“ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስ ችግሩን መሻገር የሚቻለው ከምክንያት በላይ ኾኖ በመገኘት ነው” የኢኮኖሚ ምሁር

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው ጦርነት በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ጫናዎችን እያስከተለ ነው። በተለይ ነዳጅን ጨምሮ የብዙ ነገሮች መተላለፊያ የኾነው የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ለነዳጅ እጥረት እና ለዋጋ ንረት እንዲጋለጡ እያደረገ እንደኾነ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር እና ተመራማሪ ሰይድ ሙሐመድ (ዶ.ር) የዓለምአቀፋዊነት አንዱ ተዕፅኖ ዓለም ላይ የሚከሰት ፈተና ለመላው ዓለም መትረፉ ነው ብለዋል። መካከለኛው ምሥራቅ ላይ ያለው አሁናዊ ሁኔታ እና መዘዙም የዚህ ማሳያ መኾኑን ገልጸዋል። የዓለም አሸናፊ እና የበላይ ኾኖ ለመገኘት ነዳጅ፣ ውኃ እና ኮሪደር መሠረታዊ ናቸው የሚሉት መምህሩ አንዳንድ ሀገራት በተፈጥሮ አቀማመጣቸው ስትራቴጅክ ናቸው ብለዋል። ኢራን ያላት ስትራቴጅካዊ አቀማመጥም ለሌሎች ኃያላን ሀገራት እንቅልፍ የሚነሳ ኾኖ በመገኘቱ ለጦርነቱ አንዱ መነሻ ኾኗል ብለዋል። በሆርሙዝ ሰርጥ ምክንያት ኢራን የዓለም የትኩረት ማዕከል እንደኾነችም ገልጸዋል።

ሆርሙዝ የዓለምን 20 በመቶ የንግድ ሥርዓትን ያሳልጣል፤ ከአሜሪካ ልዕለ ኀያልነት ጀርባ የበርካታ ሀገራት ነዳጅ በዶላር የመገበያየት ጉዳይም አለበት ነው የሚሉት።

ይሁንና እነዚህ በጦርነት ውስጥ የገቡ ሀገራት ስምምነት ላይ እስካልደረሱ ድረስ በሌሎች ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ እንቅፋት መኾኑ ተጠባቂ ነው ብለዋል።

ኢንዱስትሪን ለማስፋፋት እና አጠቃላይ ዕድገትን ለማሳለጥ ነዳጅ የማይገባበት የለም የሚሉት መምህሩ በተለይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሌሎች የገልፍ ሀገራት ኢኮኖሚ በሆርሙዝ የመተላለፊያ ሰርጥ ላይ በመኾኑ በሀገራቸው ኢኮኖሚ ላይ ፈተናው እንደሚበረታ ገልጸዋል።

የአውሮፓ እና የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚም መንገጫገጭ ጀምሯል ነው ያሉት። 30 በመቶ የቻይና ነዳጅ የሚመላለሰው በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ እንደኾነም አንስተዋል።

የጃፓን ኢኮኖሚም መሠረቱን የጣለው በዚሁ ቀጣና ላይ ነው ብለዋል። የዓለምን የኢኮኖሚ ሥርዓት ከዶላር ማስወጣት የሚለው የሀገራት ፍላጎትም ለችግሩ መባባስ ድርሻ እንዳለው ነው የተናገሩት።

እንዲህ አይነት ዓለም አቀፍ ጦርነቶች ኢኮኖሚን በመፈተን ረገድ ተዕፅኗቸው ከባድ መኾኑን አንስተዋል። ጅኦግራፊን መሠረት አድርጎ የሚመጣ የኢኮኖሚ ጣጣ ቀላል አይደለምም ብለዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ጦርነት የአፍሪካን ኢኮኖሚ የሚገዳደር ነውም ብለዋል። ዋናዎቹ ተጎጅዎች ደግሞ ከገልፍ ሀገራት ጋር ባለ ግንኙነት ሳቢያ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ተጠቂነታቸው ሊጨምር እንደሚችል አብራርተዋል።

ይህ መኾኑ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ብቻ ሳይኾን በአንድም በሌላም መንገድ ለዋጋ ንረት ምክንያት ይኾናል ብለዋል። እንዲህ አይነት ወቅት የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና አጠቃላይ የፖለቲካ ጫና ስለሚፈጥር ችግሩን ለመቋቋም የመፍትሔ ስልቶች መተግበር አለባቸው ነው ያሉት።

እንዲህ አይነት ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስ ችግሩን መሻገር የሚቻለው ከምክንያት በላይ ኾኖ በመገኘት ነው ብለዋል።

ሰበብ እየፈለጉ ከሁሉም ነገር ላይ ዋጋ መጨመር ተገቢነት የለውም፤ ካለም መቆም አለበት ነው ያሉት። ምክንያት እየፈለጉ ሸቀጦች ላይ ዋጋ የማንጨምር፤ እንደ ማኅበረሰብ መተሳሰብ እና የመፍትሔ ባለቤቶች መኾን ይገባናል ብለዋል።

በእንዲህ አይነት ጊዜ ራስ ወዳድነትን መቆም እንዳለበትም አሳስበዋል። በሀገር ውስጥ ያሉ ምርቶች የትም ስለማይሄዱ አቅርቦት እንዲቀንስ እና እንዲደበቅ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ጫና ስለሚፈጥር መታረም እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

የነዳጅ ጉዳይን በተመለከተ ቁጠባን መልመድ እና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አንዱ መፍትሔ ነው ብለዋል። መደማመጥን መሠረት በማድረግ ችግሩን መሻገር እንደሚገባም አንስተዋል።

በቀውስ ውስጥ ዕድሎችን መፈለግ ላይም መንግሥት ማተኮር እንዳለበት ጠቁመዋል። አሜሪካውያን የቁጠባ ባሕልን ያዳበሩት በ1920ዎቹ እና 30ዎቹ በተከሠተ ችግር ነበርና ዕድልን አሳይቷቸዋል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ያዋጡኛል ከምትላቸው ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነትን መመሥረት አንዱ መንገድ ሊኾን እንደሚችልም የአሚኮ መረጃ ያስረዳል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የዲሲና ሎንዶን ሰላማዊ ሰልፍ ይሳካል?

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለመበጥበጥ የተቋቋመው ጥምር...

የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት ደህንነት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ የወቅቱ ጥያቄ

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ በፍጥነት እየገሰገሰ የመጣውን የዲጂታል ፋይናንስ...

በመጨረሻ ሰዓት ራሳቸውን ከምርጫ ለማግለል ውጭ ካሉ ኃይሎች ጋር ውል ከገቡት መካከል አቋም የቀየሩ መኖራቸው ተሰማ

በመጪው ምርጫ በርካታ ተቃዋሚዎች በፓርላማና በክልል ምክር ቤቶች...