የክምችት ብር መጠን 4 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ደረሰ፤ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር ላይ የተደረገው ጭማሪ ጥያቄ አስነሳ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ቴሌብርና ሌሎች ባንኮች የሚደረጉ ዲጂታል  ዝውውሮች ላይ የታየው ከፍተኛ  የዋጋ ጭማሪ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቅሬታና ተቃውሞ ቀረበበት። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኢ-ተገማችና ተለዋዋጭ የዓለም ሁኔታ ውስጥ ተጨባጭ ውጤት ማስመዘገቡ ተመለከተ።

ይህ የተባለው ቋሚ ኮሚቴው የብሔራዊ ባንክን የ6 ወራት ሪፖርት ሲገመግም ነው። የኤቲኤም  የፖስ (POS) እና የሞባይል ባንኪንግ የአገልግሎት ክፍያዎች በከፍተኛ  ሁኔታ መጨመራቸው “አበረታች” የተባለውን የዲጂታል ጉዞ ጥላ እያጠላበት መሆኑን አንስቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ባንኮቹ “ኪሳራ ደረሰብን” ለሚሉት  ምክንያትም ማብራሪያ እንዲቀርብ አስታውቀዋል። “ለመሆኑ ባንኮች የሚሉት ኪሳራ እውነት ነው? ወይስ ትርፍ ለማጋበስ የሚጠቀሙበት ዘዴ?” ሲሉ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን በጥልቀት እንዲያጠናው እገረመንገዳቸውን ጠቁመዋል።

የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ወርቅነህ ለቀረበው ወቀሳ  ምላሽ ሰጥተዋል፡፡  ለአገልግሎት ክፍያ ጭማሪው ባንኮቹ እንደገለጹላቸው ከጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡-

የሶፍትዌር ወጪ ጣሪያ መንካት፡ ባንኮች ለቴክኖሎጂው የሚከፍሉት የውጭ ምንዛሬና የባለሙያዎች ስልጠና ወጪ “ከፍተኛ” ነው።

የእርስ በርስ ትስስር ጣጣ፡ አንዱ ባንክ ከሌላው ጋር ለመናበብ የሚያወጣው ወጪ ለጭማሪው ምክንያት ሆኗል።

መቆጣጠር አይቻልም፡ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች “ይህንን ያህል ቁረጡ” ብሎ ትዕዛዝ መስጠት እንደማይችልና ይህም “ዓለም አቀፍ አሰራር አይደለም” ሲሉ እጃቸው የታሰረ መሆኑን ገልጸዋል።

ብሔራዊ ባንክ ባንኮቹ ለአገልግሎት የሚቆርጡትን ክፍያ ለተጠቃሚው በግልጽ “እንዲለጥፉ” አቅጣጫ መስጠቱን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የባንኩንና የተጠሪ ተቋማትን ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡበት ወቅት፤ ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ የገንዘብና የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝ ጠባቂ ነው ብለዋል።

በዚህም የዓለም ኢኮኖሚ ባለተረጋጋበት ሁኔታ ውስጥ የዋጋ ግሽበትን አምና ከነበረበት 17 በመቶ አሁን ላይ ወደ 9 ነጥብ 7 በመቶ የነጠላ አሀዝ በማውረድ ስኬታማ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

የመንግሥት የበጀት ጉድለት ከግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ እንዲሸፈን መደረጉና የብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ አጠቃቀም ፖሊሲ ትግበራ ለዋጋ ግሽበቱ ወደ ነጠላ አሀዝ መውረድ አዎንታዊ ሚና መጫወታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ ባንኮች 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ በማሰባሰብ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ33 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማስመዝገባቸውን አስረድተዋል።

በመደበኛውና በትይዩ ገበያ መካከል ያለውን የምንዛሪ ዋጋ ልዩነት ከፍተኛ ደረጃ መጥበቡን የገለጹት ዶክተር ኢዮብ፥ የባንክ ዘርፍ ተቀማጭ ገንዘብ ክምችት 4 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር መድረሱን አስገንዝበዋል።

ይህም የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በኢ-ተገማችና ተለዋዋጭ የዓለም ሁኔታ ውስጥ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን እንደሚያሳይ አብራርተዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በብዙ አመላካቾች ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው፥ የወጪ ንግድ ገቢን ከ3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የባንኮችን የተበላሸ የብድር መጠን ከ5 በመቶ እንዳይበልጥ በተከናወኑ ተግባራት በስድስት ወራት ውስጥ የባንኮችን የተበላሸ ብድር ማስተካከል የሚያስችል አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትርፋማ፣ ጤናማና በቂ የካፒታል አቅም ያላቸው የፋይናንስ ተቋማትን መፍጠር ያስቻሉ ተግባራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውንም አንስተዋል።

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ በበኩላቸው፤ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ በመከተል የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አኃዝ ዝቅ ማድረጉ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውም በፋይናንስ ዘርፍ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮችን መፍትሔ መስጠት ያስቻሉ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ለማሻሻል የተከናወኑ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በቅርቡ የተሳሳተ መረጃ ኢትዮጵያ ላይ ያሰራጩት የሮይተርስ የአዲስ አበባ ሰራተኞች ታገዱ፤ የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ፈቃዳቸው ተነጠቀ

ሮይተርስ በአዲስ አበባ ያሰማራቸው ሶስት ጋዜጠኞቹ የስራ ፈቃዳቸው እንዳልታደሰና...

“በመናበብ አመጽና ረብሻ ለመቀስቀስ ከፓርቲዎች ጋር ተስማምተናል” ጃዋር “በትርምስና በዓመጽ አናምንም” ፓርቲዎች

አዲስ ሪፖርተር - “እኛና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ሁለት ድርጅት...

ትህነግ የአፍሪካ ህብረት ጫና ፈጥሮ እንዲያደራድረው ነጥቦችን አስቀምጦ ደብዳቤ ጻፈ

አዲስ ሪፖርተር - የፕሪቶሪያው ስምምነት በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረገ የአፍሪካ...