” ለአዲሱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ ተርሚናል ግንባታው 35 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፍላጎት አሳይተዋል ” – የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ለአዲሱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተርሚናል ግንባታው 35 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፍላጎት ማሳየታቸውንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 4.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የ6 ወራት የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ ነው። ከአሜሪካ በረራ የሚገኝ ገቢም መቀነሱን አመልክተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው “አየር መንገዱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ14 በመቶ የገቢ እድገት አስመዝግቧል” ያሉ ሲሆን በቢሾፍቱ የሚገነባው ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ (Mega Airport) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ መጀመሩንም ገልጸዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ማለትም እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ 10.64 ሚሊዮን መንገደኞች የተጓጓዙ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ11 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። በጭነት በረራ (Cargo) አማካይነት 451 ሺህ ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው”አየር መንገዱ የአውሮፕላን ቁጥሩን ለማሳደግ ባደረገው ጥረት ሰባት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የአየር መንገዱ አጠቃላይ የአውሮፕላን ብዛት 147 መደረሱን አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አጋር አየር መንገዶች (ASky, Malawi, Zambia…) የሚጠቀሙባቸውን 23 አውሮፕላኖች ጨምሮ፣ የአየር መንገዱ አጠቃላይ የአውሮፕላን ብዛት 170 ደርሷል። በአገር ውስጥ በረራም የአብይ አዲ ኤርፖርት ግንባታ ተጠናቆ በረራ በመጀመሩ፣ አጠቃላይ የአገር ውስጥ መዳረሻዎች ቁጥር 23 ደርሷል።

በቢሾፍቱ የሚገነባው አዲሱ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ የመሬት ማደላደል ስራ ጥር 10 ቀን ተጀምሯል በሚቀጥለው ዓመት ታህሳስ ወር ይጠናቀቃል።

ለተርሚናል ግንባታው 35 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፍላጎት አሳይተዋል። የአየር መንገዱ አዲሱ ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ 84 በመቶ ደርሷል። አራት የአገር ውስጥ ኤርፖርቶች በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ተጠናቀው ለአገልግሎት ይበቃሉ ” ብለዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የክፉ ጊዜ ወዳጅነት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኤምሬትስ ጉብኝት አንድምታዎች  

      የኢትዮጵያን ቀጠናዊ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚከፈለው መስዋዕትነት ታሪካዊ ዋጋ...

ማርኮ ሮቢዮ ከአብይ ጋር መከሩ፤ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በቀይ ባህርና በአፍሪቃ ቀንድ አሰላለፋቸው ይፋ እየሆነ ነው

አዲስ ሪፖርተር - አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የጠብመንጃ ግብግብ...

How Ethiopia Anchors the Horn Against Sudan’s Ongoing War

Civil wars are often explained as the inevitable eruption...