አቶ ልደቱ አያሌው የጀመሩት አብሮነት አቀጣጥለዋለሁ ያለውን ተቃውሞ ብልጭታ ሳያይ ወደ መበተኑ እያመራ ነው፤ በላዩ ላይ ከውስጡ ባሉ አመራር ሌላ “አብሮነት” ሊወለድበት ነው። ጃዋር “ጥሪ አይቀብልም” ብሏል። ውስጡ ኦሮሞ ስለሌለ ልደቱ አያሌው “ኦሮሞ አፋልጉኝ” በማለት አደባባይ ወጥተው ጥያቈ አቅርበዋል። አብሮነት እዚህ ጎዳና ላይ ነው
አዲስ ሪፖርተር – “ከአዲስ አበባ ሆነው ነው ያጠቋቸው። በድሮን አዲስ አበባ ተቀምጠው ነው የደበደቧቸው” በማለት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በጠልምት በኩል ሰሞኑን ተሞከሮ ስለነበረው ጥቃትና የመንግስት ምላሽ ማስረዳት ጀመሩ። በመካከሉ “ፋኖ፣ የጃል መሮ ኦነግ፣ ሻዕቢያና ትህነግ አንድ ሆነዋል ተብሏል። አንድ ከሆኑ ትህነግ ዳግም ወረራ ለማድረግ ለምን ሞከረ?” የሚል ጥያቄ ተነሳ። ይህን ጊዜ ፕሮፌሰሩና አቶ ልደቱ በስልክ ተጠቃቅሰው ከውይይቱ ወጡ። በወቅቱ አቶ “ልደቱ የኦሮሞ ያለህ” ማለታቸውና የጃዋር መሰረወር ምላሽ አላገኘም።
እንደተለመደው ባለፈው ዓርብ አቶ ልደቱ አያሌው የሚመሩት አብሮነት ስብሰባውን አካሂዶ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት ከነበረባቸው ሃያ አንድ የቦርድ አባላት የተገኙት ስድስቱ ብቻ ነበሩ። እነሱም ኢንጂነር ሙሉጌታ፣ አቶ አሸናፊ፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል አቶ ልደቱ፣ ዶ/ር ኢሳማኤል፣ እና ራሳቸውን የደቡብ ክልል ተወካይ ያደረጉት ነበሩ።
በስብሰባው ላይ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ተሞክሮ የተፈለገውን ግብ ሳያሳካ በኪሳራ መጠናቀቁ ስለተነገረለት የትህነግ የጠለምት አቅጣጫ ማጥቃት ማብራራት ጀመሩ። እጅግ ትኩረት የሰጡት በድሮን የተፈጸመውን ጥቃት ነበር። የአዲስ ሪፖርተር የዘወትር ተባባሪያችን የስብሰባውን መረጃዎች ጠቅሶ እንዳለው፣ ፕሮፌሰሩ “ከአዲስ አበባ ጨረሷቸው። አዲስ አበባ ሆነው ነው በድሮን ያጠቋቸው” በማለት ስለጉዳቱ ዝርዝር መረጃ ሲሰጡ፣ ከስድስቱ አንዱ በመካከል ገብተው ያልተጠበቀ ጥያቄ አነሱ።
የኦነግ ሰራዊት፣ ፋኖ፣ ሻዕቢያና ትህነግ አንድ ሆነዋል እየተባለ መሆኑን የጠቆሙት ጠያቂው፣ “አንድ ከሆኑ ትህነግ ዳግም ወረራ ለማድረግ ለምን ሞከረ? ለምን ወዚህ ውሳኔ መጣ? ትክክልስ ነው ወይ” ሲሉ ማብራሪያ እንደሚሹ አመለከቱ። ይህን ጊዜ ያተጠበቀ ድራማ ታየ።
ትህነግና ሻዕቢያ በአንድነት መንግስትን እንደሚጥሉ፣ ይህም የሚሆነው በአጭር ጊዜ እንደሆነ በተደጋጋሚ በሚገለጽበት ወቅት እንዲህ ያለው ግጭት የተመረጠበትን አግባብ ለመረዳት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ጠያቂው ሲያቀርቡ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል እዛው ስብሰባው ላይ ከሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው ስልክ ተደወለላቸው። ፕሮፌሰሩ ስልኩን እንደመጎርጎር አድርገው፣ “ስልክ ተደወለለኝ፤ እንደገና ሞክሬ እገባለሁ” ብለው ለጥያቄው መልስ ሳይሰጡ እብስ አሉ። በዛው ሳይመለሱ ቀሩ። ስብሰባው በአምስት ሰዎች ቀትሎ ወዲያ ተቋጨ።
በዚሁ ስብሰባ ላይ ሰብሳቢው አቶ ልደቱ፣ አስቀድመው አንድ አነጋጋሪ ጥያቄ ጠይቀው ነበር። አቶ ልደቱ “ከሃያ አንዱ የአብሮነት ቦርድ ውስጥ አንድ እንኳን ኦሮሞ የለም። እባክህን ኦሮሞዎችን በመመልመል እርዳን” በሚል ፕሮፌሰር ሕዝቅዔልን ተማጽነው ነበር። ሙሉ የስብሰባው መረጃ ያለው የዲሲ ተባባሪያችን እንዳለው፣
በዕለቱ ስብሰባ ነዓምን ዘለቀን መስለው ሲተውኑ የቆዩትና “መጣሁ” ብለው በዛው የጠፉት ሕዝቅዔል “ችግር የለውም እናመጣለን” በሚል ለአቶ ልደቱ ጥያቄ አጭር ምላሽ ከሰጡ በሁዋላ፣ ሌላው ያነሱት ጉዳይ የሚቀርቧቸው ሴናተሮች ጠርተዋቸው ስለገለጹላቸው ጉዳይ ነበር።
“መንግስት በድሮን እየገደለ ነው። ጭቆናውና የኃይል አገዛዙ አይሏል” በሚል እርዳታ እንደሚፈልጉ ለሴናተሮቹ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ፣ “ እንረዳችኋለን፤ በሰላም እንድትወያዩ እናግዛችኋለን። ግን ጣልቃ አንገባም፤ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ነች መፍትሄ የምትፈልገው” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው “አገር አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርብ ቀን አመጽ እናስነሳለን” በማለት አቶ ልደቱ ለጀመሩት አብሮነት ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በስብሰባው ላይ ይህን ይበሉ እንጂ “ይሄ የነፍጠኛ ስብሰብ ይፈርሳል” በማለት በግል የጋምቤል፣ የደቡድና የሶማሌ ወኪል ነን የሚሉት እሳቸው ወዳቋቋሙት አዲስ ጥምረት ለመውሰድ እንደሚሰሩ አዲስ ሪፖርተር መረጃ አላት።
በዚህ መልኩ የተጀመረው ስብሰባ ከላይ በመግቢያው የተጠየቀው ጥያቄ በፈጠረው ጫና መነሻነት ያለ ምንም የተቋጨ አሳብ መቋጨቱ ታውቋል።
በአብሮነት የመጀመሪያ ስብሰባ ከተገኘ በኋላ ደብዛው የጠፋው ጃዋር መሐመድ እንኳን ስብሰባ ሊገኝ ስልክ ማንሳት አቁሟል። በሌለበት የስራ አስፈጻሚ ሆኖ የተሾመው ጃዋር “ስላልተመቸው እንጂ ይመጣል” እየተባለ በተደጋጋሚ ቢጠበቅም ሊገኝ አልቻለም። ከፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በቀር አንድም ኦሮሞ የሌለበት አብሮነት በቅርቡ እንደሚፈርስም እየተነገረ ነው።
በኦሮሞ ጠልነት፣ “የጋላ መንግስትን እናስወግድ” በማለት እንቅስቃሴ ከጀመሩ ቡድኖች ጋር መስራት የጀመረው ጃዋር ከአዲስ አበባ ጀምሮ በመላው ኦሮሚያና በውጭ ከሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጣ ወርዶበታል። እሱ ብቻ ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በአብሮነት ጋባዥነት በስብሰባው የተሳተፉ የኦሮሞ ተወላጆች ሁሉም ክፉኛ ተወግዘዋል። ይህንኑ ተከትሎ ሁሉም እግራቸውን ሲሰበስቡ የቀሩት ጃዋርና ሕዝቅዔል ገቢሳ ብቻ ነበሩ። ሕዝቅዔል በሶማሌ በኩል የኦብነግን የተመናመነ ኃይልና በኬንያ ድንበር የተበተኑ የኦነግ ተዋጊዎችን እንዲያደራጁ በግብጽ ለተሰጣቸው ኃላፊነት ያመች ዘንዳ ብቅ ጥልቅ ቢሉም ጃዋር ግን ከነአካቴው ስብስቡን መለየቱ ታውቋል። ጃዋር እስካሁን ምንም ዓይነት ምክንያት አላቀረበም። ይሁን እንጂ አቶ ልደቱ ሲደውልለት ስልኩ ጭራሹኑ አይመልስም።
ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ታስሮ እንደነበር ይፋ በተደረበት ሪፖርት ሳቢያ ይሁን በደረሰው ማስጠንቀቂያ በግልጽ ባይነገርም አብሮነትን ስለመሰናበቱ የቦርድ አባላቱ አምነዋል። በቅርቡ የኦሮሞ ተወላጆች ያቋቁሙታል በተባለው አዲስ አብሮነት ውስጥ ስለመካተቱም ለጊዜው መረጃ የለም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






