“ሻዕቢያ ገድሎናል፣ አርዶናል፣ወግቶናል ዓለም ዓቀፍ ፍትህ እንፈልጋለን፣ አሁን ግን ጊዜው አይደል፤ቅድሚያ የጋራ ጠላታችንን አብረን እናስወግዳለን” ህወሃት

Date:

“እርግጥ አርደውናል፣ ገለውናል፣ ወግተውናል፣እውነት ነው፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰ ፍትህ እንፈልጋለን። አሁን ግን ጊዜው አይደለም።ጊዜው ሲደርስ የሚታይ ነው” በማለት ምንም እንኳን ከኤርትራ ጋር አሁን አብሮ የመስራት ውል ቢኖርም ጊዜ የሚጠብቅ ቂም እንዳለ አመላክተዋል። ይህ ንግግራቸው በሻዕቢያ ደጋፊዎች ዘንዳ “ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው”

“በሳምንቱ መጨረሻ ወይም ቀደም ብሎ የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ተረት ይሆናል”

አዲስ ሪፖርተር – “ወደ አዲስ አበባ ውሰጂን። ጓደኞቻችን ሄደዋል። አትወጂንም? ካሁን በኋላ የድሮን ድምጽ መስማት አንፈልግም። እንደ ጓደኞቻችን ውሰጂን” ይህ ዲያመንድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተማጽኖ ነው። እናት ተጨንቃ ይህን ያለችው ለአዲስ ሪፖርተር የመቀለ ተባባሪ ተባባሪ ነው።

“አሁን ያለሁት ጃቫ ነው” ይላል ልዑል (ስሙ የተቀየረ) ጃቫ ተዘግቷል፤ በመቀለ ጃቫ ቡና መጠጣት፣ ተቃጥሮ መገናኘት የባህል ያህል ተለምዷል። ከአክሱም ሆቴል ጎን ሁለት አስርት ዓመታት የተተከለው ጃቫ ተዘግቶ ማየት የመቀለን መፋዘዝ የሚተርክ ዋንኛ ማሳያ ነው።

ሰላም በተመሳሳይ ስሟ የተቀየረ የመቀለ ነዋሪ ናት። የከተማዋን ጽጥ ማለት፣ መቆምና መፋዘዝ ስትገልጽ “አሁን ላይ በመቀለ እንቅስቃሴን አይቶ ሰዓት መገመት አይቻልም። የስራ ሰዓት መውጫ የነበረው ግርግር፣ ግፊያ፣ ጎዳና ሞልቶ መፍሰስ ተረስታል።

በትግራይ የሚራወጠው ህወሃት ብቻ ነው። ይሰበሰባል፣ መመሪያ ያወጣል፣ሰራዊት ያደራጃል፣ ስንቅ ሰብስቡ ይላል፣ ወደ ሃወልቲ አዳራሽ ተሰብሳቢ ካድሬ ያጋግዛል፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን “ተረት አደርጋለሁ” በሚል በመረጠው ከተማ የመከረ ኦፕሬሽን ይቀምራል። ከአዲሱ ፍቅረኛው ጋር ይህንኑ ሩጫውን በድል አጠናቆ “ትግራይን ከገባችበት ቀውስ አወጣለሁ” እያለ በማስታወቅ ላይ ይገኛል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ “አታስቡት” በማለት በጩኸትና በግርግር ኃላፊነታቸውን እንደማይለቁ እያስታወቁ እዛው መቀለ ናቸው። ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ በውጭ ሃገራት ከሚኖሩና የአድቮኬሲ ብሎም የዲፕሎማሲ ተግባራትን ከሚያከናውኑ የትግራይ ዲያስፓራ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ቢበዛ በሳምንቱ መጨረሻ ታደሰ ወረደ የሚመሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተረት ይሆናል።

በዚህ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ከመቀለ አዲስ አበባ የአውሮፕላን ቲኬት ሳምንቱን ሙሉ አልቋል። በትግራይ ንግድ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ ተዘገተዋል። የቻሉ ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል። በመቀለ ያለው ድባብ ክፉ ነው። ሕዝቡ በየቤቱ ቁጭ ብሎ የሚሆነውን እየጠበቀ ነው።

በዙም በተደረገው ስብሰባ ዶክተር አዲስ ዓለም ባሌማ ሲሉ እንድተደመጠው አሁን ትግራይ ለገባችበት ቀውስ መፍትሄው በ2012 የመረጠውና በፕሪቶሪያው ስምምንት መሰረት “ህገወጥ ነው” ብሎ ህወሃት ራሱ የተስማማበት ምክር ቤት ነው። “ብዚህ ሳምንት የምናከናውናቸውን ስብሰባዎች ከጨረስን በኋላ ይወገዳል” ያሉት ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ከሳምንቱ ፍጻሜ በኋላ “ተረት” እንደሚሆን ተገልጿል።

በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆች መበታተናቸውን ያስታወቁት አዲስ ዓለም ቤሌማ፣ የአድቮኬሲውንና የፕሮፓጋንዳውን በቀደሞው ትጋት እንዲያከናውኑ አሳስበዋል። ሚዲያዎች በሚፈለገው ደረጃ እየሰሩ እንዳልሆነም አመልክተው፣ እሳቸው “መፍትሄ” ያሉት መንግስት በትግራይ መመለሱ ችግሩን እንደሚቀርፈው አመልክተዋል።

“ህገወጥ” የተባለው የክልሉ መንግስት መመለሱ ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ያመለከቱት ዶክተሩ፣ አሁን ላይ ደሞዝ መክፈል አለመቻሉን አስታውሰው ዲያስፖራው ይህን ክፍተት ሊሞላ እንደሚገባ አስታውቀዋል። በዚሁ የዙም ስብሰባ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመጣል ከተለያዩ ስማቸውን ካልዘረዘሯቸው ቡድኖች ጋር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ኤርትራን አስመልክቶ “እንዴት አብራችሁ “ትሰራላቹህ” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ሻዕቢያም ለራሱ ሲል ነው ፤ እኛም ለራሳችን ስንል ነው።ማለትም የጋራ ጠላት መጥቶብናል። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው እንደሚባለው ከሻዕቢያ ጋር የነበረን ግንኙነት ታክቲካል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በአንድነት ልንዋጋ ወደምንችልበት ደረጃ አድጓል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምላሻቸውን ሲጀመሩ ግን “እርግጥ አርደውናል፣ ገለውናል፣ ወግተውናል፣እውነት ነው፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰ ፍትህ እንፈልጋለን። አሁን ግን ጊዜው አይደለም።ጊዜው ሲደርስ የሚታይ ነው” በማለት ምንም እንኳን ከኤርትራ ጋር አሁን አብሮ የመስራት ውል ቢኖርም ጊዜ የሚጠብቅ ቂም እንዳለ አመላክተዋል። ይህ ንግግራቸው በሻዕቢያ ደጋፊዎች ዘንዳ “ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው” የሚል ሌላ ጥያቄ ጭሯል። ጽምዶ ሲጀመር “ስለጄኖሳይድና ስለተደፈሩ ሴቶች ጉዳይ አናነሳም” የሚል ስምምነት መኖሩ አይዘነጋም።

“መንግስት አሰብን እወስዳለሁ እያለ በመሆኑ እነሱ [ሻዕቢያ] ደስተኛ አይደለም” በማለት የተናገሩት ዶክተር አዲስ ዓለም ያገናኛቸው የጋራ ፍላጎት እንዳለ አስታውቀዋል። በሌላ አነጋገር ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን እንዳታሳካ ድርጅታቸው እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዓለም ፖለቲካ መቀየሩን ያመለከቱት ዶክተር አዲስ ዓለም፣ “ዓለም ላይ ሁሉም ነገር በጉልበት እየሆነ ነው። የሚሰማን የለም። ራሳችንን አጠንክረን ልንታገል የጋብል። ስለዚህ ዲያስፖራው ያግዝ” ብለዋል።

“አዲስ አበባ በመሄድ ዲፕሎማቶችን ማግኘት እንፈልጋለን፣ ዲፕሎማቶችን አግኝተን መወያየት እንሻለን። ግን ስጋት አለብን” ያሉት ዶክተር አዲስ ዓለም፣ ዲያስፖራው በዲፕሎማሲው ረገድ ሊሰራ እንደሚገባው አሳስበዋል። አክለውም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወይም ከዚያ በፊት የሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ መንግስት ታሪክ እንደሚሆን መተማመኛ ሰጥተዋል።

ይህ በእነዲህ እንዳለ ታዛቢዎች ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን እያነሱ ነው። የአርሚ አዛዦች መከፋፈላቸውንና የአቶ ዓለም ገብረዋህድ ቡድን ከታደሰ ወረደ ጋር መሆን ዶክተር አዲስ ዓለም ባሌማ እንዳሉት መፈንቅለ መንግስቱን ቀላል እንደማያደርገው የሚናገሩ በአንድ ወገን የሚመደቡ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ታደሰ ወረደ እንዲነኩባቸው የማይፈልጓቸውን ጉዳዮች አስከብረው በሰላም ሊያስረክቡ እንደሚችሉ እየገመቱ ነው።

ከታደሰ ወረደ ጋር የተሰለፉ ያሏቸውን የአሰራዊት አመራሮች ስም በመጠቀስ የሚናገሩ እንደሚሉት፣ በሀራ መሬት ያለው የትግራይ ሰላም ኃይሎችና ጦርነት የማይፈልጉት ጄኔራሎች እነ ዶክተር ደብረጽዮን ካላቸው ኃይል ጋር ተመጣጣኝ አቅም ስላላቸው፣ ከጀርባም የፌደራል መንግስት ስላለ ለቅዳሜ የተያዘው መፈልቅለ መንግስት በስምምነት ካልተከናወነ በቀር በኃይል የሚታሰብ አይደልም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ከመብረቃዊ ጥቃት” መግለጫ በኋላ የሴኮ ቱሬ የመጨረሻ ሳምንታት፤ “አማራ ስለሆንክ አጋለጥከን” የድምጸ ወያኔ ምስክርነት

አዲስ ሪፖርተር - በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መጽሄትና ጋዜጣ ዝግጅት መሪነት...

ኢስያስ ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከታደሰ ግንቡ እንዳይፈርስ ይሰጋሉ?

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት...