“መንግስት ከአሜሪካ ጋር በሽብር ሊፈርጀን እየመከረ ነው” የአመጽ አመቻች ግብረኃል አባል፤ ዲያስፖራው ስጋት ውስጥ እንዳይገባ ተፈርቷል

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ራሱን በቅሰቀሳ ስራ አድንቆ በተግባር ግን በውድቀት የገመገመው የአመጽ አዘጋጅ ግብረኃይል ሁለት ንዑስ ኮሚቴ አቋቁሞ የስራ ዕቅድ እንዲነድፍ ወስኖ ውጤቱን ለመጠብቅ ስብሰባውን ለሌላ ቀን ያሳለፈው የሰማዊ አመጽ አመቻች ግብረኃይል ውስጥ መንግስት ከአሜሪካ ጋር በሽብርተኛነት ህግና አፈጻጸም ዙሪያ መምከሩን የሰሙ መደናገጣቸው ተሰማ። መረጃውን የሰጡት ወገኖች ዝርዝር ጉዳይ ባያነሱም በኢትዮጵያ ትጥቅ አንሰተው እየተንቀሳቀሱና ሰላማዊ ዜጎችን የሚገሉ፣ መግቢያ መውጪያ የሚከለክሉ፣ እነዚህን ኃይሎች የሚያስታጥቁ፣ የሚያደራጁና የሚያሰለጥኑ ላይ የሽብር አዋጅ ለማወጅ ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ስለመጀመሩ መስማታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ በዋሽንግተን ዲሲ ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (Secretary of State) ማርኮ ሩቢዮ ጋር ባደረጉት ስትራቴጂካዊ ውይይት፣ በደህንነትና ቀጣናዊ መረጋጋት ዙሪያ በርካታ ወሳኝ በተባሉ ነጥቦች ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተከትሎ፣ ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጺዮን “ከማን ጋር እንደምንዋጋ አላወቅንም። የደረሱበት ስምምነት አደገኛ ነው። ባለን መስመር እንከታተለዋለን” በማለት በኢትዮጵያ ከምርጫ በፊት አመጽ ለማስነሳት በተቋቋመው ግብረኃይል ስብሰባ ላይ መናገራቸውን ተሰብሳቢዎችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ተባባሪ የተለመዱ የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው፣ አሁን ላይ በግብረኃይሉ ውስጥ ካሉ አባላት መካከል “በሽብር ወንጀል የሚፈረጁ ድርጅቶች ስለሚኖሩ ስጋት ገብቶናል” በማለት የነገሩት አሉ። እነዚህ ወገኖች እንዳሉት፣ በ”ሰላማዊ ትግል” ስም በተሰባሰበው ግብረኃይል ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) አመራርና ቃል አቀባይ፣ አሜሪካ በሽብርተኝነት ወንጀል ከፈረደቻቸው የሰሜን ሱዳን መሪ አልቡርሃን ጋር የሚሰራውና ጦር አዝምቶ እየተዋጋ ያለው የህወሃት ተወካይ፣ እንዲሁም ለጊዜው በሽብርተኝነት ያልተፈረጁ ታጣቂዎች ወኪሎች የተካተቱበት በመሆኑ ስጋት ገብቷቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የአገሪቱን የጸጥታና የደህንነት መዋቅር ኃላፊዎችን አስከትለው ወደ አሜሪካ መጓዛቸውና ከአሜሪካ የጸጥታና የስለላ ተቋማት ጋር መምከራቸው ከተሰማ በኋላ፣ ኢንጂነር ግደይ እንዳሉት ስጋት ቢኖርም በዚህ ሳምንት በአርሲ የተፈጸመውን “የሽብር ጥቃት” ተከተሎ ስጋቱ ጨምሯል።

ብብሄር ነጻ አውጪ ስም ከዴያስፖራ ከፍተኛ ገቢና ድጋፍ የሚያገኙት እነዚሁ ቡድኖች “መረጃው ዲያስፖራውን ስጋት ላይ እንዳይጥለው ጥንቃኤ ሊወሰድ ይገባል” በማለት ቀደም ሲል ባላቸው መዋቅር መሰረት መመሪያ ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። የዋሽንግቶኑና የሎንዶኑ ሰላማዊ ሰልፍ ከቀረበት ምክንያቶች መካከል አንዱ ይህ ስጋት እንደሆነ የሚገልጹት ወገኖች፣ ከህዝቡ መሰላቸት በተጨማሪ የሽብርተኛነቱ ውይይት መደረጉ በጠላት ሚዲያዎች ቀርቦ ይባሱኑ ደጋፊዎችን ስጋት ላይ እንዳይጥል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ጠቅሰዋል። በቅርቡ የፋኖ ደጋፊ ነው በሚል በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ ከአሜሪካ ወደ አገሩ እንዲላክ የተደረገውን ኢትዮጵያዊ ተከትሎ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሮ እንደነበር በወቅቱ የህግ ባለሙያዎች አነጋግረን መዘገባችን አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ (ቁጥር 1176/2012) ሽብርተኝነትን በሀገር ውስጥ ለመግታት ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ትብብሮችን ለመፍጠርና ተጠርጣሪዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ ሕጋዊ መሠረት እንደሚጥል የሚናገሩት የግብረኃይሉ አባል፤ አዋጁ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራትና ዓለም አቀፍ የሕግ አስከባሪ አካላት (እንደ ኢንተርፖል ያሉ) ጋር መረጃ እንድትለዋወጥ ሥልጣን እንደሚሰጥ ገልጸዋል። በአንድ ወዳጅ ሀገር ውስጥ የሚገኝን ተጠርጣሪ ለመከታተል፣ የባንክ አካውንቱንና የንብረት ምንጩን ለማሳገድ እንዲሁም የሰነድ ማስረጃዎችን ለመለዋወጥ ሕጋዊ ማዕቀፍ ስለሚፈጥር፣ አሁን ያለው እንቅስቃሴ ወደዚያ ሊያመራ እንደሚችል ፍንጭ እንዳለ አመልክተዋል።

የሕግ ባለሙያዎች “አዋጅ ቁጥር 1176/2012 የሽብር ወንጀል ድንበር ተሻጋሪ (Transnational) ባህሪ እንዳለው ስለሚገነዘብ፣ ወንጀለኞች በሌላ ሀገር ተሸሽገው ከሕግ እንዳያመልጡ ከወዳጅ ሀገራት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ለመሥራት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊና ሕጋዊ መሣሪያ ነው” በማለት ተጠያቂ ሊያደርጉ የሚችሉትን ጉዳዮች በማብራራት በአዲስ ሪፖርተር ላይ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። በሽብር ከተፈረጁ ቡድኖች፣ ግለሰቦች አልያም ተቋማት ጋር አብሮ መስራት፣ በገንዘብ መደገፍ፣ ማስተዋወቅ፣ በሚዲያ ድጋፍ ማድረግ ወዘተ በሕግ የሚያስጠይቁ ናቸው ከሚባሉት ጉዳዮች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ በዋሽንግተን ዲሲ ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (Secretary of State) ማርኮ ሩቢዮ ጋር ስትራቴጂካዊ የተባለ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረመውን ባለሁለት ወገን መዋቅራዊ ውይይት (Bilateral Structured Dialogue – BSD) መሠረት በማድረግ በደህንነት ረገድ የተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች የስምምነቱን ከፍተኛ ደረጃ መድረስ የሚያሳዩ እንደሆነ በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል።

በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የጸጥታ ሥጋት ለመቀነስ በተለይም አልሸባብንና ሌሎች የአሸባሪ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት ሁለቱ ሀገራት በጋራና በትብብር ለመሥራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገው ነበር። በአካባቢው እየታዩ ያሉትን የጂኦፖለቲካዊ ሽግግሮችና አለመረጋጋቶች ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ሚና ቀጣናዊ ሰላምን ለማስከበር ከፍተኛ መሆኑ ተነስቷል። አሜሪካም ለአካባቢው መረጋጋት የሚበጁ የደህንነት ትብብሮችን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አሳይታለች። የሀገር ውስጥ የጸጥታና የደህንነት ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚደረጉ ጥረቶች ጎን ለጎን፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን መደገፍና የንግድ/የመሠረተ-ልማት ትስስርን ማስፋፋት የደህንነት ሥጋቶችን በዘላቂነት ለመቀነስ መሠረት መሆኑን መክረውበት ነበር።

“አልሸባብንና ሌሎች የአሸባሪ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት ሁለቱ ሀገራት በጋራና በትብብር ለመሥራት ተስማምተዋል” የሚለውን የወቅቱን ስምምነት በመጥቀስ አርሲ ላይ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት መንግስት ከአክራሪነት ጋር አያያዞ ለመጀመሪያ ጊዜ ማቅረቡን ያመለከቱት የግብረኃይሉ አባል፣ “አሜሪካና ኢትዮጵያ በዚህ አግባብ እየመከሩበት እንደሆነ ተሰምቷል። ምክሩም አሁን ሽብርተኛ ከሚባሉት በተጨማሪ ሌሎች ታጣቂዎች በሽብር ወንጀል ሊፈረጁ እንደሚችሉና ይህም በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ አቋም እንዲያዝ ማስቻል ነው” ብለዋል።

“ባለን የግንኙነት መስመር ተጠቅመን በተለይ የተደረገውን ውይይት ቁልፍ ጉዳይ አጣርተን እናቀርባለን” ያሉት የቀድሞው የህወሃት መስራች ኢንጂነር ግደይ፣ ለግብረኃይሉ እስካሁን ያቀረቡት መረጃ የለም። ሌላው የግብረኃይሉ አባል ኢንጂነር ሙሉጌታ “ይህን መንግስት አቅለን እያየን ወደቅን” በማለት ስጋታቸውን መግለጻቸውን ጠቅሰን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን አይዘነጋም።

በአዋጁ መሠረት በሕግ የሚያስጠይቁ ዋና ዋና የሽብር ተግባራት፡-

  • የፋይናንስ ድጋፍ፡ ለሽብርተኛ ድርጅት፣ አባል ወይም ተግባር የሚውል መሆኑን እያወቁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ገንዘብ፣ ንብረት ወይም ማንኛውንም የፋይናንስ አገልግሎት መሰብሰብ፣ ማቅረብ ወይም ማስተላለፍ። የገንዘቡ ምንጭ ሕጋዊ ቢሆንም እንኳ ለሽብር ዓላማ ከዋለ ወይም እንዲውል ከተደረገ በወንጀል ያስጠይቃል።
  • የቁሳቁስና የዕርዳታ አቅርቦት፡ ለማንኛውም የሽብር ቡድን አባል የጦር መሣሪያ፣ ፈንጂ፣ ወታደራዊ አልባሳት ወይም የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ማቅረብ።
  • ለላና መጠለያ መስጠት፡ የድርጅቱን አባላት በቤት፣ በሆቴል ወይም በማንኛውም ስፍራ መደበቅ ወይም ጥበቃ ማድረግ።
  • የትራንስፖርትና መገናኛ ማመቻቸት፡ ለሽብር አባላት እንቅስቃሴ የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ወይም የመገናኛ ዘዴዎችን (ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ የሬዲዮ ሞገድ) ማመቻቸት።
  • ምልመላና ስልጠና፡ ለሽብርተኛ ድርጅት አዳዲስ አባላትን መመልመል፣ ማስተባበር ወይም ማባበል። በድርጅቱ ውስጥ ላሉ ወይም አዲስ ለገቡ አባላት ወታደራዊ፣ የቅስቀሳ፣ የቴክኖሎጂ ወይም የታክቲክ ስልጠና መስጠት (ወይም ለስልጠና መሄድ)።
  • ፕሮፓጋንዳና ማነሳሳት፡ የሽብርተኛ ድርጅትን ዓላማ፣ መፈክር ወይም ተግባር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች (በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በጽሑፍ፣ በምስል ወይም በድምጽ) ማሰራጨት እና መደገፍ። የሽብር ተግባር እንዲፈጸም ቀጥተኛም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ጥሪ ማቅረብ፣ ማነሳሳት ወይም ማበረታታት።
  • አባልነትና ተሳትፎ፡ በአዋጅ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት አባል መሆን፣ በስብሰባዎቻቸው ላይ መሳተፍ፣ መዋጮ መክፈል ወይም የድርጅቱን ዓላማ ለማስፈጸም በማንኛውም እንቅስቃሴ ውስጥ እጅና ጓንት ሆኖ መንቀሳቀስ።
  • መረጃ መደበቅ (አለመጠቆም)፡ አንድ የሽብር ተግባር ሊፈጸም እንደሆነ ወይም መፈጸሙን፣ የሽብርተኛ ድርጅት አባላት ያሉበትን ስፍራ እያወቁ ለሕግ አስከባሪ አካላት ሳይጠቁሙ መቅረብ ወይም መረጃን መደበቅ።

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ወንጀሎች እንደ ጥፋቱ ክብደት (ለምሳሌ በሰው ሕይወትና በሀገር ደህንነት ላይ ባደረሱት ጉዳት መጠን) ከባድ የእስራት ቅጣት (ከበርካታ ዓመታት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት) እና የንብረት መውረስን ጨምሮ ከፍተኛ ሕጋዊ ቅጣቶችን እንደሚያስከትሉ በሕጉ ተደንግጓል።

የኢትዮጵያ መንግስት ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሃትን (TPLF) እና ሸኔን (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት – OLA) በአሸባሪነት ፈርጆ እነነበር አይዘነጋም። ሚያዝያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ፣ ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ ከጸደቀ በኋላ፣ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሕዋሃትን የአሸባሪነት ፍረጃ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በአብልጫ ድምፅ መነሳቱ ይታወሳል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ህወሃት – የግዳጅ አፈሳ ፣ የታጣቂዎች ጥምረት፣ ከሻዕቢያ ፣ ከሱዳን አሸባሪና ግብጽ ጋር እየሰራ”ተጠቃሁ”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በኃይል የጊዜያዊ አስረዳደሩን በማፍረስ ስልጣን...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ረቂቅ በጀት አጸደቀ

አዲስ ሪፖርተር ዜና አዲስ አበባ — የሚኒስትሮች ምክር ቤት...

ካይሮ ያቀኑት ኢሳያስ “ግብፅ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ”

ኢዲስ ሪፖርተር ካይሮ — የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትላንትናው...