በባህላዊ መንገድ የአገሪቱ ሕዝብ 3 ሚሊዮን ነው ቢባልም፣ እጅግ ታማኝ የሆኑ ምንጮች እንደሚያመለክቱት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ሕዝብ ከ1.9 ሚሊዮን አይበልጥም፤ በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙት አጠቃላይ የአፍሪካ ስደተኞች መካከል 30% የሚሆኑት ከዚች አነስተኛ አገር የወጡ ናቸው። ወጣቱ አገሪቱን ጥሎ በመሰደዱ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ የቀሩት የአረጋውያን ብቻ ናቸው። ለምሳሌ ከከረን ከተማ ይልቅ በኡጋንዳ ካምፓላ ውስጥ የሚኖረው ኤርትራዊ ቁጥር ይበልጣል። ከበርካታ ችግሮች እና ከኢኮኖሚ ውድቀቱ ጋር ተዳምሮ ምልክቶቹ ኤርትራ እንደ አገር እንደማትቀጥል ነው
አዲስ ሪፖርተር ዜና አዲስ አበባ— የኤርትራ የአሰያየም ሆነ አገራዊ ምሥረታዋ ታሪካዊ መሠረት የሌለውና በቅኝ ገዥዎች ካርታ የተፈጠረ አርቴፊሻል መሆኑን በመጥቀስ፣ አገሪቱ አሁን ላይ በበረሃው የ“ሳህል መርህ” እና ዕቅድ-አልባ አምባገንናዊ አገዛዝ ተቆልፋ ወደ ‘ድንጋይ ዘመን’ መውረዷን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ባሉባት ዘርፈ-ብዙ ውድቀቶች ምክንያት እንደ አገር የመቀጠል ዕድል የሌላት በመሆኑ ኢትዮጵያ አስቀድማ ራሷን ልታዘጋጅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አቶ ጌታቸው ስለ ኤርትራ ምሥረታና አሰያየም ታሪክ ሲያብራሩ፣ “ኤርትራ” የሚለውን ስም ያወጣው ፈርዲናንዶ ማርቲኒ የተባለና በ1889 (እ.ኤ.አ) የኤርትራ ገዢ ተደርጎ የተመደበ ጣሊያናዊ የጦር መኮንን መሆኑን ጠቅሰዋል። ቃሉ “ቀይ ባሕር” ወይም “የምስራቅ ባህር” ከሚል ትርጓሜ የመነጨ መሆኑንና የአሁኑ የኤርትራ መሪዎች ግን የ2000 ዓመት ታሪክ እንዳላቸው አድርገው ለመስበክ የሚሞክሩት አርቴፊሻል ጥረት ከሳህል በረሃ የጀመረውን ማንነት ታሪካዊ ለማስመሰል የሚደረግ የተሳሳተ ትርክት ነው ብለዋል። ከዚሁ የሳህል በረሃ የተቀዳው የኤርትራ አገርነት ቅስቀሳ ያመጣው ፍሬ ስደት፣ ድህነት እና ጭቆና በመሆኑ “ሮማንቲክ ቅዠት” ነበር ብለውታል። ህዝቡ ከቀድሞው አስተዳደር የተሻለ ነፃነትና ህይወት አላገኘም፣ ይልቁንም ሀገሪቱ የዜጎች ማጎሪያና የስደት ምንጭ እንደሆነች መረጃ አጣቅሰው አመልክተዋል።
ኤርትራ በአሁኑ ወቅት የገጠማትን ሁለንተናዊ ውድቀት ተዳምሮ ወደ ድንጋይ ዘመን መመለሷን አቶ ጌታቸው ባቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ሚዲያዎች ባካሄዱት ጥናታዊ ፊልምና መረጃዎች አስደግፈው መግለጻቸው ይታወሳል። “ሰዓት በኤትራ ቆሟል” በማለት ከተናገሩት ጀምሩት የተለያዩ ሪፖርቶችና ዶክመንታሪ ፊልሞች ላይ አቅራቢዎቹ በተረዱት መጠን ኤርትራን እና መሪዎቿን ስያሜ ሰጥተዋቸዋለች። አዲስ ሪፖርተር የኤርትራን መሮ “ኦክቶፐስ” ማለቷ ይታወሳል።
የኢኮኖሚና መሠረተ-ልማት መሞት፦ አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የሚጨበጥ “ኢኮኖሚ” የሚባል መዋቅር የሌላት ሲሆን፣ የነበሩት ፋብሪካዎች በሙሉ ሥራ አቁመዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አገሪቱን አፍኖ ለመግዛት ሲሉ ወደቦችንና የተፈጥሮ ሀብቶችን ሆን ብለው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማድረጋቸውንና ሕዝቡን በኮንትሮባንድና በዕለት ተዕለት አፈና ውስጥ እያኖሩት መሆኑን ገልጸዋል። ወደቦቹ ክፍት ከሆኑ ህዝብ ለስራ ስለሚጎርፍ ኢሳያስ አፈናቸውን ማስቀጠል አይችሉም።
የአመራር ማርጀትና የተተኪ ማጣት፦ በቅርቡ የፕሬዝዳንቱ ምክትል የነበሩት ሰው በ85 ዓመታቸው መሞታቸውንና አጠቃላይ የካቢኔ አባላት ዕድሜያቸው የገፋ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው፣ ብቻኛ ከ68 ዓመት በላይ ያልገፉት የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ብቻ መሆናቸውን አመልክተዋል። አገሪቱ ያለምንም የወደፊት የፖለቲካ ፍኖተ-ካርታ (Roadmap) በአንድ ሰው የአይረን ፊስት (Iron fist) አገዛዝ ብቻ እየተመራች በመንኮታኮት ላይ መሆኗን አስታውቀዋል።
የከፋ የዲሞግራፊና የስደት ቀውስ፦ የአገሪቱ ሕዝብ ቁጥር ከ1.9 ሚሊዮን በታች መውረዱንና በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ካሉት ስደተኞች 30 በመቶ ያህሉ ኤርትራውያን መሆናቸውን በመጥቀስ፣ አገሪቱ በአረጋውያን ብቻ የተሞላችና ወታደራዊም ሆነ ዲሞግራፊያዊ መሠረቷ የደቀቀ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከዚሁ ትንታኔያቸው በመነሳት “ኢትዮጵያ ልትዘጋጅ ይገባል” ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በማጠቃለያቸው፣ ኤርትራ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ፣ በዲሞግራፊና በፖለቲካ ሙሉ በሙሉ ተሰባብራ “በውድቀት አፍፍ” (Brink of disaster) ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን አስምረውበታል።
ይህ በሳህል ዲሲፕሊን ብቻ አገርን የማስቀጠል ሙከራ መጨረሻው ጥፋት መሆኑ የማይቀረውን ያህል፣ አገሪቱ እንደ አገር የመቀጠል አቅሟ በከፍተኛ ሁኔታ የተዳከመ በመሆኑ፣ ይህ የኤርትራ የመፈራረስ አደጋ በቀጣይ በቀጠናውና በኢትዮጵያ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ስትራቴጂያዊና ወታደራዊ ተፅዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟንና ደኅንነቷን ለማስከበር ከወዲሁ በአግባቡ ልትዘጋጅና ስልታዊ አቅጣጫዎችን ልትቀይስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምስራቅ አፍሪቃ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ይህን የተናገሩት በመከላከያ ዋር ኮሊኦእጅ በተዘጋጀ ሰፊ መድረክ ላይ ታጋባዥ ተናጋሪ ሆነው ነው። አቶ ጌታቸው መከላከያ ትልቅ ክብር ያለው ተቋም በመሆኑ በየስርቻው ያሉትን በማጥፋት ትልቁን ጉዳይ እንዲመለከት ሲያሳስቡ “አልመክራችሁም” በማለት ነው።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






