የትግራይ ሰላም ኃይሎች ቁልፍ ቦታ ተቆጣጠሩ፣ በማንኛውም ሰዓት የመቀለ መንገድ ሊቆረጥ ይቻላል

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ራሳቸውን የትግራይ ሰላም ኃይሎች በሚል የሚጠሩትና በሃራ መሬት የሰፈሩት ታጣቂዎች ቁልፍ ቦታ መቆጣጠራቸው ተሰማ። በየትኛውም ሰዓት የመቀለ መሆኒ መንገድ ሊቆረጥ እንደሚችል ተመልክቷል።

አዲስ ሪፖርተር ለታጣቂ ኃይሎቹ ቅርብ ከሆኑ አመራሮች በደረሳት መረጃ መሰረት የሰላም ኃይል ሰራዊት የተቆጣጠሯት ስፍራ ገረብ አጎ ትባላለች። ቦታዋ በወታደራዊ ግምገማ ቁልፍ ስትሆን ከመሆኒ 15 ኪሎሜትር ላይ የምትገኝ ናት።

የትህነግ ኃይሎች ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም የሰላም ኃይሎች ላይ በደቡብ ምስራቅ ዞን ወጅራት ቶንሳ በተባለ አካባቢ አርሚ 44 በማሰለፍ ጥቃት ከፍቶ ነበር። ጥቃቱን ተከትሎ ምላሽ የሰጡት የሰላም ኃይሎች ገረብ አጎ የምትባለውን አነስተኛ ከተማ ለሊቱን ተቆጣጥረው አደሩ።

ከሰላም ኃይሎች የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው የትህነግ ኃይሎች፣ በበነጋታው ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ቦታዋን መልሶ ለመያዝ ኃይል አጠናክረው ተኩስ ከፈቱ። ጥቃታቸው ከአንድ ቀን በፊት እንዳደረጉት በከባድ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ የአርሚ አርባ አራትን ኃይል በማሰለፍ ነበር።

ጥር 22ቀን 2018 ዓ.ም አርሚ አርባ አራትን ጨምሮ ሰፊ ኃይል በማሰለፍ ሙሉ ማጥቃት ያደረገው የትህነግ ጦር ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን የመረጃው ምንጮች አመልክተዋል።

እንደመረጃው በርካታ ቁጥር ያለው የትህነግ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፣  በስድስት ወታደራዊ የጭነት መኪኖች የተጫኑ ቁስለኞች ወደ መቀሌ መወሰዳቸውን ከከተማዋ ነዋሪዎች ለመረዳት ትችሏል። ከሰማ ኃይሉ ወገን አንስተኛ ዋጋ የተከፈለ መሆኑም ተመልክቷል።

የመሆኒ ነዋሪ የሆኑ የተጠቀሰችው ከተማ በሰላም ኃይሎች እጅ መግባቷን ለአዲስ ሪፖርተር የትግራይ ተባባሪ አረጋግጠዋል።

ተባባሪያችን የገረብ አጎ በሰላም ኃይሎች መያዝ ምን ትርጉም እንዳለው ነዋሪነታቸው መቀለ የሆነ የቀድሞ ታጋይ አነጋግሯል። አካባቢውን ጠንቀቀው የሚያውቁት እኚሁ የቀድሞ ታጋይ እንዳሉት ከመሆኒ ወደ መቀለ የሚወስደው መነገድ በማንኛውም ሰዓት ሊቆረጥ እንደሚችል አመልክተዋል።

ከመሆኒ እስከ መቀለ 130 ኪሎ ሜትር አካባቢ መሆኑን ያመለከቱት የቀድሞ ታጋይ፣ አሁን የሰላም ኃይሎች ከያዟት ገረብ አጎ መሆኒ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ብቻ በመሆኑ፣ ይህ ኃይል መሆኒ ከገባ የመቀለ መንገድ ይቆረጣል።

“የመቀለ መሆኒ መንገድ ከተቆረጠ ድፍን ደቡባዊ ዞን ነጻ ወጣ ማለት ነው” ሲሉ የተያዘቸውን ትንሽ ከተማ ስትራቴጂክነት አስረድተዋል። በሳቸው ግምት ይህቺን ቦታ ለማስለቀቅ ትህነግ ዳግም ሃይል አጠናክሮ መሞከሩ አይቀርም።

የቀድሞ ታጋይ ያሉትን በማንሳት ለትግራይ ሰላም ኃይሎች ቅርበት ያላቸውን የመረጃ ምንጮች ያናገረው ተባባሪያችን፣ የሰላም ኃይሎች ስለ ቀጣዩ ዕቅዳቸውም ሆነ ከተማዋን ስለያዙበት ምክንያት ያሉት ምንም መረጃ እንዳልሰጡ አመልክቷል።

የትህነግ ደጋፊ ሚዲያዎች በአፋር አቅጣጫ በሰፈረው የሰላም ኃይሎች ላይ የተጀመረው ጥቃት የጅቡቲን መንገድ ለመቁረጥ የተደረገ እንደሆነና ኦፕሬሽኑ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ ሲገልጹ ነበር። ይህን ሙከራ “ሻዕቢያ የሚመራው ኃይል ወደ ጅቡቲ ኢትዮጵያ የወደብ መስምወር እየገሰገሰ ነው” በማለት በሰበር ዜናም ያሰራጩት ነበሩ።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...