ለእንቁጣጣሽ የአዲስ ዓመት የአመጽ ዝግጅት ተጀመረ፤ “ሰላማዊ ትግል የምንለው ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ማሳሳቻና እና አገር ቤት ያሉትን ተባባሪዎች በሰላማዊ ስም ለመጠበቅ ነው”

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – ለመጪው አዲስ ዓመት የእንቁጣጣሽ በዓለ አዲስ አመጽ ለማስነሳት ዝግጅት መጀመሩ ታወቀ። አዲስ በተሻሻለው የአመጽ ግብረኃይል ስም ላይ “ሰላማዊ” የሚለው መጨመሩን አስመልክቶ ለተነሳ ውዝግብ “የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት እና አገር ቤት ያሉ የአመጹን አስተባባሪዎች ለመጠበቅ ሲባል የተጨመረ እንጂ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይገባም” በሚል ሚስጥሩ ቢገለጽም ምላሹ ግን “ረብ የለሽ፣ በትጥቅ ትግል የሚያምኑትን የሚያሸሽ ነው” ተብሏል።

“የኢትዮጵያ አገር አድን የፍትህና የዴሞክራሲ ሽግግር ስልታዊ የጋራ የትግል ሰነድ” በሚል ለውይይት ለአባላቱ የተሰራጨው መነሻ እንደሚያስረዳው ምርጫ እንዳይካሄድ የተደረገው ጥረት የተዘባረቅና ህዝብ የገዛው ባለመሆኑ ከሽፏል። ሰነዱ “ውድቀት” ብሎ በርካታ ጉዳዮችን ዘርዝሮ እንዳለው ከሆነ፣ ለመጪው አዲስ ዓመት አዲስ አመጽ እንዲቀጣጠል አቅጣጫ ተቀምጧል። “ተባባሪ” ያላቸው የአገር ውስጥ ድርጅቶችን የማስተባበሩ ስራ እንደሚጀመርም አመልክቷል።

በተቀመጠው ዕቅድ መሰረት ረብሻው እና አመጹ እንዴት እና በየትኛው የተመረጡ ቦታዎች እንደሚካሄድ ባይዘርዝርም አስረጂው አቶ ያሬድ ኃ/ማሪያም ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የህዝብ መገለገያ ተቋማትና ትራንስፖርትን አንስተዋል። ከተሰብሳቢዎቹ “በተቃዋሚ ድርጅቶች ዘንዳ የሚነሱ የመታገያ አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብልጽግና ተቋማዊ አድርጎ ለመመልስ ምክክር ብሎ እየሰራ ነው። እንዴት ነው ህዝብ ለማሳመጽ የምንችለው?” የሚል ጥያቄ ተንስቷል። ዶክተር ኢሳማኤል “ምክክሩ ፌክ ነው” በሚል ሰብሳቢውንና ኢንጂነር ግደይን አስደስተዋል።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ እንዳለው ጥያቄው ሲነሳ አቶ ነዓምን “በአማራ ክልል ከፍተኛ መለያየት ፈጥሯል። ቢሆንም ግን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ አታንሱ” በማለት ከሳምንት በፊት መናገራቸውን ስብሰባው ላይ ከተገኙ አጣርቶ ዘግቧል። እግረመንገዱንም አቶ ልደቱና አቶ ነዓምን በመካከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ ከስብሰባና ከቀጥታ ተሳትፎ ርቀዋል። በተለይም አቶ ልደቱ ከስደተኛ ጉዳያቸው ጋር ተያያዞ ስጋት ላይ መሆናቸውን ከሚቀርቧቸው መስማቱን አስታውቋል። በቅርቡ ለመሳይ መኮንን “ወደ አገር ቤት መግባት እፍለጋለሁ። የአገር ቤቱን ህግ ስለማውቅ የሚያስጠይቅ ትግል ውስጥ አልገባም” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

ቀደም ሲል የህዝባዊ አምቢተኛነት አደረጃ በሚል ምርጫው እንዳይካሄድ ሲሰራ የነበረው ግብረኃይል “የሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኛነ” በሚል ያወጣውንና ያዘጋጀው አዲስ ሰነድ ላይ በትናንትናው ዕለት በተካሄደ ስብሰባ “ሰላማዊ” የሚለው ተቀጽላ አከራክሯል።

ሁለት ጊዜ አቶ ልደቱን ጨምሮ አባላቱ ሊገኙ ባለመቻላቸው ስብሰባ ማድረግ ያቃተው የጋራ መደረኩ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ለመያየት የተገኙት ከአምስት የማይበልጡ አባላት ነበሩ። አቶ ያሬድ አቶ ነዓምንን ተክተው ማብራሪያ ሰጪና አቅጣጫ አመላካች ሆነው በቀረቡበት ስብሰባ፣ ኢንጂነር ሙሉጌታ ክፉኛ ሲቃቅወሟቸው፣ ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ የጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌና ቤኒሻንጉል ወኪሎች በመገፋታቸው የጋራ መደረኩን ጥለው መሸሻቸውን አመልክተዋል። አጋር የሚባሉት አካላት የራሳቸውን ጥምረት ፈጥረው በጫካ ካሉ አካላት ጋር ግንኙነት መጀመራቸውን አስታወቀዋል “ወደድንም ጠላንም በብሄር ብሄረሰቦች ተሳትፎና እኩልነት ልታምኑ ይገባችኋል” በማለት አሳስበዋል።

“ለምን ሰላማዊ የሚለው ተጨመረ” በሚል ክፉኛ የተቃወሙት ኢንጂነር ሙሉጌታ ከሃምሳ በላይ ድርጅቶች አለ ትላላቹህ፣ በመቶኛ ምን ያህሉ በሰላማዊ ትግል። ምን ያህሉ በትጥቅ ትግል፣ ምን ያህሉ በሁለቱም የትግል አይነቶች እንደሚያምኑ በዳታ የተደገፈ መረጃ የሚቀርብ እንደማይመስላቸው አስታውቀው፣ በሳቸው እምነት ከሁለትና ሶስት ሰዎች በስተቀር ሁሉም ስማቸውን ቀይረው ወይም በፊት ለፊት የትጥቅ ትግል ስለሚያራምዱና ስለሚደግፉ “ሰላማዊ” የሚለው ተቀጽላ ዋጋ እንደሌለውና ሌሎችን እንደሚያስቀይም አስታውቀዋል። “ሰላማዊ” የሚለው ተቀጽላ ትርጉም አልባ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ኢንጂነር ግደይም ተጨማሪ በምስጠት “ሰላማዊም ተባለ ህዝባዊ እምቢተኛነት ሁሉም አመጽ ነው። ጠብ መንጃም ማንሳት አመጽ ነው” በማለት “ሰላማዊ” የሚለው ተቀጽላ ብዙም አስፈላጊ እንዳልሆነ አመልክተዋል። አክለውም እሳቸው ያሉበት ድርጅት ጨምሮ በአብዛኛው ፋኖ፣ ኦላ፣ ህወሓት፣ አፋር ወይም ሌላ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አቶ ያሬድ በምላሹ ሃሳቡን አሰባስበው ለአለቆቻቸው እንደሚያቀርቡ ካስትያወቁ በኋላ፣ “ዘንግቼው ነው” በማለት “ሰላማዊ” የሚለው ስም በአዲሱ ስያሜ ላይ ተቀጽላ የሆነው አገር ቤት ያሉ የህቡዕ ተባባሪዎችና አመጽ አቀጣጣዮች ላይ መንግስት ሸኔ፣ ፋኖ፣ ወይም ሌላ ብሎ የከፋ እርምጃ እንዳይወስድና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብን ለማታለል እንደሆነ አቶ ያሬድ ተናግረዋል። “ትግሉ ሰላማዊ ነው ለማለት እንዲመቸን ነው” በማለት “ሰላማዊ” የሚለው እንዲጨመር መድረጉን አቶ ያሬድ ቢያስረዱም። ጥያቄውን ያቀረቡት ባለመስማማታቸው፣ በተለይም ኢንጂነር ሙሉጌታ “ውሳኔው ስለማይቀየር መናገር ዋጋ የለውም” በሚል ስሜት ሊሉት የፈለጉትን አስድረውታል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

እኔ ያልገባኝን ስለ አማራ ክልል ማን ያስረዳኝ? በልማትና በፈተና መካከል መንክላወስ!

ዛሬ በአማራ ክልል ስንት ልጆች ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለዋል? ሦስት...

የድሃ ቆዳ ገፈፋና ህጋዊ ማጅራት መቺነት / ለኢትዮጵያ ነጋዴዎች መረን መልቀቅ ማንን እንጠይቅ?

አዲስ ሪፖርተር - በአሁኑ ወቅት በአገራችን የኑሮ ውድነት የብዙዎችን...

የፌደራል መንግስት እና ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ትህነግ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ ተጠራ

አዲስ ሪፖርተር -በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ሁለንተናዊ ቀውስ ለማስቆም፣...