አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | መቀመጫውን በፈረንሳይ ስትራስቡርግ ያደረገው የአውሮፓ ፓርላማ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. በኤርትራ ውስጥ እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የተመለከተ ጠንካራ የውሳኔ ሐሳብ በሰፊ ድምፅ አጽድቋል። የፓርላማው አባላት ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል አነስተኛ ተቃውሞና ድምጽ አልባነት ያጸደቁ sihon The resolution was adopted by 529 votes in favour, 2 against and 25 abstentions. ፣ በአገሪቱ ያለውን ሰብአዊ ሁኔታ አስመልክቶ ገለልተኛና ነፃ ምርመራ እንዲካሄድ በግልጽ ጠይቀዋል።
የውሳኔ ሐሳቡ ዋና ትኩረት ያደረገው ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል በሚባሉ የኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ እንዲጣል በማሳሰብ ላይ ነው። የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ይህ ዓይነቱ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እርምጃ መወሰዱ አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ፣ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት አገልግሎትም ከኤርትራ መንግሥትና ባለሥልጣናት ጋር በሚያደርጋቸው ማናቸውም ግንኙነቶች የሰብአዊ መብቶች መከበርን እንደ ዋና ቅድመ-ሁኔታ እንዲይዝ ጥሪ አቅርበዋል።
በጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የኤርትራ ባለሥልጣናት ለበርካታ ዓመታት በጋዜጠኞች፣ በፖለቲካ ተቃዋሚዎች፣ በሃይማኖት መሪዎችና በተራ ሲቪል ዜጎች ላይ ሲፈጸሙ ቆይተዋል የተባሉ ስልታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና አዋራጅ አያያዞች በጽኑ ተወግዘዋል። ፓርላማው በአገሪቱ ውስጥ የሐሳብ፣ የመናገርና የመደራጀት ነፃነቶች መታፈናቸውን እንዲሁም ዜጎች ያለፍርድ ብይንና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የሚቆዩበት አሠራር አሳሳቢ መሆኑን አመላክቷል።
በተጨማሪም የአውሮፓ ፓርላማ አባላት በኤርትራ በእስር ላይ የሚገኙ ሁሉም የሕሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ-ሁኔታና በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። መሠረታዊ ሰብአዊ ነፃነቶች እንዲከበሩ፣ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና የፍትሕ ሥርዓቱ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ እንዲሠራ ጥሪው አካቷል።
ይህ የኤርትራን ጉዳይ የሚመለከተው ውሳኔ የአውሮፓ ፓርላማ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመከታተል በዚሁ ዕለት ካሳለፋቸው ሰፋፊ ዲፕሎማሲያዊ ውሳኔዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ፓርላማው ከዚህ ጎን ለጎን የጆርጂያን እና የማካውን የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች የሚመለከቱ ሌሎች የውሳኔ ሐሳቦችንም አጽድቆ ማሳለፉ ተገልጿል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






