“የእኛን ኃይል የሚያሸንፍ የለም” ትህነግ የሐራ መሬት ሽምግልና ሲፈርስ ኃላፊዎቹን በስልጣን የሰከሩ፣ የትግራይ ደመኛ ጠላቶች ተላካሊ አላቸው

Date:

❝…የእኛን ወታደር ማሸነፍ የሚችል ኃይል የለም። ይሄንን ስላችሁ እዚህም እዚያም ውጊያ አይኖርም እያልኳችሁ ግን አይደለም። በአጠቃላይ የማድረግ አቅም እና ስትራቴጂካዊ ብቃት ግን እኛን ማቆም የሚችል ሃይል እዚች ሃገር የለም። በመረጥነው ጊዜና ቦታ ኦፕሬሽኖችን እንፈጽማለን። ድልን እየተቀዳጀን የምንፈልገውን ሁሉ እናደርጋለን… ወልቃይት ወይም ሞት ሲሉ ይሰማሉ እስኪ ወልቃይት ወይም ሞት ከማለታቸው በፊት ባህርዳር ወይም ጎንደር ስለመቀመጣቸው እርግጠኛ ይሁኑ…❞

አዲስ ሪፖርተር – የአሜሪካው አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ “ወደ ዘላቂ ሰላም ለማምራት የተሻለው መንገድ ምክንያታዊ እና የሰከኑ ውይይቶች ወሳኝ ብቻ ናቸው” በማለት ከውይይት ውጪ አማራጭ እንደሌላ አመልክተው ባለፈው ሃሙስ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ህጋዊ የማህበራዊ ገጾች ያሰራጩት መልዕክት በትህነግና በትህነግ ቤተሰቦች ዘንዳ ቁጣ ፈጥሯል። “የብልጽግና ኦሮሞ ይመስላሉ። ባሪያ ናቸው” በሚል በገሃድ እንዲሰደቡ አድርጓቸዋል።

በጠለምት በኩል ተከስቶ የነበረው ጦርነት ሲቆም ትህነግ ለአፍሪካ ሕብረት የጻፈውን “የእንደራደር” ጥያቄ መንግስት ውድቅ ማድረጉ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ውጭ የሚቀበለው አንዳችም ጉዳይ እንደሌለ ማሳወቁን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረትና አፍሪካ ህብረት ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው መገለጹን ተከትሎ ማሲንጋ “ ምክንያታዊ ሆኖ መነጋገር ብቻ ነው የሚያዋጣው” ማለታቸው የፈጠረው ብስጭት በደጋፊዎች ቁጣና ስድብ ብቻ ሳይሆን በትህነግ ከፍተኛ አመራሮች ዘንዳም የስነ ልቦና መዛል አስከትሏል።

ከጥር 25 ቀን ጀምሮ እስከ 29 ድረስ ትህነግ ከጦርነት ጋር በተያያዘ በተለያዩ ጉዳዮች ባደረገው ግምግማ የዓለም ማህበረሰብ ዘንግቶናል ማለቱን ከዚሁ ከአምባሳደሩ ንግግር ጋር ያያዙ አሉ። ትህነግ በዚህ ግምገማው መስተካከል አለበት ካላቸው ጉዳዮች መካከል በውጭ ያሉ ደጋፊዎቹ እንደቀድሞው አደባባይ መውጣት እንዳለባቸው ነው።

ሰሞኑን ሻዕቢያ በአፋር በኩል ሐራ መሬት ላይ ያሉት የትግራይ ሰላም ኃይሎች እንዲመቱ ባዘዘው መሰረት በተደረገው ያልተሳካ ጦርነት፣ የሞቱት ተዋጊዎች መርዶ እየተነገረ ባለበት በአሁን ሰዓት ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑን፣ በቋፍ ላይ ሆኖ ፊሽካ እንደሚጠበቅ ዘ ኢኮኖሚስት ዘግቧል።

ሚስጢር የሆኑ ጉዳዮችን ይፋ በማድረግ የሚታወቀው ዘ ኢኮኖሚስት ጦርነቱ መቃረቡን ይፋ ባደረገበት ዘገባው እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት ሰፊ ኃይል ወደ ትግራይ አንቀሳቅሷል።

መንግስት ለአፍሪካ ሕብረት “በውስጥ ጉዳዬ እንዳትገቡ” በማለት ምላሽ ሰጠ ሲል ዘ ኢኮኖሚስት ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ መንግስት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በስተቀር ማናቸውንም ጉዳዮች ለመስማት ፈቃደኛ አይደለም።

ስሜን አትጥቀስ ያሉ የትህነግ ጄኔራል፣ መንግስት ያንቀሳቀሰው የሰው ኃይልና ከባድ መሳሪያ ከፍተኛ መሆኑን በመጠቀስ ጦርነቱ ከተጀመረ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደስር ማስታወቃቸውን ዘገባው ያስረዳል።

ሰሞኑን የአገር መከላከያ በሁለቱም ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን፣ በምስራቅ ጎጃምና በደቡብ ወሎ ከአካባቢ ሚሊሻ፣ ፖሊስ፣ ጸረ ሽምቅ፣ ኮማንዶና የተለመደውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ድምጹን፣ የኢንተርኔት የግንኙነት ምስመር ገድቦ ሰፊ ኦፕሬሽን እያደርገ መሆኑ ታውቋል። የኦፕሬሽኑ ውጤት ለጊዜው አልተገለጸም። አዲስ የተቋቋመው አፋብን ይህንኑ ተቃውሞ ባወጣው መግለጫ የከባድ መሳሪያ በመጠቀም መንግስት ሰፊ ኦፕሬሽን መክፈቱንና በሶስተኛ ወገኖች ያልተረጋገጡ የወነጀል ክሶሽ አእምቷል።

በጠለምት በኩል ተጀምሮ የነበረው ጦርነት “መደረግ ያልነበረበት ነበር” በማለት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ ብሔር የቀድሞ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

ትህነግ ባካሄደውና እስካሁን ባላላቀው ግምገማው የተዋጊዎቻቸው ስነ ልቦና፣ ወኔና፣ ትጥቅ አሳሳቢ እንደሆነ ቢያመልክቱም፣ ያላቸውን አርሚዎች ከሻዕቢያና ፋኖ ኃይሎች ጋር እያዋሃዱ በ፣ማሰለፍ ላይ ናቸው።

አሰላለፉንና ዕቅዱን መንግስት እንደሚያውቅ የሚናገሩ፣ መግለጫና ወሬ የለም እንጂ አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት ከመንግስት ወገን በቂ ዝግጅት እንዳለ እያሳወቁ ነው። መንግስት በቂ ዝግጅት ቢኖረውም፣ ነገሮች በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት እንዲቋጩ አሁን ድረስ ፍላጎት እንዳለው እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።

አርሚ70፣ አርሚ 35 እና የኤርትራ 65ኛ ክፍለ ሰራዊትና 3ኛ ብርጌድ ወደ ሱዳን በማምራት ግንባር ፈጥረዋል። መረጃውን የላኩልን እንዳሉት ከሆነ፣ ሱዳን ለጊዜው ከግብጽ መሳሪያ በማቀባበል ኝባሩን ትደግፋለች። ፋኖ ኤርትራና መቀለ እንዲሁም ሱዳን በስም በሚታወቁ ስፍራዎች ባደረገው ስብሰባ ውሳኔና ስምምነት መሰረት ይህ ከሱዳን ተነስቶ ወልቃይትን ለመያዝ የሚነሳው ኃይል አካል ሆኗል።

ይህ መረጃ ያለው መንግስት የአገር መከላከያ በተጠነቀቅ እንዲቆም መመሪያ የሰጠ ሲሆን፣ እንዲሁም የአካባቢው አሰተዳደር የተከዜ ዘብ፣ ፖልኪስ፣ የቀበሌ ሚሊሻ፣ ሕዝብን በየመንደሩ በተጠንቀቅ ማቆሙን ስማቸውን ያልጠቀሱ የመዋቅር ሰው ለአዲስ ሪፖርተር ነገረዋል።

በዚሁ ከሱዳንና ኤርትራ መገናኛ ድንበር ላይ ህብረት ፈጥረው ጥቃት ለመስንዘር መመሪያ እየጠበቁ ያሉት ኃይሎች አስደንጋጭ መርዶ የሆነባቸው የሱዳን ፈጣን ኃይል በሚገርም ፍጥነት አካባቢውን እየተቆጣጠረ መሆኑ ነው።

ከቀናት በፊት ታማኘ ሚዲያዎች እንዳሉት የጄኔራል ሃምዲ ኃይል ከሱዳን ሕዝብ ነጻ አውጪ እንቅስቃሴ ጋር በመሆን እያሸነፈ ደቡባዊ የብሉ ናይል አቅጣጫዎችን መቆጣጠሩ ምን አልባትም ተቆርጠው ሙሉ በሙሉ ለጥቃት ሊያጋልጣቸው ስለሚችል ኢትዮጵያ ወታደራዊ ጥቅም እንዳገኝችበት ተመልክቷል።

ከሱዳን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የሱዳን ፈጥኖ ደርሻ ኃይሎች የትህነግና የሻዕቢያ ኃይሎች ለሰሜን ሱዳን አግዘው ስለወጓቸው ህብረት ፈጥረው በስፈሩበት አቅጣጫ ሊወጓቸው እንደሚችል ምልክት አለ።

በጠለምት አቅጣጫ አርሚ 15 በእግረኛ ብቻ እየተጠጋ ሲሆን፣ አርሚ 26 እና 11 ድጋፍ እንዲሰጡት ወደዛው ግንባር ቀርበዋል።

በራያ አቅጣጫ አርሚ 24 በአላማጣ ቆቦ አቅጣጫ ስምሪት የወሰደ ሲሆን፣ ፋኖ አጋዥ ሆኖ እንዲዋጋ ምድብ ወጥቶለታል።

በአፋር በኩል አርሚ 43፣44፣33 እና መበተኑ የሚነገርለት አርሚ 50 ምድብ ወስደዋል። በዚህም አቅጣጫ የፋኖ አሃዝ ተደራቢ ሆኖ መከላከያን እንዲወጋ መደብ ወርዶለታል። አጠቃላይ በሁሉም አቅጣጫ የሚደረገውን ውጊያ አስመልክቶ የወጣው የስምሪት መረጃ የደረሰው መንግስት አሁንም በዝምታው ቀጥሎበታል።

የዝምታ ዲፕሎማሲ የሚከተለው መንግስት፣ ከላይ የተዘረዘረው ሻዕቢያ፣ የትህነግ፣ የፋኖ፣ የሱዳንና የግብጽ የተቀናጀ ዘመቻ ድግስ በተጧጧፈበት በዚህ ወቅት፣ ያሰራቸውን ፕሮጀክቶች ከመመረቅ፣ ከጎረቤት አገራትና አሜሪካን ጨምሮ ከታላላቅ የአለማችን አገራት ባለስልጣናት ጋር በቀጠናው ጸጥታ ጉዳይ ሲመከር ከማሳየት በቀር ስለ አራቱ ዝግጅት በይፋ ሲናገር አይሰማም።

አሜሪካ፣ እስራኤል፣ አርብ ኤምትስ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ ወዘተ ጋር በጸጥታ ጉዳይ ታላላቅ ስምምነቶችን እያደረገ ያለው መንግስት “ጦርነት አይጠቅምም። ከተጀመረ ግን ማልቀስ መፍትሄ አይሆንም” የሚል ማስጠንቀቂያ ከማሰራጨት የዘለለ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ባለፈው ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት፣ እነዚህ ግንባር ፈጠሩ የሚባሉትን ኃይሎች የባሪያ፣ የባንዳና እነዚህን በብር የሚገዙት የኢትዮጵያ የምንጊዜም ጠላቶች ጥምረት ኢትዮጵያን አይሸንፍም ማለታቸው አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ዝግጅት ምሶሶስውን ለመንካት ለሚመጣ እንጂ ሌላው የወፍ ድምጽ አይነት ነው ማለታቸው አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታማኝ ምንጮች የአገር መከላከያ በየተኛውም ሰዓት መቀለ ለመግባት ዝግጅቱን እንዳተናቀቀ ጠቁመዋል። ዝርዝሩን እንመለስበታለን፣

አሁን በደረሰን ዜና መሰረት የትህነግ ኃይል ሃራ መሬት ላሉት የትግራይ ሰላም ኃይሎች ሽማግሌ ልከዋል። ከኃይማኖት መሪዎችና ከታዋቂ ግለሰቦች የተውጣጡ አስትራቂዎች ላቀረቡት ጥያቄ በሃራ መሬት ያሉት ወገኖች የሰጡት ምላሽ የተህነግን የሽምግልና ጥያቄ እንደማይቀበሉ ነው።

አፋር ክልል “ሐራ መሬት” የሰፈሩት ታጣቂዎቹ ወደ ትግራይ እንዲመለሱና ሰላም እንዲወርድ የተለኩት ሽማግሌዎች ጥረት ውጤት አልባ መሆኑን ። ትናንት ማሻውን የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ትናንት አመሻሹን ባወጣው መግለጫ TPF ወይም የሰላም ኃይሎች የሚባሉት ክፉኛ ተችቷል።

ቢሮው በመግለጫው፤ መንግሥትና የጸጥታ አካላት ጉዳዩን በሃይማኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት በውይይት ለመፍታት ከግማሽ መንገድ በላይ በመሄድ በተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም፣ በሌላኛው ወገን እምቢተኝነት ሳይሳካ ቀርቷል ብሏል። ያልተሳካበትን ምክንያት ግን አልገለጸም።

“እነዚህ ቡድኖች የትግራይን ደመኛ ጠላቶች ደጀን በማድረግና የውጭ ኃይሎችን ተልዕኮ በመቀበል በትግራይ ላይ አላስፈላጊ የጦርነት ስጋት ደቅነዋል” ሲል ከሷል። ጠላት ያለውን አካል በግልጽ ያላስቀመጠው የትህነግ መግለጫ፣ የሰላም ኃይሎችን የስልታን ጥመኞች፣ በስልጣን የታወቁ፣ ሰራዊቱን ለግል ጥቅማቸው ሰራዊቱን እንደሚጠቀሙ አመልክቷል።

የሰላም ኃይሎች መሪ ወታደራዊ ኃይሉ በሲቪል አስተዳደር ጣልቃ መግባት የለበትም፣ የፖሊስና የጸጥታ ስራ መስራት ነው ያለበት፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን ይገባዋል። በትግራይ ሕዝብ የሚወስንበት ምርጫ ይደረገ፣ ሁሉም ፓርቲዎች በነጻነት በኩል ደረጃ የሚወከሉበት የሽግግር ስርዓት ይዘርጋ የሚል አቋም እንዳላቸው አስቀድመው መናገራቸው የሚታወስ ነው፣

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የብሪክስ ሕብረት የዓለምን ግማሽ ያህል የወርቅ ምርት መሸመቱ ተሰማ

የዓለምን የፋይናንስ መልክ የሚቀይረው አዲሱ የብሪክስ መድረክ የዓለምን ግማሽ...