የሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አዲሱ ወዳጅነት፤ “ለኢትዮጲያ በረከት፣ ለአኤርትራ መርዶ፣ ለተቃዋሚዎች እሬት” 

Date:

ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ደጋፊዎች፣ ሱዳኑ ጄኔራል አልቡርሃን ጎን ቆመው አገራቸውን ለሚከሱ ተቃዋሚዎች፣ ኢትዮጵያን ተንኳሽ በማለት በገሃድ ለሚከሷት፣ ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም በሚል ጥብቅናቸው ለባዕድና ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ለሆነ ወዘተ ሁሉ ዜናው ከባድ መርዶ፣ እጅግ እሬት፣ ነው። አሜሪካ አልቡርሃንን አሸባሪ ብላ ከፈረጀች በኋላ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ የደመራውን አወዳድቅ የሚያመላክቱ ሆነዋል።

አዲስ ሪፖርተር – ዜናው ለአኤርትራው ፈላጭ ቆራጭ መሪ ፐሬዚዳንት ኢሳያስ መርዶ እንደሚሆን ተመልከቷል። በተቃራኒው ለኢትዮጲያ  መልካም አጋጣሚ ነው ተብሏል። 
በመካከለኛው ምስራቅ የተነሳው የጦርነት ማዕበል፣ የአፍሪቃ ቀንድን የኃይል አሰላለፍ እንደተገመተው እየበወዘው ነው። የሰልፍ ለውጡ  ከቀይ ባህር በግፍ ለተገለለችው ኢትዮጲያ ዕድል ይዞ እየመጣ ስለመሆኑ በርካታ ምልከቶች አሉ። 

ኢትዮጲያ ወደ ቀይ በሕር ድርሸ እንዳትል፣ ሳዑዲ፣ ግብጽና ኢራን ጉያ ሰር ተወትፈው ሲያሴሩ ዕድሜያቸውን የገፉት ኢሳያሰን  ጫና ውስጥ የሚከተው ዜና፣ ኢሳያስን መከታ አድርገው ደፋ ቀና ለሚሉት የተቃዋሚ ደርጅቶችና “ከምርጫው በፊት ይህን መንግስት እንብላው” ስብሰቦች የሚያርዳቸው እንደሆነ ተገለጿል።

ለረጅም ጊዜ በቀይ ባህርና በአፍሪካ ቀንድ የበላይነት ፉክክር ውስጥ ገብተው (በተለይም በየመን እና በሱዳን) ተቃራኒ ጎራ ይዘው የቆዩት ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ አሁን ላይ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማደስ መስማማታቸው ይፋ ሆኗል። 

ኤርትራና ኢትዮጲያ ግንኙነታቸው በሻከረበት በአሁኑ ወቅት፣ ሳዑዲና ኢምሬትስ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸው፣ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን አቋም የተለያየ አቋም አንድ ያደርገዋል። ይህ ደግሞ ኤርትራ ቀደም ሲል ቀይ ባህር ለይ ያላትን የዲፕሎማሲ ተሳትፎ ይቀንሰዋል ተብሏል። በዚህም ሳቢያ ታገኝ የነበረው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚቀንስ ከወዲሁ እተገለጸ ነው። 
ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ታሪካዊ ለተባለ መቀራረብ ያበቃቸው ዋነኛው ምክንያት የህልውና ጉዳይ ነው። ከኢራን የሚሰነዘርባቸው ጥቃት የጋራ የደህንነት ስጋት ልዩነታቸውን ለማስወገድ ገፊ ምክንያት እንደሆነ ተንታኞች እየገለፁ ይገኛል። 

በተለይም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በገልፍ ቀጠናው ላይ እየታየ ያለው ወታደራዊ ውጥረትና በሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች፣ ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት “ከባላንጣነት ወደ ወዳጅነት” እንዲሸጋገሩ አስገድዷቸዋል። 

የሳዑዲው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬትሱ ፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ ዛሬ ያደረጉት የስልክ ጥሪ፣ በሁለቱ መሪዎች መካከል ለወራት ተቋርጦ የነበረውን ቀጥተኛ ግንኙነት የሰበረ ታሪካዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። 

ንግግሩ ያተኮረው በኢራንና በወኪሎቿ አማካኝነት እየተፈጸመ ያለውን ወታደራዊ ትንኮሳ በጋራ ለመመከት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ነው። ይህ የከፍተኛ አመራሮች ግንኙነት፣ ቀደም ሲል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ሲደረግ የነበረውን የአጋርነት መግለጫ ወደ ተግባራዊ ወታደራዊና ደህንነት ትብብር እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ቅራኔ በየመን የደቡብ ተገንጣዮች ድጋፍ፣ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነትና በሶማሊያ የወደብ ይዞታ ጉዳዮች ላይ በእጅጉ ሥር ሰዶ የቆየ ነበር። ይሁን እንጂ የኢራን ጥቃት የቀጠናውን ሰላም አደጋ ላይ መጣሉን የተረዱት መሪዎቹ፣ የኢራንን ቀጥተኛንም  “የወክልና ጦርነቶች” (Proxy Wars) በጋራ ለመከላከል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ይህም በየመንና በሱዳን ለሚታየው ቀውስ አዲስ የሰላም ተስፋ ሊፈነጥቅ የሚችል ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት የያዙትን ተቃራኒ አቋም በማለስለስ ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ መንገድ እንደሚከፍቱ አመላካች ሆኗል።

የሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ጽሕፈት ቤት እንደገለጹት፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙና ለተፈጠረው ችግር ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈለግ የቀረበው ጥሪ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱ አገራት ጥምረት በቀጠናው የሚንቀሳቀሱትንና የኢራን ወኪሎች እንደሆኑ  የሚታሰቡትን እንደ ሁቲ፣ አልሸባብ፣ የሱዳን ሙስሊም ወንድማማች ቡድን እና እንደ ሻዕቢያ ያሉ ኃይሎችን በጋራ ለመዋጋት መወሰናቸው ተነግሯል። 

እነዚህ ኃይሎች የቀይ ባሕርን ደህንነት በማናጋትና የንግድ መርከቦችን በማጥቃት የዓለምን ኢኮኖሚ እያወኩ በመሆኑ፣ ሳዑዲና ኤምሬትስ ወታደራዊ አቅማቸውን በማስተባበር የባሕር ላይ ጥበቃቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል። 

ይህም በአፍሪካ ቀንድና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ የሚታየውን የፀጥታ ክፍተት በመሙላት የአሸባሪ ቡድኖችንና የጎረቤት ሀገራትን አፍራሽ ጣልቃ ገብነት ለመግታት ያለመ ነው።

ከወታደራዊ እርምጃው ጎን ለጎን፣ ሁለቱ ሀገራት ለዓለም አቀፉ የነዳጅ ንግድ ወሳኝ ለሆነውና በኢራን ቁጥጥር ስር ለሚገኘው የሃርሙዝ የባህር ውሽመጥ (Strait of Hormuz) አማራጭ የሚሆን የነዳጅ መስመር ለመገንባት ማቀዳቸው ሌላው ስትራቴጂካዊ እንድምታ ነው። 

ይህ እቅድ በቀይ ባሕር በኩል የሚያልፍ አዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በመዘርጋት፣ የገልፍ ሀገራት ነዳጃቸውን ያለ ኢራን ስጋት ለዓለም ገበያ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። ይህ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት የቀይ ባሕር ቀጠናን ወደ ታላቅ የንግድና የኃይል ማዕከልነት የሚቀይረው ሲሆን፣ የኢራንን የጂኦ-ፖለቲካ የበላይነት በእጅጉ የሚገታ ይሆናል። 

ይህም የገልፍ ሀገራት የራሳቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ ከውጭ ኃይሎች ድጋፍ ይልቅ የውስጥ አንድነታቸውን ማጠናከር እንደሚቀድም የተረዱበት ይመስላል። ይህ ስምምነት በተለይም በነዳጅ ገበያና በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ደህንነት ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የዓለም ኃያላን ሀገራትም በትኩረት እየተከታተሉት ይገኛሉ።

የሳዑዲና የኤምሬትስ ዳግም መገናኘት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የፖለቲካ ካርታ እየቀየረው ነው። የኢራን ጫና ሀገራቱን ወደ አንድነት ማምጣቱ፣ በቀጠናው ለረጅም ጊዜ የቆዩ ግጭቶች እንዲረግቡና አዲስ የኢኮኖሚና የደህንነት ጥምረት እንዲፈጠር በር የሚከፍት ነው። ሁለቱ ሀገራት ልዩነታቸውን በውይይት ለመፍታት መወሰናቸው፣ በአፍሪካ ቀንድና በገልፍ አካባቢ ለሚታየው አለመረጋጋትም ቁልፍ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይስማሙበታል።የሳውዲ እና የአቡዳቢ መስማማት ኢትዮጵያን “ከስጋት ቀጠናነት” አውጥቶ “የኢኮኖሚ ኮሪደር” ተጠቃሚ እንደሚያደርጋት ግልፅ ነው። 

ከሱዳን ጦርነት ጀርባ የሁለቱ አገራት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጦርነቱ እንዲቆም የማድረግ አቅም አላቸው። የጦርነቱ መቆም በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ያለውን ስጋት ይቀንሳል።
በሱዳን በኩል ሾልከው በመግባት በኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት የሚፈጥሩ ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት፣ በድንበር አካባቢ የሚስተዋለው ህገ-ወጥ የመሳሪያና የሰዎች ዝውውር እንዲቀንስ ያደርጋል። በተለይም በግብፅና በኤርትራ እየተረዱ፣ ሱዳንን መሸጋገሪያ በማድረግ ሰላም የሚነሱ ታጣቂዎች የሁለቱን አገራት ስምምነትና አሜሪካ በቅርቡ የወሰደችውን አቋም ተከትሎ እንደሚከስም ይጠበቃል። 

ሳዑዲና ኢምሬትስ በአረብ ሊግ ውስጥ ያላቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የእነሱ መግባባት ሊጉ በኢትዮጵያ ላይ የሚይዘው አቋም ሚዛናዊ እንዲሆን ሊረዳ ይችላል። ይህ ደግሞ የህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ከወተሮው የተለየ ኢትዮጵያ ፍትሃዊ ድጋፍ እንድታገኝ ለማድረግ የሚደረገውን የዲፕሎማሲ ጥረት ያግዛል። በበርካታ ምክንያቶች ለአኢትዮጲያ መልካም አጋጣሚ ይዞ የሚመጣው የሁለቱ አገራት አዲስ ግንኙነት ውጤቱ በቅርቡ የሚታይ እንደሚሆን ጉዳዩን የሚከታተሉ እየገለፁ ነው። 

ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኢትዮጵያ ባንኮች ዕጣ ፈንታ “መዋሃድ አለያም መጥፋት” መሆኑን የብሔራዊ ባንክ አዲስ ሪፖርት ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው የፋይናንስ መረጋጋት ሪፖርት...

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ ሪፖርተር - በመንግሥታት ለውጥ ሂደት በዜጎች ላይ የተፈፀሙ...

ኢትዮጵያ ኢራንን ተክታ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ የገበያ ክፍተት ብትጠቀምስ?

አዲስ ሪፓርተር- በፋርስ ባህረ ሰላጤ በአሜሪካና ኢራን መካከል በተጠረው...