የ”ግራጫ ጦርነት(Gray Zone Warfare)” ዘመቻ፤ “ኦሮሚያ ብልጽግናን አፍርሱ”

Date:

አዲስ ሪፖርተር –  “ግራጫ ጦርነት (Gray Zone Warfare) ይህ ስውር የጦርነት ዘዴ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት በቀጥታ ስጋት የሆኑ በርካታ የጥቃት አይነቶችን ያጠቃልላል። ከእነዚህም መካከል፣ በግለሰብ፣ ተቋም እና ማኅበረሰብ ላይ ዒላማ አድርጎ ሚካሄድ የስነ-ልቦና ጦርነት፣ የሀሰት መረጃዎችን እና የጥላቻ ንግግሮችን በማሰራጨት በመንግስትና በሕዝብ መካከል ያለውን መተማመን መሸርሸር ዋነኛው መገለጫው ነው።” ይላሉ ቀድም ባሉት ጊዜያት በሉእላ ጉዳይ አዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኮሙኒኬሽን ባለሙያ፤ ይህ አደገኛ ጦርነት ከመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ደካማነት ጋር ተዳምሮ አሳሳቢ እንደሚሆንም ባለሙያው ጠቁመው ነበር።

“ይህንን ዘመናዊና ስውር የጦርነት ስልት ተረድቶ በንቃት መዘጋጀት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ እነዚህን ከቀዝቃዛው ጦርነት የተወረሱ እና አዲስ የተፈጠሩ ስጋቶችን በትብብር እና በብልህነት በመመከት፣ ብሔራዊ ጥቅሟንና የሕዝቧን ሰላም ማስከበር የሁላችንም የቤት ሥራ መሆን አለበት። እዛም እዚህም የምንሰማቸው መርዶዎች የዚህ በሽታ ጅማሮ ሊሆኑ ይቻላሉና ዘመኑን በጥንቃቄ እንመርመር” በማለት አንድ ሰሞን ተጀመሮ የነበረውን “እኔንም ብሎኝ ነበር” ዘመቻ ተንተርሰው እኚሁ ባለሙያ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

አሁን ላይ ባለው መረጃ ተረኞቹ የኦሮሞ ባለስልጣናትና የተመረጡ ባለሃብቶችን በዘመቻ ማጥቃት ሲሆን በዋናናትይ የተያዘው መመሪያ “ኦሮሚያ ብልጽግናን አፍርሱ” የሚል ነው። ይህን መመሪያ እንዲያስፈጽሙ የተመለመሉት አዳዲስ የኦሮሞ ተወላጆች ሳይሆኑ የሚታወቁ እንደሆኑ ዜናውን ያደረሰን ተባባሪያችን አመልክቷል።

የውጭ ሚዲያዎች እንደ ስትራቴጂያዊ መሳሪያ – የቀዝቃዛው ጦርነት ውርስ – VOA, BBC, DW እና “ኢትዮጵያዊያን” ወኪሎቻቸው

በኦሮሚያ ሕዝቡ ለአመጽ ተባባሪ አለመሆኑ በውጭ ያሉትን የተቃዋሚ ኃይሎችና እነሱኑ ከጀርባ ሆነው የሚመሩትን ቡድኖች እረፍት ነስቷል። መንግስትን ለመገልበጥ የሚደረገው ትግል ኦሮሚያ ላይ እዚህ ግባ ሊባል የሚችል ትርጉም አለማሳየቱና ሕዝቡም ለነውጥ ጀርባውን መስጠቱ ሊቀየር የሚገባው ተግዳሮት እንደሆነ በመገምገሙ ነው አዲስ ዕቅድ የተነደፈው።

በግለሰብ፣ ተቋም እና ማኅበረሰብ ላይ ዒላማ አድርጎ ሚካሄድ የስነ-ልቦና ጦርነት፣ የሀሰት መረጃዎችን እና የጥላቻ ንግግሮችን በማሰራጨት በመንግስትና በሕዝብ መካከል ያለውን መተማመን መሸርሸርን ዋንኛ ዒላማው ያደረገው ይህ የጥቃት ዘመቻ በኦሮሚያ ላይ እንዲጀመር ጥብቅ አቅጣጫ ነው የተቀመጠው።

ዶክተር ደብርጽዮን የሚመሩት በትግራይ የተቋቋመ ኮማንድ ፖስት ከሰራዊት አመራሮች ጋር በመሆን ያደርገውን ስብሰባ መረጃ በማጣቀስ አዲስ ሪፖርተር የትህነግን አጠቃላይ ግምገማ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል። በዚሁ ግምገማ ኦሮሚያን በተመለከተ “ከልሂቃኑ ጋር ተስማምተናል” የሚል ሃሳብ ቀርቦ ነበር።

እነ አቶ ስብሃት ነጋ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ከእነ ጃዋር ጋር በመገናኘት ሲመክሩበት በነበረው የሽግግር መንግስት ሰነድ ጎን ለጎን “አጥፍተናል። ኦሮሚያን በድለናል። ከአሁን በኋላ እንደ በፊቱ አይሆንም አብረን እንሰራለን” በማለት ለኦፌኮ ሰዎች መናገራቸውን የጠቀሱ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት፣ አሁን ተጀመረ የተባለው ግንኙነት አዲስ ሳይሆን እስር ቤት ከዞን አራት እስከ ዋይት ሃውስ የነበረው የህቡዕ ጥምረት ቀጣይ ነው።

በቅርቡ በመንግስት ቴሌቪዝን ቃለ መጠይቅ አድርገው የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ “ጃዋር ከሸኖ እንዳታልፉ” ይለን ነበር ሲሉ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ የትህነግ ከፍተኛ አመራሮችና እነ ጃዋር ያደርጉ የነበረውን ግንኙነት ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም። እሳቸው ከመናገራቸው በፊትም አዲስ ሪፖርተር ባደረገቸው ማጣራት ከዋይት ሃውስ ወደ ዞን አራት በሚደረግ ምልልስ ከእነ ጃዋር ውይይት ያደረግ ነበር። በህክምና ባለሙያዎች፣ እውስጥ ባሉ ተባባሪዎች ስልክ እየገባ ትግራይና ውጪ አገር ድረስ በመደዋወል ግንኙነት ይደረግ ነበር።

ድብረጽዮን ለሰራዊት አዛዦች ኦሮሚያ ላይ በፍጥነት መንግስት አፍርሶ አዲስ የመትከል ስራ እንደሚሰራ ሲያስታውቁ ይህ የቀደመው አሰራር መጀመሩን ማብሰራቸው እንደሆነ ታውቋል። ስብሰባውን ከተካፈሉ መረጃ የሚያገኙ ዝርዝር ጉዳዩን ባይናገሩም፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ከአቶ ልደቱ አያሌው አብሮነት ራሳቸውን ያገለሉት ለዚሁ ሲባል ነው። ከእሳቸው በተጨማሪ ጃዋር መሐመድ ከትህነግ ሰዎች እንደ አዲስ አብሮ መስራት መጀመሩ ተመልክቷል። የሰሞኑ የጃዋር መሐመድ እንቅስቃሴም ይህንኑ መረጃ የሚያጠናክር ሆኖ ተወስዷል።

/ ውድ አንባቢያን አዲስ ሪፖርተር ይህን ከአሜሪካ እስር እስር ቤት ዘልቆ ጃዋር የተስማማበትን የሽግግር መንግስት ሰነድ ክፍል ሁለት በመጪው ቅዳሜ በዩቲዩብ ገጻችን እንደምናቀርብ ከወዲሁ እናስታውቃለን/

ዕቅዱ ይህ ቢሆንም፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይህ ነው የሚባል የተቃውሞ እንቅስቃሴ አለመኖሩ፣ ሕዝቡም ለአመጽና ለረብሻ ጀርባውን መስጠቱ ከታሰበው መንግስት የመገልበጥ ትልም ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ አዳዲስ ስልቶች ተነድፈዋል። 

ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ከትህነግ የበላይ አመራሮች ጋር በመስማማት ሁሉንም ብሄሮች ያካተተ አዲስ ጥምረት ለመፍጠር የአቶ ልደቱ አያሌውን አብሮነት ጥሎ ከመውጣቱ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ተመክቷል። ይህ እንዲሆን የተፈለገው የኦሮሞ ልሂቃኖች ጃዋርን ጨምሮ በብዛት የፋኖና የትህነግ አስተባባሪና ደጋፊዎች ጋር አብረው መታየታቸው ድርጅቶቹና ሰዎቹ ኦሮሞ ላይ ካላቸው አቋም፣ ከሚያራምዱት የተሳሳተ ፖለቲካ አንጻር ተቃውሞ ስለገጠማቸው እንደሆነ ታውቋል። በክህደት የተፈረጁም አሉ። በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ፍላጎት ያላቸው ሳይቀር አሁን ትግሉ እየሄደ ያለበት አግባብና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ እየታየ ያለው መማገጥ እንዳላስደሰታቸው እየገለጹ ነው።

በተለያዩ ወቅቶች የኦሮሚያ ክልልን መዋቅርን ለመሰነጣጠቅ ሙከራ ይደረግ እንደነበር። የአቶ ታዬ ደንደአና የጃዋ ፍቅርም መነሻ ምክንያቱ ይህ እንደሆነ የሚያመለክቱ እንደሚሉት፣ አዲስ በሚጀመረው የኦሮሞ ህዝብን ቁጣ ለማነሳሳት በኦሮሚያ አመራሮች መካከል ልዩነት እንዲፈጠር ይደረጋል።

የአቶ ልደቱን አብሮነት ጥለው እንዲወጡና ከፕሮፌሰሩ አዲስ ስብሰብ ጋር እንዲቀልቀሉ ከተጠይቁ መካከል ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ መረጃ የሰጡ እንዳሉት የኦሮሚያን ቁልፍ ሰዎችና ባለሃብቶች በደቦ የማቆሸሽ ስራ ለመጀመር ተወስኗል። ዘመቻው እስከ ቤተሰባቸው የሚዘለቅ እንደሆነ ተመልክቷል።

ከተለያዩ ቡድኖች ድጋፍ ያላቸውና ለጊዜው ህብረት የፈጠሩ ሚዲያዎች በመቀባበል በኦሮሚያ ባለስልጣናት ላይ በፈጠራ፣ ለማስመሰያ ይረዱ ዘንዳ የቀደሙ ጉዳዮችን በማንሳት የስም ማጥፋት ዘመቻ ይከፈትባቸዋል። በተመሳሳይ ባለስልጣናቱን በወንጀል፣ በሙስና፣ ስልጣንን አለ አገባብ በመጠቀም፣ በግድያ፣ በአፈና፣ እንዲሁም ወደፊት “ይህን ለመስራት አቅደዋል” በሚልና እርስ በራስ መጠራጠር እንዲፈጥሩ በሰላም ወቅት የነበሩ ግንኙነቶችንና፣ በወቅቱ ነገሮች ለማብረድ ሲባል የተደረጉ ውይይቶችን በማንሳት ተከታታይ ዘመቻ ይከፈትባቸዋል።

በተለይም በተለያዩ ወቅቶች በክልሉ ውስጥ የተደረጉ የመሰነጣጠቅና መሃል የመግባት ሙከራ ያከሸፉና ስርዓቱን ያረጉ፣ ጫካ ያለውን ትልቁን የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ወደ ሰላም ለማስገባት ትልቁን ሚና የተጫወቱ የክልሉ ታማኝ ባለስልጣናት አስፈጻሚዎቻቸው የዚህ ዘመቻ ዒላማ እንደሆኑ አዲስ ሪፖርተር በስም ዝርዝር አግታለች።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ክልሉ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጣ ሰፊ ስራ በመስራት የሚታወቁ ባለሃብቶችና ባለሙያዎች፣ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የሰሩ፣ የወጣቶች አደረጃጀቶች ላይም ተመሳሳይ ዘመቻ እንደሚከፈት ታውቋል። ከዘመቻው ጎን ለጎን ሕዝብ ብሶት ውስጥ እንዲገባ፣ እንዲማረር ለማድረግ ለመስማት የሚከብዱ ታሪኮችን የሚያቀርቡ ምስክሮች ተዘጋጅተዋል። እነዚህ ክፍሎች ለጆሮ የሚከብድ ቃለ ምልልስ በስልክ እንዲሰጡ እየተደረገ ጎንለጎን በዋናናት የሚጠቁትን ወገኖች በማቅረብ ህዝብ አመኔታውን እንዲያጣባቸው የንጽጽር ዘገባ ይሰራል።

የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ይህንኑ እንዲሰራ ከታዘዘው የዩቲዩብ አምደኛ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው “እኔንም ብሎኝ ነበር” የሚለው ባለፈው የተጀመረው ስልት ብዙም ስላላስኬደ በደልን በሚያሳዝንና ሰሚዎችን በሚያስቆጣ መልኩ ማቅረብ አዲሱ ስልት ነው። ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ተቋማት ያሉ ተባባሪዎችን፣ በገንዘብ የሚደለሉ ሰዎችን በመጠቀም የተቋማትን መረጃ ለዚሁ ቅስቀሳ ለማዋል መታሰቡ ታውቋል።

በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ሚዲያዎችም አጀንዳ የማዘጋጀትና የመትከል ስራዎች እንደሚሰሩ ተባባሪያችን አመልክቷል። ተባባሪያችን ከስፍራው የሰማውን ጠቅሶ እንዳለው አዲስ አበባ ያሉ የፌደራል ባለስልጣናትን ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ በሆነ የተመዘገቡ ሚዲያዎች አማካይነት መረጃ እየተጠየቁ ለተፈለገው ዓላማ እንዲውል ይደረጋል። በዚህም የባልስልጣኑ ንግግር እየተቆረጠ ለአዲስ ዘመቻ ማጀቢያ ይደረጋል።

ከፍተኛ አመራሮችንና የክልሉን የኮሙኒኬሽ አገልግሎት ኃላፊ ለማነጋገር ስልክ ብንደውልም ባለመሳካቱ ማካተት አልቻልንም። የኦሮሚያ ክልልም መረጃ በመስጠት ረገድ ሊያብብበት እንደሚገባ አዲስ ሪፖርተር በዚህ አጋታሚ ለመጠቆም ትወዳለች። ኦሮሚያ ከተበጠበጠ ለውጥ ሊመጣ አይችልም በሚል ስለታቀደው አዲስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አስተያየት የጠየቅናቸው የኦሮሚያ መካከለኛ አመራር፣ “ኦሮሚያ ውስጥ ሕዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ አይሳሳትም” ብለዋል።

“እንደቀድሞ በስካር ኮምባይነሩን አቃጥሎ፣ የውሃ መሳቢያ ሞተሩን ሰባብሮ፣ ትራክተሩን ሰባብሮ፣ ህንጻ አውድሞ፣ መንገድ ቆፍሮ የተጠቀሱትን ቡድኖች ፍላጎት ማብረጃ ወጣት ካገኙ ይሞክሩ” ያሉት የመካከለኛው አመራር፣ “እስከዛሬ ምን ያላሉት አለና አዲስ ነገር ይጠበቃል? በማለት በሰሙት ዕቅድ አለመገረማቸውን አመልክተዋል። አክለውም “በራሳችን በኩል መስራት የሚገባንን መስራት ግድ ነው፤ ከህዝብ ጋር ኮንትራት አድሰን እንድንኖር የሚያደርገንም እሱ ነው። መልካም አስተዳደርና ሌብነት ላይ ጥብቅ መሆን አለብን” ብለዋል።

አዲስ ሪፖርተር ስምንት የሚጠጉ በስም ከሚታወቁ ፖለቲከኞች ባገኘችው መረጃ መሰረት ከመንግስት ሚዲያና በግል ተመዝግበው ከሚሰሩ የድረ ገጽ አውዶች እንደሆነ በመግለጽ መረጃ መጠየቅ የተለመደ ነው። የሚዲያዎቹን ስም ጠቅሰው ቃለ ምልልስ መስጠታቸውን የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች፣ የሰጡት መረጃ ችራሹኑ ባላነጋገራቸው ሚዲያ ሲዘገብ መስማታቸውን አመልክተዋል” ቃለ ምልልሴን ባልተናገርኩበት ሚዲያ ሳየው ደነገጥኩ” ሲሉ ገጠመኛቸውን በመገረም የተናገሩ አሉ። እነዚህ ወገኖች ብቻ ሳይሆኑ የመንግስት ባለስልጣናትም በተመሳሳይ መረጃ እየተጠየቁ የሰጡት መረጃ “ምንጮች” በሚል ባላገኟቸው ሚዲያዎች እንደሚዘገብ አዲስ ሪፖርተር ሰምታለች።

አዲሱ ዘመቻ ይህን አግባብ የሚከተል እንደሆነ ተባባሪያችን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የሰማውን ጠቅሶ ዘገቧል። ታዋቂ ሚዲያዎች እንደ ግብአት እንዲጠቀሙበት ታስቦ ፈቃድ ባላቸው የግልና የመንግስት ሚዲያዎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች የፌደራልና መንግስትና የክልሉን ባለስልጣናት ቃለ ምልልስ እያደረጉ ወይም መረጃ እየጠይቁ ወደ ውጭ በሽያጭ እንዲያቀርቡ እንደሚደረግ አመልክቷል። የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ይህን አስመልክቶ የሚያውቀው እንዳለ ለመጠይቅ ሞክረን “ተገምግማችሁ ስራችሁ ከተለየ በኋላ ነው መረጃ የሚሰጣችሁ” ተብለናል።

የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ናትናኤል ጋር በእጅና በውስጥ መስመር ስልካቸው በተደጋጋሚ ልናገኛቸው ብንሞክርም ሊያናግሩን አልፈቀዱም። በተለይ ጉዳዩ የሚመለከተው እሳቸውን በመሆኑ በአካል ቢሯቸው ድርሰ በመሄድ በተለያዩ ጉዳዮች ማብራሪያ እንዲሰጡን ብንሞክርም አልተሳካም። አቶ ናትናዔል ቀደም ሲል ለሚዲያ ቅርብ የሆኑና ከሚዲያ ጋር አብረው ይሰሩ የነበሩ እንደመሆናቸው መረጃ ለመስጠት ለዚያውም በሚመለታቸው ጉዳይ ላይ ዳተኛ መሆናቸው አግባብ እንዳልሆነ አዲስ ሪፖርተር ለመጠቆም ይወዳል። በቀጣይም እሳቸውን በማግኘት መረጃዎቹን በማጥራት አዲስ ሪፖርተር በዚሁ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ እንደምናቀርብ ከወዲሁ እናስታውቃለን።

መንግስት በቅርቡ መረጃ መስጥትን የሚያስገድድ መመሪያ ቢያወጣም በአብዛኛው ኃላፊዎች፣ የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤትን ጨምሮ ተግባራዊ አለማድረጋቸው ሚዲያዎችን ላልተመጣጠነ መረጃና ሚዛን ለሳት ድምዳሜ እንደሚዳርጋቸው ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ይገልጻሉ። በተለይም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽፈትቤት ዕለት ዕለት መረጃዎች ሙሉ ሆነው ህዝብ ዘንዳ እንዲደርሱ መስራት ሲገባው ቀን እየጠበቀ መግለጫ አውጪ፣ ስብሰባ አደራጅ፣ ሪባን ቆራጭ መሆኑ በበርካቶች ዘንዳ መንግስትን የሚያስወቅስ ተቋም እንደሆነ ይነገርበታል። የየተቋሙ የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤትም ከተወሰኑቱ በቀር መረጃ ለመስጠት ቁብ የሌላቸው፣ ስልካቸውን የማያነሱ፣ በቀጠሮ ምላሽ የማይሰጡ፣ በዋናነት የሚሰሩበት ክፍልና ሚናቸውን የዘነጉ መሆናቸው “የጠያቂ ያለህ” የሚያሰኝ እንደሆነ በርካቶች በምሬት ይናገራሉ። በዚሁ የተቋማቱ ስንፍና ሳቢያ ሕዝብ ለተሳሳተና ላልተመጣጠነ መረጃ እንደሚዳረግ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሊያቋቁሙ ሞክረው ያልተሳካላቸው ተቋም ቢኖር በዚሁ ዘርፍ ስራ ያለው እንደሆነ በተደጋጋሚ ይተቻል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ከድጡ ወደ ማጡ – የሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት ስጋት እና ተጠባቂው የቀጣናው መናወጥ

አዲስ ሪፖርተር - ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ሰሞኑን ባወጣው...

በሱዳን ጦርነት ብሄራዊ ጥቅሙን አሳልፎ እየሰጠ ያለው ደናቁርት “ኢትዮጵያዊ ሊሕቅ” እና ተጨባጩ እውነታ

እነ ጀዋር መሃመድ እና መሰሎቹ የድንቁርና ጌቶች  መሃመድ ዳጋሎ...

“ጃዋር ለምን ከጀርባ ይደበቃል? እኛ እንደ እናንተ ከግብጽ ገንዘብ አናገኝም”

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምጽና እንዲነሳ የሚጠይቅ መግለጫ...