የአመጽ አደራጅ ግብርኃይል በአብይ አህመድ ጉዳይ ተለያየ፤ “ግምት ውስጥ ገብተናል፤ ሚዛን እንጠብቅ”

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – “በምንም ይሁን በምን ምርጫ መደረግ የለበትም” በሚል ህዝባዊ አመጽ ለማደራጀት የተቋቋመው ግብረኃይል በተለያዩ ጉዳዮች መግባባት ሳይችል መበተኑ ተገለጸ። ልዩነት ካስነሱት ነጥቦች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መሆናቸው ታውቋል።

የተለመዱት የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪዎች ከዲሲ በላኩት መረጃ፣ ልዩነቱ የተነሳው በትናንትናው ዕለት በተደረገ ስብሰባ ነው። ዶክተር ሚኒሊክ የተባሉ የግብረኃይሉ አባል፣ “Realstic እንሁን” በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ በማነጣጠር የሚደረገው ዘመቻ ፅብት ውስጥ እንደሚከት አመልክተዋል።

አቶ ነዓምን ዘለቀ በድንገት ጣልቃ ገብተው “ኖ ኖ …” ሲሉ ዶክተር ሚካኤል “ልጨርስ” በማለት ከወትሮው በተለየ አቶ ነዓምንን ስርዓት እንዲይዙ በማድረግ፣ “ይህን መንግስት አግላይ ነው ማለት ትክክል አይደለም። በዳታና በመረጃ ተደግፈን መተቸት አለብን። ስማቸውን እየጠራን በምንተቻቸው ተቋማት ውስጥ የሚሰሩት ባልደረቦቻችን ናቸው። ይታዘቡናል” በማለት ላነሱት አሳብ ምሳሌ አስከተሉ።

አቶ ልደቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ ውጪ እንደሆኑና ብዙ ለመናገር እንደሚቸገሩ አመልክተው በተሳተፉበት ስብሰባ የአምክንዮ ጥያቄ በማንሳት ሃሳባቸውን የቀጠሉት ዶክተር ሚካኤል፣ “የኢትዮጵያ አየር መንገድን ብንወስደ 54% አማራ፣ 15% ትግሬ፣ 14% ኦሮሞ እና የተቀረው ሌሎች ብሄሮች አሉበት፣ ይህን ተቋም ጠቅሰን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አግላይ ናቸው ስንል እዛው ያሉት ሰራተኞች ይታዘቡናል” ብለዋል። አክለውም “ይህ እኔ የፈጠርኩት ሳይሆን የተቀመጠ ዳታ ነው። በዚህ ማመን አለብን”

ከዚህ ቀደም በተደረጉ ስብሰባዎችና የፕሮፓጋንዳ የሁለት ወር ዕቅድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያነጣጠሩ ዘመቻዎች እንዲሰሩ፣ ሚዲያዎችና ተናጋሪዎች እንዲሁም የመናገሪያ ማንዋል ተሰርቶ እንደነበር ምንጮቻችንን ጠቀሰን መዘገባችን ይታወሳል። የዲሲ ተባባሪያችን አቶ ነዓመንን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኤርትራ ለህወሃት ቁልፍ ሰዎች አጭር ቀነ ገደብ ያለው የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለመስጠት የወሰነችውን ውሳኔ መልሳ መያዟ ተሰማ

አዲስ ሪፖርተር - የኤርትራ መንግስት ለህወሃት አመራሮችና ከፈተኛ ወታደራዊ...

አሜሪካ እና ከኢትዮጵያ ጋር “ቋሚ ማዕቀፍ” የተባለ ስምምነት ተፈራረሙ፤

ዲስ ሪፖርተር - የአሜርካና የኢትዮጵያ አዲሱ ስምምነት "ቋሚ ማዕቀፍ"...

በግብጽ አስተባባሪነት ከሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ሱዳን ጋር ጥምረት የፈጠሩ በዲሲና ሎንዶን [ዳስ ይጥላሉ] ተባለ፤

“አሳቡ አገዛዙን ማውገዝ፣ ሕዝብን በጋራ ማነሳሳት እና አመጽ ማቀጣጠል...