የኢትዮ – አሜሪካ ስትራቴጂካዊ ትብብር እና የቀጠናው አዲስ አሰላለፍ፤ “አሰላለፉ የኢትዮጵያ የጂኦስትራቴጂ ኩስምና ማሳያ ነው”

Date:

የማይሰማ ነገር የለም። ሰሞኑን “ጽምዶ” በሰበር ዜና ኢትዮጵያን ሊያነካካት ጡንቻ ማብቀሉን የሚያነገሩ በዝተዋል። ጽምዶ የተባለው የኃይል አሰላለፍ የምስራቅ አፍሪቃን የኃይል አሰላፍ ቀይሮታል እያሉ ነው። የአፍሪቃን ቀንድን አሰላለፍ ቀይረዋል ተብለው እየተወደሱ ያሉት ዘመነ ካሴ፣ ድብርጽዮን ገብረመድህን፣ ኢሳያስ፣ የሱዳኑ አልቡርሃን ናቸው። በድርጅት ሲጠሩ ሻእቢያ፣ ትህነግ፣ ፋኖ እና ሱዳን መሆናቸው ነው። በሌላ በኩል የተፈጠረውና ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ኩስምና ነው የተባለው ጥምረት የቬኒቩዙዌላ ፕሬዚዳንት ከመኝታ ቤቱ አንጠልጥል የወሰደችው አሜሪካ፣ የገልፍ አገራት በወታደራዊ ክንዷ የበወዘችው እስራኤል፣ ሃያ የአራታተኛው ትውልድ ጀቶች ባንድ ጀንበር እንካቻሁ ያላቸው አረብ ኢምሬት እንዲሁም ለዚህ ሕብረት መንደርደሪያ የሆናቸው ሶማሊ ላንድ ናቸው። ጎበዝ ይህን ጥምረት እያወዳደሩ የኢትዮጵያን ቁመና “አሰላለፉ የኢትዮጵያ የጂኦስትራቴጂ ኩስምና ማሳያ ነው” በማለት ማንጓጠጥ የጤና ይሆን? ሕክምናውስ ከወደየት ነው፣ ደንቆሮ ባያፍር የደንቆሮ ዘመድ ያፍር እንዲሉ ሆኖ እንጂ ብዙ ባልን ነበር። ለሁሉም የቀጣናውን የኃይል አሰላለፍ ተጨባጭ አሁናዊ እውነታ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

አዲስ ሪፖርተር – የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው፣ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ (AFRICOM) አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን እና አምባሳደር ኸርቪን ማሲንጋ በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት በዓል ላይ መገኘታቸው ተራ ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት አይደለም። ይህ ክስተት ዋሽንግተን ለአዲስ አበባ የምትሰጠውን ትኩረት በይፋ ያሳየ አጋጣሚ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና የአፍሪካ ወታደራዊ እዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ያደረጉት ውይይት፣ ወታደራዊ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ መገለፁ የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከፍ የሚያደርገው ነው። የሱዳን ቀውስና የሶማሊያ የፀጥታ ስጋት በቀጠናው ላይ ጥቁር ጥላ በጣሉበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያና አሜሪካ ስምምነት ለምሥራቅ አፍሪካ መረጋጋት ተስፋ የሚሰጥ ነው።

የሁለቱ ሃገራት ታሪካዊ ስትራቴጂክ አጋርነት ዳራ

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ወታደራዊ ስትራቴጅ ግንኙነት የዛሬ ክስተት ሳይሆን፣ በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝና ጽኑ መሠረት ካላቸው ዲፕሎማሲያዊ ትስስሮች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው። የዚህ ትብብር ታሪካዊ መነሻ በ1950ዎቹ መጀመሪያ (እ.ኤ.አ በ1951) የኮርያ ጦርነት ወቅት የተመሰረተው የጋራ ተጋድሎ ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ በንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለሥላሴ ትዕዛዝ በክቡር ዘበኛ ስር የተውጣጣውን “ቃኘው ሻለቃ” ወደ ኮርያ ልካ ከአሜሪካ ጦር ጋር ትከሻ ለትከሻ በመጋጠም ለዓለም ሰላም መስዋዕትነት ከፍላለች። ይህ የጦር ሜዳ ወንድማማችነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚፈጠረው የዘመናት ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ትብብር የመሠረት ድንጋይ ሆኖ አገልግሏል።

በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ይህ ግንኙነት ይበልጥ ጎልቶ የታየው፣ የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግንባታ በሰጠው ያልተገደበ ድጋፍ ነው። በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የአየር ኃይል ፓይለቶች በከፍተኛ ብዛት ወደ አሜሪካ በመጓዝ በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ሰልጥነዋል። አሜሪካ በወቅቱ በቢሾፍቱ (የቀድሞው ደብረ ዘይት) የአየር ኃይል እና በሐረር የጦር አካዳሚ ግንባታ ላይ የነበራት ሚና፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ግዙፍና ዘመናዊ ጦር ያላት ሀገር እንድትሆን አስችሏታል። ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉር የአሜሪካ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ወዳጅ አድርጓት ቆይቷል።

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃና በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በዓለም ላይ የተከሰቱ ፖለቲካዊ ለውጦችም ግንኙነቱን በአዲስ መልክ አጠናክረውታል። በተለይም እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 (9/11) በአሜሪካ የዓለም የንግድ ማዕከል ላይ የደረሰውን አውዳሚ የሽብር ጥቃት ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ለሚካሄደው የፀረ-ሽብር ትግል ግንባር ቀደም አጋር ሆና ብቅ ብላለች። ዋሽንግተን የቀጠናውን ጽንፈኝነት ለመቆጣጠርና ዓለም አቀፍ የፀጥታ ስጋቶችን ለመግታት አዲስ አበባን እንደ ዋነኛ የደህንነት ምሰሶ በመቁጠር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወታደራዊና ደህንነት ድጋፎችን ስታደርግ ቆይታለች።

ኢትዮጵያ በፀረ-ሽብር ትግሉ ውስጥ ያበረከተችው አስተዋፅኦ፣ በተለይም በሶማሊያ የሚገኘውን አል-ሸባብን በመመከትና ቀጠናዊ ስጋቶችን በማስወገድ ረገድ ያሳየችው ቁርጠኝነት በአሜሪካ ዘንድ ትልቅ እውቅናን አትርፎላታል። ይህ የጋራ የጥቅም ትስስር፣ ሁለቱ ሀገራት በጸጥታና መረጃ ልውውጥ ዙሪያ በቅርበት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል። ይህም ግንኙነት ከወቅታዊ ፖለቲካዊ ውጥረት ባለፈ፣ በጋራ ደምና መስዋዕትነት የተገነባ መሆኑን ያሳያል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ልዑካን የቢሾፍቱ ጉብኝት

ይህ ጉብኝት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት ጂኦስትራቴጂካዊ ተፈላጊነት እና ሚና በድጋሚ ያረጋገጠ ነው። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስከበር ኢትዮጵያ ወሳኝ ታሪካዊ አጋር አድርጋ እንደመረጠቻት መረዳት አይከብድም። ኢትየጵያ 130 ሚሊየን ሕዝብ ያላት፣ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫና የቀጠናው የደህንነት መሠረት መሆኗ፣ ኢትዮጵያን በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ውስጥ የማይተካ ሚና እንዲኖራት አድርጓታል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ አመራሮች በቢሾፍቱ መገኘታቸው፣ የትራምፕ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አስቀድሞ ያሳየበት ምልክት ነው እንደሆነ የቀጠናወ ጂኦፓቲካዊ ጉዳይ ተንታኞች ይገልፃሉ። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን ግንኙነት ወደ “ስትራቴጂካዊ የጋራ ጥቅም” እያደገ መሆኑን ያሳያል። አሜሪካ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ የምትፈልገው አስተማማኝ የፀጥታ አጋርነትን እንደሆነ ጉብኝቱ በግልጽ አመልክቷል።

ይህ አጋጣሚ ኢትዮጵያ በዚህ ቅጥ አምባሩ በጠፋበት የዓለም ጂኦፓለቲካ ሉዓላዊነቷ ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ፍላጎቶች ጋር ለማጣጣም ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው። በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ግንኙነት ወደ ጽኑ ወዳጅነት እንዲቀየርና በቀጣናው ለሚታዩ የፀጥታ ስጋቶች በጋራ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱ የጉብኝቱ ትልቁ ስኬት ነው። ይህም ኢትዮጵያ በአካባቢው ያላትን የበላይነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስመሰከረችበት ክስተት ነው።

የአየር ኃይሉ ዘመናዊነት ፋይዳ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት 90 ዓመታት የተጓዘበት መንገድና አሁን ላይ የደረሰበት የዘመነ አቅም፣ አሜሪካ ኢትዮጵያን እንደ ተለዋዋጭ አጋር ሳይሆን እንደ ጽኑ “ስትራቴጂካዊ የደህንነት አጋር” እንድታያት እድል ይፈጥራል። አየር ኃይሉ ያሳየው ዘመናዊነትና ዝግጁነት፣ ኢትዮጵያ የራሷን ሉዓላዊነት የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰላም የማስከበር አቅም እንዳላት በተግባር አሳይቷል። ይህ ደግሞ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ለምታከናውናቸው የፀጥታ ስራዎች ኢትዮጵያን ቁልፍ አጋር እንድታደርግ አድርጓታል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና የAFRICOM አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ያደረጉት ውይይት፣ ወታደራዊ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ የሥራ አጋርነት ለማሳደግ ያለመ ነው። ይህም በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በመረጃ ልውውጥ ዙሪያ የሚደረጉ ስራዎችን ያካትታል። የሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብር ማደግ፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ዘመናዊነት ከማረጋገጡም በላይ የቀጠናውን የኃይል ሚዛን የሚወስን ይሆናል።

በቀይ ባሕር መዳረሻ፣ በሱዳን ቀውስና በሶማሊያ ጉዳይ ዙሪያ ያለው ውጥረት የቀጠናውን የኃይል ሚዛን እየፈተነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥንካሬ ለአሜሪካ ትልቅ ዋስትና ነው። አሜሪካ በቀጠናው ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ጠንካራና አስተማማኝ አየር ኃይል ያለው አጋር ማግኘቷ ስትራቴጂካዊ ብልጫ ይሰጣታል። ይህ ትብብር በተለይም እንደ አልሸባብ ያሉ አሸባሪ ቡድኖችን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል።

ሚኒስትር አይሻ መሀመድ እንዳሉት፣ የሁለቱ ሀገራት የቆየ ግንኙነት አሁን ካለው ተለዋዋጭ የዓለም ፖለቲካ ጋር ተጣጥሞ መሄድ አለበት። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን እኩልነትና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ያከበረው ይህ ስምምነት፣ ኢትዮጵያ በቴክኒክና በስትራቴጂ ረገድ ከአሜሪካ ጋር በቅርበት እንድትሰራ መንገድ ከፍቷል። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያን የጦር ኃይል በአህጉሪቱ ተወዳዳሪና ዘመናዊ እንዲሆን ያደርገዋል።

በአጠቃላይ፣ የአየር ኃይሉ የ90 ዓመት ክብረ በዓል የታሪክ መዘከሪያ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ትብብር መነሻ ሆኗል። ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን እንደገለጹት፣ ጉብኝታቸው በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንደገና ለማየት ዕድል ሰጥቷቸዋል። ይህም የሁለቱን ሀገራት ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና በጋራ የደህንነት ተግዳሮቶች ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ጽኑ መሠረት ጥሏል።

የትብብሩ ቀጠናዊ የጂኦ – ፖለቲካ አንድምታና

ከጂኦ-ፖለቲካ አንጻር ሲታይ፣ የኢትዮጵያና አሜሪካ ወታደራዊ ቁርኝት ማደስ በቀጠናው ያለውን የኃይል ሚዛን በአዲስ መልክ የሚቀርጽ ነው። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ኃይሎች በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር አካባቢ ተጽዕኖ ለመፍጠር በሚሽቀዳደሙበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያደረገችው ስምምነት ትልቅ ፖለቲካዊ ብልጫ ይሰጣታል። ይህ ትብብር ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን የዲፕሎማሲያዊና የፀጥታ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ “አሜሪካን ቀዳሚ ማድረግ” (America First) ፖሊሲ፣ አሜሪካ ጥቅሟን በሚያስከብሩላት ሀገራት ላይ እንድታተኩር ያደርጋታል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በአሸባሪነት ላይ ያላት ጽኑ አቋምና በቀጠናው ሰላም ለማስከበር የምታደርገው ጥረት ከአሜሪካ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። በመሆኑም አሜሪካ ኢትዮጵያን እንደ ዋና አጋር መምረጧ በቀጠናው የሚኖራትን ተፅዕኖ በዘላቂነት ለማስቀጠል ይረዳታል።

የሱዳን ቀውስና የሶማሊያ የፀጥታ ስጋት በቀጠናው ላይ ጥቁር ጥላ በጣሉበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያና አሜሪካ ስምምነት ለምሥራቅ አፍሪካ መረጋጋት ተስፋ የሚሰጥ ነው። ሁለቱ ሀገራት አሸባሪነትን በጋራ ለመዋጋት መወሰናቸው፣ በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ክፍተት ለመሙላት ወሳኝ ነው። ይህም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም አስከባሪነቷ ያላትን ልምድ ከአሜሪካ የቴክኖሎጂ አቅም ጋር በማቀናጀት ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችላታል።

የኢትዮ-አሜሪካ ወታደራዊ ግንኙነት መጠናከር፣ ሌሎች የቀጠናው ሀገራትም ለሰላምና ለፀጥታ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ግፊት ያደርጋል። ኢትዮጵያ ያሳየችው ስትራቴጂካዊ ጥንካሬ፣ አሜሪካ በቀጠናው ለሚኖራት ማንኛውም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ አዲስ አበባን እንደ መነሻ እንድትጠቀም ያደርጋታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነትና የድርድር አቅም ከፍ ያደርገዋል።

በአጠቃላይ ይህ አዲስ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተመልክቷል። ይህም ኢትዮጵያ የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ሳታስከብር ከአሜሪካ ጋር የምታደርገው ግንኙነት እንደማይኖርና ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ እንደሚቀየስ ያሳያል። የጋራ መግለጫውም ለወደፊት ግንኙነት እንደ መመሪያ ሆኖ የሚያገለግልና በምሥራቅ አፍሪካ አዲስ የሰላም ምዕራፍ የሚከፍት ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...