ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ የአብሮነት ቦርድ ሊቀመንበርነት ሹመትን አልቀበልም አሉ፤ ህወሃት ስብስቡን በቦርድ ሰብሳቢነት እንዲመራ ሃሳብ አቀረቡ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የተበተነው የአቶ ልደቱ አያሌው አብሮነት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ባደረገው ስብሰባ የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ የሾማቸው ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ “ወንድሞቼ” በማለት አስቀድመው ከሥራ አስፈጻሚነት ራሳቸውን ባሰናበቱበት ግብረኃይል ውስጥ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸውን እንደማይቀበሉ አመለከቱ። በምትካቸው ከህወሃት የተወከሉት መሪ እንዲሆኑ ጠይቁ።

የተጠናቀቀውን ብሔራዊ ምርጫ “በሚቻለው ሁሉ ለማሰናከል” አቶ ልደቱ ያቋቋሙት አብሮነት በሻዕቢያ መሪነት በሚንቀሳቀሰው የአቶ ነዓምን ድርጅት እንዲዋጥ ከተደረገ በኋላ ስብሰባ አቁሞ እንደነበር አባላቱን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ከወራት በኋላ ስብሰባውን ለሁለተኛ ጊዜ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ የጠራው አብሮነት “ምን ሊሠራ እንዳሰበ ባይገባንም አዲስ ቦርድ ይመረጥ ብለውን ነበር” የሚሉት የስብስቡ አባል፤ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በአሥራ አንድ ድምፅ በሰብሳቢነት፣ አቶ ቢኒያምን በአሥር ድምፅ በጸሐፊነት መምረጡን አመልክተዋል። ኢንጂነር ሙሉጌታ አራት፣ አቶ ታምሩ ሦስት ድምፅ በማግኘት ወድቀዋል።

ምርጫው ከመደረጉ በፊት እነ አቶ ታምራት ላይኔ ባዘጋጁት የስብሰባው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ምክንያታቸው በውል ባይታወቅም፣ አቶ ልደቱ ከሚመሩት ሰባት አባል ያለው ሥራ አስፈጻሚ በላይ የቦርዱ አመራሮች ሥልጣን እንዲኖራቸው ባቀረቡበት ወቅት አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር።

በመጨረሻ ሰነዱን ያዘጋጁት ክፍሎች ሐሳብ አሸንፎ የቦርድ አባላት ስያሜ ካለቀ በኋላ ሰኞ ዕለት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በዋትስአፕ ግሩፕ ምርጫውን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል።

የምሥራቅ ኢትዮጵያ የትጥቅ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ኃላፊነት ወስደው እየሠሩ ያሉት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል “ስለ ተሰጠኝ ድምፅና አመኔታ እጅግ አመሰግናለሁ። በሌላ ተመሳሳይ አደረጃጀት ውስጥ በአመራር ላይ የምሳተፍ ስለሆነ የምርጫውን ውጤት መቀበል ቸግሮኛል” በማለት ፍላጎት እንደሌላቸው አመልክተዋል።

ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ሌላ ተመሳሳይ በኦሮሞ ልጆች የሚመራ ግብረኃይል ማቋቋማቸውና በአብሮነትና አቶ ነዓምን ስብስብ ውስጥ ያሉት “አናሳ ብሔር ተወካይ” የሚባሉትን እያስኮበለሉ እንደሆነ በመግለጽ ሲከሰሱ ነበር።

“የአቢሲኒያ ስብስብ ነው። እናፈርሳቸዋለን” በማለት ራሳቸውን ከግብረኃይሉ አግልለው የነበሩት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል፣ የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ተባባሪ አቶ ነዓምን “ከኦሮሞዎች ጋር መሥራት አይቻልም” ማለታቸው መዘገቡን ተከትሎ “መሳቂያ ሆነናል” በሚል አቶ ጂረኛን ጨምሮ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ስብሰባ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር።

በዚሁ ስብሰባ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በመኪና ወደ ሌላ ከተማ እየተጓዙ መሆኑን ገልጸው በተቆራረጠ ድምፅ ስለ ምርጫ አጭር አስተያየት ሰጥተው ተሰናብተው ነበር። ይህ በሆነ በሦስተኛው ቀን፣ የቦርድ ሰብሳቢ የተደረጉት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል፦ “ወዳጆች እኔ ጥቆማውን ለመቀበል እንደማልችል ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴም አስቀድሜ እንደለቀቅሁ በዙም ገጽ ላይ በጽሑፍ አስታውቄ ነበር። በቃል ባለመናገሬና አስቀድሜ በመውጣቴ አሁን የታየው ውጤት እንዲመጣ ምክንያት ሆኛለሁ። ይቅርታ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ” በማለት ስንብታቸውን በይፋ አውጀዋል።

“ባለፈው የቦርድ ስብሰባ ስለ ተሰጠኝ ድምፅና አመኔታ እጅግ አመሰግናለሁ። በሌላ ተመሳሳይ አደረጃጀት ውስጥ በአመራር ላይ የምሳተፍ ስለሆነ የምርጫውን ውጤት መቀበል ቸግሮኛል። የሰጣችሁኝን ኃላፊነት ለመቀበል ብዙ አሰብኩበት፤ መከርኩበት። ሆኖም በግልጽ የሚታየውን የቃል ጠባቂነት ቅራኔ (Conflict of Commitment) ማስታረቅ አልቻልኩም:: ስለዚህም የተመረጥኩበትን ኃላፊነት መቀበል አለመቻሌን እገልጻለሁ” ብለዋል።

“በእኔ በኩል ማድረግ የምችለው ራሴን ከተመረጥኩበት ቦታ በመልቀቅ ለሌሎች በር መክፈት ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ የቦርድ ሰብሳቢ የአደባባይ ሰው መሆን አስፈላጊ አይደለም። አንድ ድርጅት የሚወከለው በአንድ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ስለዚህም ብንያምና ታምሩ ሰብሳቢና ጸሐፊ ሆነው እንዲያገረግሉ ቦርዱ እንዲፈቅድ በአክብሮት ሐሳብ አቀርባለሁ” በማለት ሕወኃትን በመወከል ምክትላቸው ሆነው የተመረጡት እንዲተኳቸው አቅርበዋል።

በደብዳቤያቸው መጨረሻ “በቅሬታ ስሜት፣ ሕዝቅኤል” ሲሉ ስማቸውን አትመው ምርጫውን ውድቅ ቢያደርጉም፣ እሳቸውን ጨምሮ የኦሮሞ ወኪሎች ከሁሉም የገሃድ አደረጃጀቶች በመውጣት በሕቡዕ እንደሚንቀሳቀሱ በሚታወቁ አደረጃጀቶች ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ በተለያዩ ወቅቶች አዲስ ሪፖርተር በማስረጃ በማስደገፍ መዘገቧ የሚታወስ ነው።

ምርጫውን ለማደናቀፍ “ሕዝባዊ አመጽ እናቀጣጥላለን” በሚል ከፍተኛ በጀት በማፍሰስ በአገር ቤት ከፖለቲካ ድርጅት አመራሮችና የሕቡዕ አደረጃጀትና የሃይማኖት ክንፍ ጋር በመመስጠር፣ ታጣቂ ኃይሎች ሳይቀር ሕዝብ ድምፅ እንዳይሰጥ በማስፈራራት በትብብር ቢሠራም ውጤታማ ሊሆን እንዳልቻለ ግብረኃይሉ መገምገሙን መዘገባችንም አይዘነጋም።

በግምገማው “ሕዝብ ሊተባበር አልቻለም፤ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣትም ፈቃደኛ አልሆነም። በስፋት ሠርተዋል የተባሉት የአማራ ድርጅቶች እንኳን ከለንደን በስተቀር ከሃምሳ በላይ ሰዎች አልወጡላቸውም። ይህ ውድቀት ነው። ልንገመግምና አዲስ ስትራቴጂ ልንንደፍ ይገባል” በማለት ኮሚቴ ሰይመው የውድቀታቸውን መንስኤ እየጠኑ መሆናቸውን አባላቱ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።

በዚህ መነሻ ይመስላል ከግምገማው ጎን ለጎን ለድኅረ ምርጫ በተያዘው ዕቅድ መሠረት የሃይማኖት ልዩነት መፍጠርና ታጣቂ ኃይሎችን ማደራጀት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን፣ ታጣቂ የሚባሉትን ውስን ወይም ከአመራር ውጪ ምንም ተዋጊ ኃይል የሌላቸውን ተገንጣይና ከኢትዮጵያ ተለይተው ወደ ሱዳንና ሶማሊያ መጠቃለል የሚፈልጉ ቡድኖችን ለማሰባሰብ አዲስ ግብግብ መጀመሩን የአዲስ ሪፖርተር የዜና ምንጮች አሰላለፉን ጠቅሰው አስታውቀዋል። ዝርዝሩን እናስከትላለን።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

መመህር ፋንታሁን ዋቄና ተባባሪዎቻቸው ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ እንዲደረግ ክስ ቀረበባቸው

አዲስ ሪፓርተር ዜና ፡- በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፣"በሃይማኖት ሽፋን...

ለሽብርና ወታደራዊ ስልጠና ወደ ወደ ኤርትራ ሊጓዙ የነበሩ የኦብነግ ምልምሎች ፑንትላንድ ላይ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በተሳሳተ መረጃ ተደልለው ለሽብር ስልጠና...

የቤት አከራሮች ዛቻና የበታች መዋቅሩ ሌብነት ዜጎችን ጭንቀት ውስጥ ጥሏል፤ አስተዳደሩ ” በህግ እቀጣለሁ”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - "አራት ልጆች አሉኝ። ቤቱን ከተከራየሁ...