ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ፤ ዶ.ር ወርቁ ጋቸና አሉበት

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር የሆኑትን ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢነት ሹመትን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ ለኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባልነት የቀረቡ ዘጠኝ ዕጩዎችን ሹመት አፅድቋል። በዚሁ መሰረት

ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት – የቦርዱ ሰብሳቢ (የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር)

ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) – የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

ዶ/ር መቅደስ ዳባ – የጤና ሚኒስትር

እንደገና አበበ (ዶ/ር) – የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ

አቶ ቸሩጌታ ገነነ – የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ

ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) – የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በአዲስ አባልነት ተሾመዋል፡፡

የቀድሞ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ ጃፋር በድሩ (የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር)፣ አቶ የሱፍ ኢብራሂም (የአብን ፓርቲ አመራር) እና አብዱልዋሳ አብዱላሂ ( ዶ/ር) (ከብልጽግና ፓርቲ) አባልነታቸው እንዲቀጥል ተደርጓል።

ምክር ቤቱ ከዚህም ባሻገር አቶ ልዑል ካሳዬ ወልዱ እና አቶ ምትኩ ማዳ ድልነሳው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል። ምክር ቤቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመትንም አፅድቋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related