“እኔ የለሁበትም፤ ጄኔራሎቹ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ አይታዘዙም” ሌ.ጄኔራል ታደሰ፤

Date:

አዲስ ሪፖርተር “ትግራይን የጦርነት አውድማ ያደርጋታል” የተባለውን ጦርነት በሁሉም አቅጣጫ ለመጀመር ሩጫው በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር “እኔ የለሁበትም። ጄኔራሎቹ ለጊዚያዊ  ለአስተዳደሩ አይታዘዙም” ሲሉ ለመንግስት ቃላቸውን እንደሰጡ ተሰማ። 

ወደ ሙሉ ጦርነት ለመሸጋገር በቋፍ ላይ ያለው ግጭት ሙሉ በሙሉ እንደሚቃወሙ ገልጸው ለፌደራል መንግስት ያስታወቁት ታደሰ ወረደ፣ ሕዝብ ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚቃወምም ተናግረዋል። 

ስማቸውን ያገለጹ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ለአዲስ ሪፖርተር እንደተናገሩት መንግስት ለሌተናል ታደሰ ወረደ ማብራሪያ የሰጠው መልስ አጭርና ግልጽ እንደሆነ አመልክተዋል። 

መንግስት ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምንም ፋልጎት እንደሌለው የትግራይ ሕዝብ፣ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርህቶች፣ የዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም ራሳቸው አንታዘዝም የሚሉት የጦር አበጋዞች በቂ መረጃ አላቸው ያሉት ባለስልጣኑ ሌተናል ታደሰ ወረደ ማከናወን የሚገባቸው ጉዳዮች ተነግሯቸዋል።

በትግራይ ግጭት እያወጁና በየአቅጣጫው ጦርነት እየከፈቱ ያሉት የሻዕቢያና ግብጽ ተላላኪ ጄኔራሎች አስተዳደሩን እንደማይሰሙና አስተዳደሩ ጦርነቱን እንደማይፈልገው በይፋ ለሕዝብ እንዲያሳውቁ ለታደሰ ወረደ ተነግሯቸዋል። 

በሌላ በኩል መንግስት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ማሳሰቢያ የሰጠበት ጉዳይ ስለተቋረጠው የአየር መንገድ በረራ ነው። አዲስ ሪፖርተር በደረሰው መረጃ አየር መንገድ የተለመደውን በረራ ለመጀመር ታደሰ ወረደ በአደባባይ ዋስትና እንዲሰጡ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። 

“የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ ከሆኑ፣መደበኛ በረራ እንዲጀመር እንደ መንግስት ዋስትና ስጡ” የተባሉት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ይህንኑ ለማድረግ እንደተስማሙ ታውቋል። መረጃውን ያጋሩን እንዳሉት ታደሰ ወረደ በገቡት ቃል መሰረት መንግስታቸው ኃላፊነቱን በአደባባይ ከወሰደ የተቋረጠው በረራ ይጀመራል። 

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በኃይል ከስልጣን በተነሱት አቶ ጌታቸው ረዳ እግር ሲተኩ “ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር የጀመረውን ከሕገ መንግሥቱን እና ከሀገር ሉዐላዊነት፤ ያፈነገጡ ግንኙነቶችን ኃላፊነትን የሚጥልባቸው የቃል ኪዳን ሰነድ በዓለም ዓቀፍ ታዛቢዎችና ዲፕሎአቶች ፊት መፈረማቸው ይታወሳል።

“አደርገዋለሁ” በሚል ፊርማቸውን ያኖሩበት የቃል ኪዳን ሰነድ፤ የቀድሞ ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታትና  መልሶ መቋቋም ሂደቱ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ የማድረግ ኃላፊነትን ያካተተ ነበር። 

መጋቢት 30/2017 ዓ.ም. የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመሪነትን ሥልጣንን ከአቶ ጌታቸው ረዳ የተረከቡት ሌ/ጄነራል ታደሰ፤ በአዲሱ ኃላፊነታቸው የሚያከናውኗቸውን ተግባራት የዘረዘረ ሰነድ ሲፍርሙና፣ ከፊርማው ስነ ስርዓት በሁዋላ በአንደበታቸው ሲናገሩ ለሕዝብ ይፋ ሆኖ እንደነበርም አይዘነጋም። 

“የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም ቃል ኪዳን ሰነድ ” የተባለውና ታደሰ ወረደ በተገባር ያውሉታል የተባለው ሰነድ ሲገመገም በዜሮ የተጣፋ እንደሆነ የትግራይ ክልል ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ቃል በቃል አስታውቀዋል። 

ስምንት ጉዳዮችን ዘርዝሮ ለታደሰ ወረደ ኃላፊነት የሰጠው ይህ ሰነድ የትግራይን ክልል ገጽታ እንደሚያሻሽል ተስፋ የሰጠ ቢሆንም እንደታሰበው ሳይሆን ቀርቷል። 

በትግራይ ሻዕቢያ እንዳሻው እንደሚፈነጭ፣ የውክልና ጦርነት እያቀጣጠለና የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ የተለያዩ ታጣቂዎችን በትግራይ ምድር እያደራጀ ሙሉ ጦርነት ወደ ማቀጣጠሉ ደረጃ የደረሰው በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የስልጣን ዘመን መሆኑ በርካቶችን ተስፋ አስቆርጧል። 

ከሁለት ሳምንት በፊት የትህነግ ስራ አስፈጻሚ፣ የኮርና አርሚ አዛዦች በጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የግል መኖሪያ ቤት ለሁለት ቀናት በዝግ ስብሰባ መቀመጣቸውን አዲስ ሪፖርተር መዘገቧ ይታወሳል። ይህ ስብሰባ ሲካሄድ ዶክተር ደብርጽዮን አሰመራ ነበሩ።

የክልሉ የጸጥታ ኃላፊ ፍስሃ ማንጁስ እንደጠሩት የተነገረለት ይህ ስብሰባ በታደሰ ወረደ መኖሪያ ቤት እየተካሄደ ከመገለጹ ውጭ በቀቅቱ ስለ ስብሰባው አጀንዳና የተደረሰበት ውሳኔ የተባለ ነገር የለም ነበር። 

ትህነግ ከተከፈለ በሁዋላ “የጽንፈኛ ኃይል” የሚባለው ቡድን ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን “አትሰማንም፣የምትወስነው ሳታማክረን ነው፣ለፌደራል መንግስት ትታዘዛለህ፣ ከኤርትራ ጋር የተጀመረውን ጽምዶ አትደግፍም” የሚሉና ተመሳሳይ አቤቱታ እንደሚቀርብባቸው ስለ ስብሰባው መረጃ የሰጡ አመልክተው፣ ከትግራይ የጸጥታ ኃይል ኃላፊነታቸው እንደሚነሱ አመልክተው ነበር። 

ከስብሰባው መጠናቀቅ ሳምምት በሁዋላ ታደሰ ወረደ ክትግራይ የጸጥታ ኃይል ኃላፊነታቸው እንዲነሱና አደረጃጀቱ ሙሉ በሙሉ በአዲስ አመራሮች መቀየሩ ይፋ ሆኗል። ይህ ሹም ሽር ከተደረገ በሁዋላ ከሻዕቢያና ወልቃይትን ለትህነግ አሳልፎ ለመስተት ኦምሃጀር ላይ ከተስማማው የፋኖ ሃይል ጋር በመቀናጀት በተለያዩ አቅጣጫዎች ጦርነት መጀመሩን መረጃዎችን በማጣቀስ የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እያስታወቁ ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...