“አዲስ አበባ ከገባሁ ሁለት ዓመት አልፎኛል፤ ጦርነት መፍትሄ እንደማያስገኝ በህይወቴ በተግባር ተምሬያለሁ፣ አይቻለሁ፣ ይህን እመሰክራለሁ” ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  “በህይወቴ በተግባር ያየሁትና የተማርኩት ትልቅ ጉዳይ ቢኖር በጠብመንጃ  ወይም በጦርነት የሚፈታ ችግር እንደሌለ ነው” ሲሉ ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቁ። ሰላም የሚሰፍነው በውይይት ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

በኢህአዴግ ዘመን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ዋና ዳይሬክተር ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ይህን ያሉት “ወደ አዲስ ጦርነት መግባት አልፈልግም” በማለት ትግራይን ለቀው ወደ አዲስ አበባ መሸሻቸውን የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች መዘገባቸውን ተከትሎ ነው።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲተገበር የቻሉትን ሁሉ ጥረት ማድረጋቸውን ያስታወቁት ጄኔራሉ፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ከእውነተኛ ውይይትና ድርድር ውጪ ሊፈታ እንደማይችል አስታውቀው፣ ሁሌም የሰላም መንገድ አዋጪ መሆኑን አመልክተዋል።

“በህይወቴ ተሞክሮ የተማርኩት እውነት፤ ይህንን እውነት ለሰላም ስል እመሰክራለሁ” ሲሉ ጦርነትን አብዝተው እንደሚቃወሙ የገለጹልን ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን፣ በአዲስ አበባ የራሳቸውን ስራ መሰራት ከጀመሩ ሁለት ዓመት አልፏቸዋል።

አዲስ ሪፖርተር አዘጋጅ ከሁለት ዓመት በፊት ጄኔራሉን አዲስ አበባ በተደጋጋሚ አግኝቷቸዋል። በወቅቱም አዲስ አበባ በመዘዋወር የግል ስራቸውን እየሰሩ እንደሆነ መደበኛ ባልሆነ ውይይት መናገራቸውን ያስታውሳል። አዲስ አበባም ከገቡ ሁለት ዓመት እንዳለፋቸው፣ ከሙያቸው ጋር የተያያዘ ስራ እንደሚሰሩና “ሰላማዊ ውይይት ብቸኛው አዋጪ መንገድ ነው” መሆኑን እንደሚያምኑም በተለያዩ ቀናት መግለጻቸውን አይዘነጋም።   

ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን አዲስ አበባ የግል ስራቸውን መስራት መጀመራቸው እየታወቀ ለምን ዛሬ መቀለን ጥለው እንደወጡ ተደርጎ ለመዘገብ እንደተፈልገ ለማጣራት በግል ስልካቸው ስንጠይቃቸው፣ “ከሁለት ዓመት በፊት ተገኛኘተን አይተኸኛል” በማለት ሚዲያዎች ያሰራጩትን ዘገባ እንደማንም ሰው ማየታቸውን አመልክተዋል። ምክንያቱንም እንደማይረዱ አስታውቀዋል።

ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በግል የፌስ ቡክ ገጻቸው ከማናቸውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ራሳሳቸውን ከፖለቲካ ማግለላቸውን ሲገልጹ፣ በቀጣይ በግል ህይወታቸው፣ ስራቸው እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እንደማንኛውም ነጻ ዜጋ እንደሚያተኩሩ ገልጸው ነበር። ይህንን አቋማቸውን ይፋ ያደረጉት አዲስ አበባ ተቀምጠው እንደሆነም የሚታወስ ነው። ይህ ውሳኔያቸው በግል የፌስ ቡክ አካውንታቸው አሁን ድረስ አለ።

እሳቸው ቃል በቃል ባይናገሩም አሁን ትግራይን እየመራ ያለውን የህወሃት አንድ ክፍል አካሄድ እንደሚቃወሙ የሚያውቁ እንደሚሉት፣ ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ይህን አቋማቸውን ዛሬ እንደተንጸባረቀ ተደርጎ መዘገቡ፣ ፖለቲካዊ ፋይዳው ሊገባቸው አልቻለም።

እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በርካታ መኮንኖች በኃይል ትግራይን እያስተዳደረ ያለው የህወሃት አንድ ክፋይ የሚከተለውን የጦርነት መንገድ በመቃወም፣ እንደተለዩት ይታወቃል። ሃራ መሬት ሆነው የሚደራጁትን ጨምሮ በርካታ ጄነራሎች አዲስ አበባ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ህወሃት የጤና ተቋማትና ትምህረት ቤቶች ሰራዊትና መሳሪያ እያከማቸባቸው ነው፤ ህዝብ ሰግቷል

አዲስ ሪፖርተር l መቀሌ — ከትግራይ የሚወጡ ዜናዎችና እማኞች...

ኢሳያስ የሃያ ሁለት ዓመታት ተቃዋሚያቸውን “እየፈረሰ ነው” ለተባለው “ጽምዶ” የቅስቀሳ አስተባባሪ አድርገው ሾሙ

ሰሞኑን የሚሰሙት መረጃዎች የጽምዶን ሞት አመላካች ናቸው እየተባለ ነው።...

ስዊድን ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ የሚያሳጣ ሕግ ሥራ ላይ አዋለች

ከታጣቂዎች፣ ከአክራሪ ድርጅቶች ወይም ከተደራጁ የወንጀል መረቦች (Gangs) ጋር...