ጃልመሮ በየኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃል አቀባይና አማካሪ አማካይነት የእነ አቶ ልደቱን የአመጽ አስተባባሪ ቡድን ተቀላቀሉ

Date:

ዛሬ የጥምር ስብሰባ ይካሄዳል፤ በስብሰባው ሻዕቢያ ያደራጃቸው ቡድኖች ይሳተፋሉ

አዲስ ሪፖርተር – “ትዕይንተ ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ-ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” በሚል አቶ ልደቱና አቶ ነዓምን በሻዕቢያ ምሪት በመሰረቱት ቡድን ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪ ጃልመሮ በአማካሪያቸው በኩል ጃዋር መሀመድን እንደተኩ አቶ ልደቱ አረጋገጡ።

ይህ ይፋ ይሆነው በትናንትናው ዕለት በተደረገው የቡድኑ ስብሰባ ላይ “አቶ ጃዋር ስብሰባ የማይገኙበት ምክንያት ምንድን ነው?” በሚል ከተሰብሳቢዎች ለቀረበ ጥያቄ አቶ ልደቱ መልስ ሲሰጡ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በስብሰቡ ውስጥ እንዲገባ የተወሰነበትን ውሳኔ ግን ይፋ አላደረጉም። እሳቸው ባያብራሩም ውሳኔው አቶ ነዓምንና ጃዋር በሻዕቢያና በሌሎች የውጭ ኃይሎች ምሪት እያደራጁት ያለው ስብሰብ ውሳኔ መሆኑ ታውቋል። በዚህ ስብሰባ ላይ ግን የጃልመሮ ሰራዊትና ድርጅት በከፍተኛ ደረጃ ተከሷል። “አብረን መቅመጥ አንችልም” በማለት የተቃወሙ ነበሩ።

በስብሰባው የተሳተፉ ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ እንዳስታወቁት፣ አቶ ጃዋርን ተክተው የገቡት አቶ ጅሬኛ በተከታታይ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው በሚል የሚከሰሰውና በቅርቡ አምነስቲ አስደንጋጭ ሪፖርት ያወጣበት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባል ሆነው ሳለ እዚህ ስብሰብ ውስጥ መግባታቸው አነጋግሯል። ጃዋርን መተካታቸው ደግሞ ጃዋር ከጃል መሮ ጋር አብሮ እየሰራ ነው የሚለውን ሃሜት ያጸና ሆኗል ብለዋል።

አቶ ጅሬኛ ጉደታ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (OLA) ቃል አቀባይ እና ከፍተኛ አማካሪ ናቸው። አቶ ጅሬኛ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን ታጣቂዎች በተመለከተ በተለያዩ ወቅቶች ማናቸውንም መግለጫዎችን በመስጠት ይታወቃል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎችን የሚወክሉት አቶ ጅሬኛ የኩምሳ ድሪባ ወይም ጃል መሮ አማካሪ ናቸው። በኢትዮጵያ አመጽ ለማስነሳት በተደራጀው ቡድን ውስጥ አቶ ጃዋርን ወክለው በመግባት ከእነ አቶ ልደቱ ጋር “የሰላማዊ ትግል አመቻች” እንዲሆኑ ተደርጓል።

አቶ ልደቱ በተደጋጋሚ “ሰላማዊ ትግል ብቻ” ቢሉም አሁን አሁን እየወጣባቸው ያለው መረጃ ከሚሉት ጋር የሚቃረን ሆኗል። በቅርቡ “ትዕይንተ ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ-ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” ይፋ ባደረገው የጥምር ቡኖች ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በመናበብ እንዲሰራ፣ ለታጣቂ ኃይሎች የአብረን እንስራ ጥሪ መደረጉን፣ የትጥቅ ትግሉንና ሰላማዊ የሚባለውን አመጽ አብሮ ለማስኬድ ዕቅድ ስለማውጣትና አመጽ ሲካሄድ ታጣቂ ኃይሎች እንዴት አመጹን እንደሚያግዙ ለመምከር የተያዘውን ዕቅድ ይፋ ያደረገው ቃለ ጉባኤ ላይ አቶ ልደቱ ስማቸው ቀዳሚ እንደሆነ ተመልክቷል። አቶ ልደቱ ከአትላንታ ወደ ዋሽንግቶን ዲሲ የተዘዋወሩት በአቶ ነዓምን በኩል የኑሮ ክፍያ እየተደረገላቸው እንደሆነ አብረዋቸው የሚሰሩ ይናገራሉ።

አብዛኛውን ጊዜያቸውን በሲልቨር ስፕሪንግ ከአቶ ያሬድ ጋር በአንድ ካፌ የሚያሳልፉት አቶ ልደቱ እንዴት ወደ ዲሲ ሊመጡ እንደቻሉ ከነገሯቸው ባልደረባቸው የሰሙ እንዳሉት፣ ክፍያ በአቶ ነዓምን በኩል ስለሚፈጸምላቸው ደስተኛ እንዳልሆኑም እያስታወቁ ነው።

በተያያዘ የአብሮነት እና ከስምንት የተለያዩ ማህበራትና ሻዕቢያ እንዳደራጃቸው የሚታወቁ ቡድን መሪዎች ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ለሊት አካባቢ በጋራ እንደሚመክሩ ታውቋል። ስብሰባውን የተጋበዙ እንዳሉት የስብሰባው ዋና ዓላማ በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ለማካሄድ በታሰባው ስብሰባ ላይ እንዴት በጥምረት እንደሚሰራ መመከርና ዕቅድ ማውጣት፣ በአገር ቤት አመጽ የሚነሳበትን አግባብ አስመልክቶ እንዴት በጋራ መስራት እንደሚገባ መምከር ነው። እንደ ታማኝና አቶ አንዳርጋቸው አይነቶች በይፋ ቅስቀሳውን እንዲቀላቀሉ በዚህ ስብሰባ ላይ መመሪያ እንደሚሰጥ አጀንዳውን የሰሙ አመልክተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – በሶምሊ ክልል የጥፋት ኃይሎች ተስፋ መቁረጥ የወለደው የሃሰት ትርክ ዘመቻ ሲፈተሽ

አዲስ ሪፓርተር- በግምት ከወር በፊት በዚህ ድረገጽ ቀጣዩ የተቃዋሚው...

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

አዲስ ሪፖርተር - ኢራን በእስራኤልና በአሜሪካ የተከፈተባትን  ጦርነት ለመመከት...