ምዕራብ ትግራይ ጠረፋማ አካባቢ እንደሚገቡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ይህ ዜና የተሰማው መንግስት የሱዳንን ክስ ባስተባበለበት፣ ይልቁኑም ህወሃት የላካቸውን ቅጥረኛ ወታደሮች በማስታጠቅ እና ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሱዳን መንግስት እንደሚሰራ በርካታ ማስረጃዎች እንዳሉ ገልጾ ካስጠነቀቀ በኋላ ነው። መንግስት ይህን ሲል ህወሃት በበኩሉ የሱዳንን መንግስት አወድሶ፣ ወታደሮችና ተፈናቃዮች ሱዳን እንደሚገኙ አስታውቆ የኢትዮጵያን መንግስት ከከሰሰና የሱዳን መንግስት አጻፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ከገለጸ በኋላ ነው። አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ጦርነት እንዳይጀመር ሲያሳቡ ለህወሃት አመራሮች “ዓለም ዓቀፍ ቅጣት ይከተላል” ማለታቸው አይዘነጋም።

በይፋ ባይገለጽም በትግራይ ምዕራብ በኩልና በሱዳን በኩል በተመሳሳይ ሰዓት ጥቃት ለመሰነዘር የተያዘውን ዕቅድ ለመመከት “የተከዜ ኃይል” የሚባለው አደረጃጀት፣ ሚሊሻና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የአገር መከላከያ ዝግጁ ሆኖ እነሚጠብቅ ተሰምቷል።

ሰላም እንደሚሻል በርካቶች እየወተወቱ ባሉበት በዚህ ሰዓት አካባቢው ወደ ጦርነት እንዲመለስ የሚያስችሉ ገፊ ጉዳዮች መበራከታቸው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል። አሁንም ጊዜው ገና በመሆኑ አቅሙ ያላቸው በሙሉ ሁሉም ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ ጫና ማድረግ እንደሚገባቸው እየተገለጸ ነው።

ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ጦርነቱ በይፋ ይጀመር አይጀመር ለጊዜው ምንጮቹ ያሉት ነገር የለም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአመጽ አደራጅ ግብርኃይል በአብይ አህመድ ጉዳይ ተለያየ፤ “ግምት ውስጥ ገብተናል፤ ሚዛን እንጠብቅ”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - “በምንም ይሁን በምን ምርጫ መደረግ...

በረከት ገበሬዋን ጨምሮ ከነዳጅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የተያዙ ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ ሪፖርተር - የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል...

ግብጽ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ህወሃት፣ አፋብን፣ ኦነሰ፣ እና ትንንሽ ታጣቂዎች ኢትዮጵያን ሊወጉ ነው

አዲስ ሪፖርተር - ግብፅ፣ ኢሳያስ እና የሱዳኑ ጄኔራል አል...