ተመድ ኢሳያስ ያሰረቻቸውን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የሕሊና እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አሳሰበ

Date:

አዲስ ሪፓርተር (ጀኔቭ)- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት፣ በኤርትራ ለ18 ዓመታት ያለ ፍርድ ታስረው የቆዩ 13 ዜጎች መፈታታቸውን ተከትሎ በሰጠው መግለጫ፤ አሁንም በሀገሪቱ በእስር ላይ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የሕሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ።

የጽሕፈት ቤቱ ቃል አቀባይ ሰይፍ መጋንጎ በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ፣ የ13ቱ እስረኞች መፈታት አበረታች ቢሆንም፣ በኤርትራ አሁንም ከ10,000 በላይ ዜጎች ያለ ፍርድ በታሰሩበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የ18 ዓመታት የጨለማ እስር

ተፈቺዎቹ ግለሰቦች ለረጅም ዓመታት የታሰሩት ያለምንም ክስና የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ዓይነቱ “የዘፈቀደ እስራት” (Arbitrary Detention) የኤርትራ መንግሥት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በግልጽ እየጣሰ ስለመሆኑ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

የG-15 ጉዳይ፡ የፍትህ ጥያቄ

የተመድ መግለጫ ልዩ ትኩረት የሰጠው በ1994ዓ.ም. የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ በቁጥጥር ስር ስለዋሉት የG-15 ተብለው የሚታወቁ የኢሳያስ የካቢኔ አባላት የነበሩ ቡድን አባላት ነው። እነዚህ ግለሰቦች የቀድሞ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሲሆኑ፣ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲሰፍንና ሕገ-መንግሥታዊ ለውጥ እንዲደረግ በመጠየቃቸው ብቻ ለ24 ዓመታት የት እንዳሉ ሳይታወቅ ታስረው ይገኛሉ። ተመድ እነዚህ የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቆ አሳስቧል።

የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶች ምን ይላሉ?

ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች (Amnesty International እና Human Rights Watch) የተገኙ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በኤርትራ የእስረኞች አያያዝ እጅግ አስከፊ ነው።

  • የእስር ቦታዎች፦ አብዛኞቹ እስረኞች ከመሬት በታች በሚገኙ ጉድጓዶች ወይም በብረት ኮንቴይነሮች ውስጥ እንደሚታሰሩ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
  • የእስረኞች ስብጥር፦ በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ በሃይማኖታዊ ዕምነታቸው (በተለይ በታገዱ የሃይማኖት ተከታዮች)፣ እና በብሔራዊ አገልግሎት ጥያቄ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የሃይማኖት መሪዎችና ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።
    • የሕግ ከለላ እጥረት፦ በኤርትራ እስረኞች ጠበቃ የማግኘት፣ ቤተሰብ የመጠየቅ ወይም የፍርድ ቤት ቀጠሮ የማግኘት መብት የላቸውም።

በአጠቃላይ የተባበሩት መንግስታት ተመድ ኤርትራ ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን እንድታከብር ቢጠይቅም፣ የኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት ለዓመታት ለእንዲህ ዓይነት ጥሪዎች ጀርባውን ሲሰጥ ቆይቷል። አስራ ሶስት እስረኞች መፈታታቸው እንደ መልካም ዜና ቢወሰድም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አሁንም በጨለማ ውስጥ ባሉበት ሀገር፣ እውነተኛ ነፃነት መጣ ለማለት አዳጋች ነው። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና በቁጥር ላይ ሳይሆን በኤርትራ ስር ነቀል የዴሞክራሲ ለውጥ እንዲመጣ መሆን እንዳለበት ባለሙያዎች ያሳስባሉ።

በኤርትራ መንግስት ላይ ከየአቅጣጫው የሚሰነዘረው ውግዘትና “አምባገነን” ተብሎ የተፈረጀውን የኢሳያስ መንግስትን የሚረዱ በስደት ያሉ የኤርትራ ተወላጆች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ፖለቲካዊ እንደሆነ መገለጹ አይዘነጋም።

በቅርቡ ራሳቸውን የገለጡና ከኤርትራ እንዳመለጡ የገለጹ እንዳሉት የኤርትራ ሕዝብ “ከነጻነት” በሁዋላ ያተረፈው ባርነት እንደሆነ አመልክተው፣ ድርጊቱን በመደጋገም “አሳፋሪ” ብለውታል።

Website፡ https://addisreporter.com/

Email፡ info@addisreporter.com

Telegram፡ https://t.me/addisreporter11

X፡ https://x.com/addisreporter

Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...