አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — የትግራይ ዴሚክራሲያዊ ስምረት ድርጅት በውስጡ እየታዩ ያሉ የፖለቲካ ድክመቶችን በዝርዝር ከገመገመ በኋላ፣ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ። በሽታው ከየኋላቀር ቡድን ባህሪ ጋር ተያይዞ የመጣ ድርጅትን የማፍረስ እንቅስቃሴ መሆኑንም አመልክቷል። መግለጫው ጥፋተኛ ያላቸውን አልዘረዘረም።
የስምረት ስራ አስፈጻሚ መስከረም ስድስት ቀን ስብሰባ ማድረጉን አስታውቆ ባሰራጨው መግለጫ “በድርጅቱ ውስጥ የተዛባ ውንጀላና የሐሰት ወሬ ተሰማርተው ድርጅቱን ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከአሁን በኋላ አልታገስም” ብሏል። እንደ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ግምገማ፣ ይህ ለረጅም ጊዜ የቆየው የተዛባ ፍላጎትና መከፋፈል ከ“የኋላቀር ቡድን” ባህሪ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
በተለይም በአንዳንድ የድርጅቱ አባላት ከስምረት ድርጅት አሠራርና ደንብ ውጭ እየተሰራጩ ያሉ ወሬዎች መንስኤና መነሻቸውን በመለየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለማስቀመጥ በቅርቡ መደበኛ የስምረት ድርጅት ምክር ቤት ስብሰባ እንደሚካሄድና የምክር ቤቱ ውሳኔ ይፋ እንደሚደረግ አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴው በመግለጫው አመልክቷል። ስምረት ያወጣው መግለጫ የትግርኛ ትርጉም ከስር ቀርቧል።
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ድርጅት አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴ ዛሬ 6 መስከረም 2019 ዓ.ም. መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
በዛሬው የስብሰባው ውሎ አስፈላጊና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቷል።
በአሁኑ ወቅት ትግራይ ለትግራይ ሕዝብ “ምድራዊ ሲኦል” ሆና በመቀጠሏ የትግራይ ልጆች የሚወዱትን ክልላቸውን ትተው እግራቸው ወደሚመራቸው አቅጣጫ እየተሰደዱ መሆናቸው ሁሉም የሚያውቀውና የሚረዳው እውነታ ነው።
ሕዝባችን ከአሁን በኋላ በያለበት የሥቃይ ደረጃ ረዥም ጊዜ ሊቀጥል እንደማይችል በዝርዝር የገመገመው የስምረት ድርጅት አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴ፣ በሕዝባችን ላይ የተጫነውን የውጭ ኃይሎች መሣሪያ ሆኖ የሚገኘውን “የኋላቀር ቡድን” ለማስወገድ በመጨረሻው ደረጃ ላይ እንደምንገኝ መላው ሕዝባችን እንዲያውቅና ይህንን በትክክል ተረድቶ የራሱን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርቧል።
በትግራይ በመካሄድ ላይ ባለው ወታደራዊ ግፍና ውድመት ምክንያት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ተማሪዎች በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበትን ዕድል ለመፍጠር የፌዴራል የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠውን አዎንታዊ ምላሽ የስምረት ድርጅት አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴ አድንቋል።
በዚህ አጋጣሚም ያ “የኋላቀር ቡድን” በከፍተኛ የፌዴራል ተቋማት ላይ እያደረገ ያለውን አስቂኝና አሳፋሪ ጫና መላው ማኅበረሰብ እንዲታገለው ጥሪ አቅርቧል።
በሌሎች የፌዴራል መንግሥት ተቋማትም በትግራይ እየታዩ ያሉ መሰል ችግሮችን በቀጣይነት ለመፍታት አቅሙ በፈቀደ መጠን ሁሉም እንዲተባበርና የማይታክት ጥረት እንዲደረግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በሌላ በኩል፣ የስምረት ድርጅት በውስጡ እየታዩ ያሉ የፖለቲካ ድክመቶችን በዝርዝር ገምግሟል። እንዲህ ባለ የተዛባ ውንጀላና የሐሰት ወሬ ተሰማርተው ድርጅቱን ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከአሁን በኋላ እንደማይታገስ ገልጿል።
እንደ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ግምገማ፣ ይህ ለረጅም ጊዜ የቆየው የተዛባ ፍላጎትና መከፋፈል ከ“የኋላቀር ቡድን” ባህሪ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው።
በተለይም በአንዳንድ የድርጅቱ አባላት ከስምረት ድርጅት አሠራርና ደንብ ውጭ እየተሰራጩ ያሉ ወሬዎች መንስኤና መነሻቸውን በመለየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለማስቀመጥ በቅርቡ መደበኛ የስምረት ድርጅት ምክር ቤት ስብሰባ እንደሚካሄድና የምክር ቤቱ ውሳኔ ይፋ እንደሚደረግ አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴው አስታውቋል።
በመጨረሻም፣ በትግራይ እያጋጠመ ያለውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ በሰዎችና በእንስሳት ሕይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ከፍተኛ ጉዳት የስምረት ድርጅት አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴ በዝርዝር መርምሯል።
ይህንን አደጋ ለመከላከል የሚመለከታችሁ መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተገቢውን ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ዘላለማዊ ትዝታ ለሰማዕታችን! የስምረት ድርጅት አስፈጻሚ ጉዳይ ኮሚቴ
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






