በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ህንድ፣ እንግሊዝ፣ ብራዚል፣ ስፔይን፣ ዴንማርክ፣ ጃፓን፣ ሳዑዲ በመሪ ደረጃ አልተወከሉም፤ “የሎሌነት መንፈስ”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ናራንድራ ሞዲ የህንድ፣ ካሪ ስታመር የእንግሊዝ፣ ሉላ ዳ ሲልቫ የብራዚል፣ መሪዎች እጅግ በጣም የሚጠብቁ የስብሰባው እንግዶች ነበሩ። ስፔይን፣ ዴንማርክ፣ ጃፓን፣ የሳዑዲ አልጋወራሽ በዳቮርሱ ስብሰባ ካልተገኙ መሪዎች የሚጠቀሱቱ ናቸው። የእነዚህ አገራት ተቃዋሚዎ ድርጅት መሪዎችም ሆኑ ሚዲያዎች መሪዎቹ በስብሰባው ባለመሳተፋቸው ያሉት ነገር የለም፤ ከስብሰባው ጎን ለጎን በወጡ የተሰብሳቢዎች ዝርዝር የተገኙና ያልተገኙ ስማቸው ተጠቅሶ የቀሩበት ምክኛትና የወከሏቸውን ሚኒስትሮች ስም በግልጽ ማየት ይቻላል።

ከላይ እንድተጠቀሰው ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በምክንያት አልተገኙም። የገንዘብ ሚኒስትራቸውን አቶ አሕመድ ሺዴን ልከዋል። የሚገርመው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚህ ስብሰባ አለመሳተፋቸው “የዲፕሎማሲ ክስምና” ተደርጎ መወሰዱ ነው። መቼም የሎሌነት መንፈስ ካልሆነ በስተቀር ምን ሊባል ይችል ይሆን? የሚባል ሲታጣና ሃሰት እያመረቱ ለልመና ትርፍራፊ የሚጥሉት ፊት ከመልከስከስ አባዜ እንደሚመነጭ ከመግለጽ ሌላ ምን ያባላል?

በዓለም የኢኮኖሚ ፎረም የኢትዮጵያ ተሳትፎ  እና እውነታን በዚሁ ከላይ ባሰፈርኩት መነሻ ለማየት ያነሳሳኝም በተለይ ራሱን የ “Fact Checkers” ፊት አውራሪው አድርጎ የሾመው አቶ ኤሊያስ መሰረት የሞነጫጨረው የሽንፈቱ ኑዛዜ ነው።

ኢትዮጵያ በዓለም የኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum) ላይ ያላት ተሳትፎ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውና በየዓመቱ ተሳትፎ የምታደርግበት የአደባባይ ሚስጥር ነው። በተለይም እ.አ.አ በ2019 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዳቮስ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር እና የጀመሩት “የኢኮኖሚ ማሻሻያ” (Homegrown Economic Reform) ለአለም አቀፍ ባለሃብቶች የቀረበበት ትልቅ መድረክ ነበር። ከዚያ በኋላም በነበሩት አመታት፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች—ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን እና የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ—በመድረኩ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ሲያስከብሩና የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ሲያስተዋውቁ ቆይተዋል።

የዚህ ዓመት የልዑካን ቡድን  ተሳትፎ

ሰሞኑን የተካሄደውን የዳቮስ ጉባኤ በተመለከተ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከፍተኛ ልዑካንን በመምራት መሳተፋቸው የዚሁ ቀጣይነት ያለው የዲፕሎማሲ ስራ አካል ነው። ሚኒስትሩ በጉባኤው ወቅት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች እና ከተለያዩ ሀገራት የኢኮኖሚ ዲፕሎማቶች ጋር ያደረጓቸው ውይይቶች፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያካሄደች ላለው የዕዳ ሽግሽግ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸው። ይህ ተሳትፎ ሀገሪቱ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ ተቋርጦ የማይታወቅ ሂደት ነው።

የመረጃ አጣሪዎች ሃላፊነትና ክፍተት

የመረጃ አጣሪዎች (Fact Checkers) ሚና እውነትን ከሃሰት መለየት መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ግን፣  አቶ ኤልያስ መሰረት የራሱን የግል አመለካከት ወይም ፖለቲካዊ ዝንባሌ፣ ትራፊ የሚጥሉለትን ለማስደሰት ያለውን የሎሌነት ቃል ኪዳን ለማክበር፣ በመረጃ ማጣራት ስም መልከስከስ ለማዱ በመሆኑ፣ እንደ አሁኑ ያሉ የመንግስትን ከፍተኛ ተሳትፎ “አላውቅም” በማለት ወይም የተዛባ ትርክት በመፍጠር ለህዝብ ማቅረብ፣ ቀድሞም ቢሆን የሚታወቅበትን የገለልተኝነት ጥያቄ አጉልቶ አሳይቶበታል። መረጃን በአግባቡ ሳያጣሩ ወይም ሆን ብሎ በመደበቅ የሚሰጥ መግለጫ፣ የዜጎችን የመረጃ የማግኘት መብት ከመጣሱም ባለፈ በማህበረሰቡ ዘንድ አላስፈላጊ ጥርጣሬን በ”ጋዜጠኛነት” ካባ እየረጨ ነው።

እውነታን የማረጋገጥ አስፈላጊነት

በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሚደረጉ ተሳትፎዎች በምስል፣ በቪዲዮ እና በይፋዊ መግለጫዎች የሚታወቁ በመሆናቸው፣ እነዚህን እውነታዎች መካድ ወይም ማዛባት የረጅም ጊዜ ተዓማኒነትን ያሳጣል። እውነተኛ መረጃ አጣሪ  በትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዳቮስ መድረክ ያላቸው ተሳትፎ በየዓመቱ የሚዘገብ ሀቅ ሆኖ ሳለ፣ ይህንን እንደሌለ አድርጎ ማቅረብ በሙያው ስነ-ምግባር ላይ ትልቅ ጥቁር ነጥብ ነው። ህዝቡም መረጃን ሲመዝን ከተለያዩ ገለልተኛ ምንጮች የማረጋገጥ ልምዱን ሊያዳብር ይገባል።

ከዚህ ውጭ የገንዘብ ሚኒስትሩን ኢትዮጵያን መወከል ከሌሎች አገር አቻዎቻቸው በመለየት ማንኳሰስ እሳቸውን ላይ ያለ የተንሸዋረረ ወይም የተለመደው የቀነጨረ የአካባቢነት ስሜት በሽታ ከሆነ ገሃድ ማውጣቱ የተሻለ ይሆናል።

እንደ ማስታወሻ

አንተም ሆንክ መሰል ባልደረቦችህ ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የጂ20 ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካይነት የስብሰባው መሪ ተዋኛን እስክትመስል ድረስ ገና ስትወጣ ያላችሁት ምንም ነገር የለም። በብራዚል በተካሄደው ታላቅ የዓለማችን ስብሰባ ኮፕ32ን እንድታዘጋጅ ኢትዮጵያ ስትመረጥና የውጭ ሚዲያዎች በስበር ዜና ሲያቀርቡት ለመሆኑ የት ነበርክ? የዲፕሎማሲ ኩስመና ነበር? ከሃምሳ ሺህ በላይ እንግዳ የሚተራመስበት፣ የኢትዮጵያን የቱሪዝም አብዮት አንድ እርምጃ ከፍ የሚያደርግ፣ የኢትዮጵያ ግሪን ሌጋሲ ውጤት ስለሆነው ስለዚህ ጉባኤ ተንፍሰሃል?

ኢትዮጵያ ከቻይና ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን ግዙፉን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ (World Internet Conference – WIC) በመጪው መስከረም ወር በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች መሆኑ ሲገለጽ ምነው አልተነፈስክም? በለመድከው የማጣሪያ ወንፊትህ ተሰብሮ ነበር?

ይህ ኮንፈረንስ ለኢትዮጵያ በርካታ ጥቅሞችን ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል። የቴክኖሎጂ ሽግግርን ብቻ እንኳን ብንመለከት እንደ Google፣ NVIDIA፣ IBM እና Alibaba ያሉ ከ200 በላይ የዓለም ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት መሳተፋቸው ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዕድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር መረዳት የሚቻለው ከሎሌነት እሳቤ መላቀቅ ሲቻል ብቻ ነው።

ኮንፈረንስ ቱሪዝም በተመለከተ ስብሰባው አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መዳረሻ (Hub) የማድረግ ራዕይን ያሳካል። ከኢንቨስትመንት አንጻር የዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋናዮችና ምሁራን በሚሳተፉበት በዚህ መድረክ አዳዲስ የኢንቨስትመንት በሮች እንደሚከፈቱ ጥርጣሬ ውስጥ ከወደቅህ የግርድናህን ሸማ አውልቅ፣ የዛኔ ይታይሃል።

የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ (WIC) ከ2012 ጀምሮ በየዓመቱ በቻይና ሲካሄድ የቆየው ይህ ታዋቂ ኮንፈረንስ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ውጭ እንዲካሄድ ሲወሰን ኢትዮጵያ መመረጧ የሀኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ተቀባይነትና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያመጣችውን እመርታ የሚያሳይ እንደሆነ በዘርፉ የተካኑ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች መስክረዋል። የሎሌነት መንፈስ ያልተጫናቸው የዕድሉን ጠቃሚነት በማስተዋወቅ ስለ ተግባራዊነቱ እየሰሩ ነው። ገና ብዙ ብዙ ይሆናል።

በየነ ኃይለ ላዑል ከኬፕታዎን

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...