አቶ ነዓምን በቁጣ ድምጽ “እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ይነሳል፤ ከዚህ በላይ የሚያሳስቡ ጉዳዮች አሉብን። ስለ ኤርትራ መንግስት ማንሳት አያስፈልግም” አሉና ጥያቄውን አበሻቀጡት። አቶ ገዱ ነዓምንን ተከትለው “ህብረቱ ጊዜያዊ ነው” በማለት ለማጀብ ሞከሩ። …. “ከመንግስት ጋር ችግር አለ ብለን እንዴት ከኤርትራ ወይም ሌላ አገር ጋር ሆነን ኢትዮጵያን እንወጋለን፤ ይህ አይዋጥልኝም”
አዲስ ሪፖርተር – “አንተ” አሉ አንዱ ተሳታፊ፣ የሰው ልጆች የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እንደሆኑ በማስታወቅ በግልና በቡድን መግለጫ የሚያወጡት አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም እየጠቆሙ፤ “አንተ በሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነት ትታወቃለህ። የኢትዮጵያዊያን መብት እንዲከበር ተከራካሪ ነኝ ትላለህ፤ 1200 የትግራይ እህቶችና እህቶች የደፈረ፣ 700 የሚሆኑትን ሆን ብሎ በኤች አይቪ ቫይረስ እንዲያዙ ያደረገውን ሻዕቢያን እንዴት ታየዋለ?” ሲሉ ጠየቁ።
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ አባይ፣ አቶ መስፍንና የደቡብ ተወካይ የተባሉት በጥቅሉ ሶስቱ ሰዎች ዶክተር ኢስማኤልን ደገፉና “የሰው ልጆች መብት ተከራካሪ ነኝ” የሚሉትን አቶ ያሬድን ነቀፉ። ይህ ሲሆን አቶ ልደቱ አያሌው አልተነፈሱም። የሻዕቢያ ተወካይ አቶ ነዓምን ጣልቃ ገብተው “ስለ ኤርትራ መንግስት አታንሱ” በማለት መመሪያ ሰጡ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነዓምንን ተከትለው “ ከኤርትራ ጋር የተጀመረው ህብረት ጊዚያዊ ነው፤ ህብረት ቢፈጠረም ኤርትራ የኢትዮጵያ ናት” በማለት የሻዕቢያ ስም እንዳይነሳ ተከላከሉ።
ይህ ክርከር የተነሳው የቀድሞው የኢህአፓ አመራር ኢንጂነር ሙሉጌታ ሰብሳቢ የሆኑበት ኢትዮጵያን በህዝብ እንቢተኛነት ለማተራመስ ከሻዕቢያ የወረደውን መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርጉ ስራ አስፈጻሚዎችን ለመምረጥ ባለፈው ሳምንት በተያዘው ቀጠሮ መሰረት በተደረገ ስብሰባ ላይ ነው።
በፕሪቶሪያ የሰላም አማራጭ ስምምነት መሰረት በተቋጨው ጦርነት ወቅት በትግራይ እናቶች፣ እህቶችና ታዳጊዎች ላይ ሻዕቢያ ያደረሰውን የመብት ጥሰት ሲያወግዙ የነበሩት፣ ራሳቸውን በሰብአዊ መብት ተሟጋችነት የሚገልጹትና በተለያዩ ሚዲያዎች በዚሁ አግባብ መግለጫ የሚሰጡት አቶ ያሬድ “ይህን መንግስት ለማስወገድ ከሴጣንም ጋር ቢሆን እንሰራለን” በማለት አቶ ነዓምንን ደግፈው መናገራቸውን ተከትሎ ነበር፣ መራራ ጥያቄ የቀረበላቸው።
ባለፈው ሳምንት በአሜሪካና አውሮፓ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት፣ “አገር አንቀጥቅጥ” የተባለ የሳይበር ላይ ክተት ለማወጅና የኢትዮጵያን ህዝብ በተቃውሞ በማነሳሳት የትጥቅ ትግሉን ለማገዝ እነ አቶ ልደቱ ከትህነግ ሰዎችና ከሻዕቢያ ጋር መክረው ዕቅድ ማዘጋጀታቸው ይፋ መሆኑ ይታወሳል። ይህንኑ በድምጽ የተደገፈ ስብሰባ አስመልክቶ ባቀርብነው ሪፖርት ስብሰባ ለቅዳሜ ተላልፎ ነበር።
አቶ ነዓምን መመሪያና አቅጣጫ እየሰጡ ሲመሩት በነበረው ያለፈው ሳምንት ስብሰባ ውሳኔ መሰረት አምስት ሰዎችን ለመምረጥ እቅድ የያዘው ስብሰባ ሲጀመር ሃያ አንድ ሰዎች ተገኝተው ነበር። ጃዋር መሐመድ ድጋሚ ባልተገኙበት በዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ አባይ የተባሉ የትግራይ ተወላጅ መሰረታዊ ጉዳይ ማንሳታቸውን ተከትሎ ስብሰባው ወደ ንትርክ ተቀየረ።
“ምንድን ነው የምናሳካው ዋና ዓላማችን? በምን ጉዳይ ላይ ነው ያለ ልዩነት አንድ ሆነን የምንሰራው? የሻዕቢያንና የኢትዮጵያን ሁኔታ እንዴት ነው የምናየው? ይህ ግልጽ መህን አለበት” ሲሉ አቶ አባይ ጥያቄ አነሱ። የሶማሌ ኮንግረንስ መሪ ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ አክለው “በጋሪ ብቻ አይኬድም። ፈረስ ያስፈልጋል። ፈረሱ የምንከተለው ርዕዮተ ዓለም ነው” በማለት አቶ አባይ ያነሱትን ጥያቄ አጎሉ።

አቶ ነዓምን በቁጣ ድምጽ “እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ይነሳል፤ ከዚህ በላይ የሚያሳስቡ ጉዳዮች አሉበን። ስለ ኤርትራ መንግስት ማንሳት አያስፈልግም” አሉና ጥያቄውን አበሻቀጡት። አቶ ገዱ ነዓምንን ተከትለው “ህብረቱ ጊዜያዊ ነው” በማለት ለማጀብ ሞከሩ።
ይህ ሁለት ሰዓት የፈጀው የድምጽ መረጃ እንደሚያመልክተው በብዛት የሚናገሩት አቶ ነዓምን ናቸው። አቶ ነዓምን በይፋ ከሻዕቢያ ውክልና ያላቸው መሆኑን በግልጽ በሚያሳይ መልኩ መመሪያና አቅጣጫ እየሰጡ ስብሰባውን ለመምራት ቢሞክሩም ዶክተር ኢስማኤል “ ከአባይ ጋር እስማማለሁ” በማለት ነዓምንን ወጥረው ያዙ። “ኢትዮጵያ ሉዐላዊ አገራችን ናት” ካሉ በሁዋላ በዚህ ረገድ የአገርን ክብር መጠበቅና ሉዐላዊ ክብሯን መስጠበቅ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አወሱ፤ አክለውም “ከመንግስት ጋር ችግር አለ ብለን እንዴት ከኤርትራ ወይም ሌላ አገር ጋር ሆነን ኢትዮጵያን እንወጋለን፤ ይህ አይዋጥልኝም” በማለት ነዓምንን ሞገቱ፤
ይህን ጊዜ ነዓምንን ለመርዳት አቶ ገዱ “ኤርትራ አገራችን ናት” በማለት ላነሱት፣ ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ “ኤርትራ አገራችን ከሆነች ሶማሊላንድም አገራችን ናት። ጅቡቲም ግዛታችን ናት” በማለት ሞገቱ።
ይህኔ ነዓምን በስጨት በማለት ስለ ኤርትራ ማንሳት እንደማያስፈልግ ልክ አቶ ያሬድ እንዳሉት ዓይነት ንግግር ሲናገሩ፣ “ከምትናደድ ኢሳያስ እንዳለው ለምን አራቱን የስድብ ቃላቶች አትጠቀምም” በማለት ዶክተሩ ምላሽ ሰጡ።
ለወትሮው ብዙ በመናገር የሚታወቁት ልደቱ አያሌው እጃቸውን በአፋቸው በመጫን ያጠናቀቁት ስብሰባ አምስት ሰዎችን መርጦ ይፋ አደረገ።
አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ ጃዋር መሐመድ / በሌሉበት የተመረጡ ናቸው። አቶ ጃዋር ሁለቱንም ስብሰባ የቀሩት ከፍተኛ ወቅሳ ስለተሰነዘረባቸው እንደሆነ ገልጸን መጻፋችን ይታወሳል/ ፣ አቶ ያሬድ ኃ/ማሪያም፣ ዶክተር ኢስማኤል/ አልፈልግም ብለው ነበር/ አቶ ኦባንግን በመምረጥ በአቶ ነዓምን አማካይነት በተነሱ የልዩነት ጥያቄዎች ላይ ስምምነት ሳይደረስ ተቋጭቷል።
ከሚያራምዱት የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነታቸው አንጻር የሻዕቢያን መንግስት ወንጀልና ግፍ እንዴት እንደሚመከቱት የተሞገቱት አቶ ያሬድ መልስ ሳይሰጡ ዝምታን መርጠዋል። ምርጫው ላይ በገቡበት ወቅት እሳቸው፣ አቶ ገዱ፣ አቶ ልደቱና አቶ ነዓምን ብዙ ስራ እንዳለባቸው በመግለጽ የኃይል አሰላለፉን ሳያስቡት ይፋ አድርገዋል። ባለፈው ሳምንት “በአሜሪካና ሎንዶን ሰልፍ ላማድረግ አስቻይ ሁኔታ የለም” አቶ ነዓምን መናገራቸው ጠቅሰን ከቪዲዮ ማስረጃ ጋር ማተማችን አይዘነጋም።
አቶ ነዓምንና አቶ ገዱም ከአምስቱ የኮሚቴ አባላት ምርጫ በተደራራቢ ስራዎች ምክንያት ራሳቸውን አግልለዋል። አቶ ነዓምን የኤርትራ ወኪል ሆነው ሲንቀሳቀሱ ሶስት የሚታወቁ በኢትዮጵያዊያን ስም የሚጠሩ ድርጅቶችን እንደሚመሩ ራሳቸው አመልክተዋል። አቶ ነዓምን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለመሆን ጠይቀው “አይሆንም” መባላቸው ይታወሳል። በብቃት፣ በባህሪና ባላቸው ውስልትና በኡጋንዳ፣ በአዲስ አበባ አርፈውባቸው በነበሩ ሆቴሎችና በሚኖሩበት አገር በሚፈጽሟቸው ተግባራት፣ እንዲሁም ባላቸው አቅም ለደረጃው እንደማይመጥኑ መንግስት ሳይሆን አጠገባቸው ያሉ ቢመክሯቸውም አሻፈረኝ ማለታቸውን በርካቶች ይናገራሉ። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በዚሁ በጥቅምና በስልጣን ጥያቄ ሳቢያ “ለምን ተገለልን” በሚል አኩርፈው መስመራቸውን የለወጡትን ዝርዝር ሪፖርት አቀናብረን ይፋ የማናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናስታውቃለን።
- “ኢትዮጵያ የራሷ ባህር በር አያስፈልጋትም”- የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማህበር ነዳጅ ማስገባት መቸገሩን ይፋ አደረገርየኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማህበር ነዳጅ ምርት ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሎጀስቲክ… Read more: “ኢትዮጵያ የራሷ ባህር በር አያስፈልጋትም”- የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማህበር ነዳጅ ማስገባት መቸገሩን ይፋ አደረገር
- መንግስት በተደጋጋሚ ጥቃት፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት በሚፈጽሙና የሰዎችን የመዘዋወር መብት በሚገድቡ ላይ በቂ የፀጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ተጠየቀ… ኮሚሽኑ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ የሰዎችን የመዘዋወር መብት… Read more: መንግስት በተደጋጋሚ ጥቃት፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት በሚፈጽሙና የሰዎችን የመዘዋወር መብት በሚገድቡ ላይ በቂ የፀጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ተጠየቀ
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393








