ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ – የገበታ ለትውልድ የምሥራች ፍሬ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ታሪክ፣ ተፈጥሮ እና መዳረሻ ሲጣመሩ የአንድን ሀገር ቱሪዝም ኢንዱስትሪ የተሟላ ያደርጋሉ። ታሪክ ከተፈጥሮ ጋር ተደምሮ ሲገኝ፣ በዚያ ላይ ምቹ መዳረሻ ሲጨመርበት ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ የሚባለው ቱሪዝም የማይነጥፍ የሀብት ምንጭ ይሆናል።

በዓለም ላይ እነዚህን በአንድነት የያዙ ሀገራት ጥቂቶች ናቸው። በተለይም ነባር ታሪክን ከተፈጥሮ ጋር አጣምረው የያዙ የዓለማችን ሀገራት በጣት የሚቆየጠሩ ናቸው። ከነዚህ ሀገራት ደግሞ ጥቂቶቹ ብቻ መዳረሻቸውን በማልማት ከቱሪዝም ተዝቆ የማያልቅ በረከት እያፈሱ ይገኛሉ።

ይህ ዘርፍ ከኢኮኖሚ ትሩፋቱ በላቀ የአንድን ሀገር ገጽታ በበጎ በማሳየት ረገድ ያለው አስተዋፅኦም እግጅ ታላቅ ነው።

ኢትዮጵያ በታሪክም ሆነ በተፈጥሮ እጅግ ከታደሉት ጥቂት የዓለማችን ሀገራት አንዷ ነች። ታሪክን ብናይ በሥልጣኔ የዳበረ የሺህ ዓመታት ሀገረ መንግሥት ያላት ሀገር ነች። ለዚህም ከአክሱም እስከ ጀጎል ያሉት የሥልጣኔ ቅሪቶቿ ቋሚ ምስክሮች ናቸው።

ተፈጥሮን ብንመለከትም ለሁሉም ተስማሚ አየር፣ ሁሉም ዓይነት የአየር ንብረት፣ አስገራሚ መልክዓ ምድሮች እና በሌላ ዓለም የማይገኙ እንስሳት እና አዕዋፋት ጭምር ያላት ሀገር ነች። ከደናክል ጥልቅ ሸለቆ እስከ ከፍተኛው የዳሽን ተራራ፣ ከአርታ አሌ ሀሩር እስከ ጮቄ የውኃ ምንጭ ኢትዮጵያ በውስጧ የያዘቻቸው ታይተው የማይጠገቡ ውድ ሀብቶቿ ናቸው።

13 ወራት የፀሐይ ብርሃን የማይጠፋባት ኢትዮጵያ የተስተካከሉ እና ለትንበያ የማይቸግሩ የተስተካከሉ አራት ዓመታዊ ወቅቶችን ታስተናግዳለች። አየሯ ብቻ ፈውስ የሆነ፣ ሕዝቧ እንግዳ ተቀባይ፣ ምድሯ የበሰለ የሚያበቅል መሆኗ በጥቂት ልፋት ብዙ በረከት የምታፈስባት ያደርጋታል።

ነገር ግን አለመታደል ሆኖ እነዚህ ሀብቶቿ አቧራ ለብሰው በመኖራቸው ከትሩፋታቸው የሚገባትን ሳትቋደስ ቆይታለች። ታሪኳ እና መልክዓ ምድሯ ተጎብኝተው ለብዙዎች የእንጀራ ምንጭ፣ ለገጿ ደግሞ መብራት መሆን ሲገባቸው ሲባክኑ ኖረዋል።

ይህንን ስብራት ለማስተካከል ታዲያ የመደመር መንግሥት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቁርጠኛ አመራር ሰጪነት ወደ ሥራ ገባ።

* ገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ – አቧራን አራግፈው ኢትዮጵያን የገለጡ ፕሮጀክቶች

ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቮች አቧራ የለበሱ የኢትዮጵያን ሀብቶች የገለጡ ምርጥ ፕሮጀክቶች ናቸው።

“በትልቁ ማሰብ፤ ከትንሽ መጀመር” የሚል መርሕን የሚከተሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቧራን ማራገፍ የጀመሩት ከቤተመንግሥት ነው። ከቢሮ የጀመረው ሸገርን የማስዋብ ሥራ ከወዳጅነት አደባባይ እስከ እንጦጦ ዘልቆ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ሙሽራ አድርጓታል።

የኮሪደር ልማትን ያስከተለው ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት አዲስ አበባ በየቀኑ እየፈካች አዲስ ነገር እያስመለከተች ብዙዎችን እጅን በአፍ ማስጫኗን ቀጥላለች።

አንድ ወቅት “ለአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነት አትመጥንም” የተባለችው አዲስ አበባ ዛሬ በርካቶች “መቼ ሄደን ባየናት?” እያስባለች የምታጓጓ አበባ ሆናለች። ከለውጧ ደግሞ የምሥራች ፍሬዋን ከተቋደሰች ውላ አድራለች።

የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል ሆና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ እና የአፍሪካ ኮንፈረንሶችን በብቃት አስታናግዳለች። 32ኛውን የዓለም አየር ንብረት ጉባኤን (COP32) ያለተቀናቃኝ እንድታስተናግድ ዕድል ያስገኘላት ይህ ለውጧ ነው።

በገበታ ለሸገር ስኬታማ የሆነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንሼቲቭ ወደ ገበታ ለሀገር አድጎ በርካታ የተደበቁ የኢትዮጵያ ሀብቶችን ገልጧል።

ኦሞ ወንዝ አጠገብ ከተደበቀው ኮይሻ እስከ ተዘነጋው ጎርጎራ አስደናቂ ውበትን የገለጠው ገበታ ለሀገር ነው። ማንም ካላሰበው የቤኑና መንደር ብዙዎች እስከተማረኩበት ወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትንሽ ላብ ተዝቆ የማያልቅ በረከት የሚታፈስባት ሀገር እንደሆነች ያሳዩ በረከቶቿ ናቸው።

የገበታ ለሀገር ስኬት ደግሞ ገበታ ለትውልድን ወልዷል። ገበታ ለትውልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመደመር ትውልድ መጽሐፋቸው በሚገኘው ገቢ ያስጀመሩት ኢኒሼቲቭ ነው።

“ሀገራችን ከአባቶቻችን የወረስናት ብቻ ሳትሆን ከልጆቻችን የተዋስናትም ጭምር ናት” የሚል ብሂል ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለትውልድ ነገን የሚያሳምሩ ለትውልድ ተስፋ የሚሆኑ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ።

ገበታ ለትውልድ ከአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት እስከ ገረዓልታ ተራሮች፣ ከሶፍ ዑመር እስከ ሐይቅ/ሎጎ ሪዞርት የኢትዮጵያን ድንቅ ውበት አየገለጠ ይገኛል።

እነዚህ በግንባታ ላይ የሚገኙ መዳረሻዎች ሲጠናቀቁ የትውልድን ተስፋ የሚያፈኩ፣ የኢትዮጵያን መፃኢ ጊዜ የሚያሳዩ ይሆናሉ። ይህም “ከልጆቻችን የተዋስናትን ኢትዮጵያን አስውቦ መመለስ ይገባናል” የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን መርሕ የሚያረጋግጥ ይሆናል።

የገበታ ለትውልድ የምስራች ፍሬ – ደንቢ ኢኮ ሎጅ

ገበታ ለትውልድ ዛሬ የመጀመሪያውን መዳረሻውን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ገልጧል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ የተከፈተው የደንቢ ኢኮ ሎጅ በጥምቀት ዋዜማ ከኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ የመጀመሪያው የገበታ ለትውልድ ገጸ በረከት ሆኗል።

በ36.7 ሔክታር ስፋት ላይ ያረፈው ደንቢ ኢኮ ሎጅ አስደናቂ የጥብቅ ደን እና የተፈጥሮ ሃብት ስጦታን በውስጡ የያዘ፤ እኛው ጋር የነበረ ነገር ግን ዓይናችንን ገልጠን ያላየነው ስፍራ ነበር።

በገበታ ለሸገር እና ገበታ ለትውልድ ያላየናቸውን ፀጋዎቻችንን ማሳየት የተጀመረው ጉዞ እነሆ በገበታ ለትውልድም ድንቅ ውበትን በመግለጥ ጀመሯል።

የደንቢ ኢኮ ሎጅ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ትኩረት አድርጋ በሠራችው ሥራ እያስመዘገበችው ያለው ስኬት መገለጫ ነው።

እምቅ ሀብትን ለይቶ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ መዳረሻውን በማልማት የተደበቁ ሃብቶችን መግለጥ ከኢትዮጵያ ብልፅግና መሻቶች መካከል ነው። ዛሬ በገበታ ለትውልድ የመጀመሪያው መዳረሻ በሆነው የደንቢ ኢኮ ሎጅ የታየው ይህ እውነታ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደንቢ ኢኮ ሎጅን የገለጹት፣ “የፀጋ፣ ውበት፣ ምቾት፣ ያልተገደበ ድንቅ ስፍራ” በማለት ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

via fanna

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...