“ጃዋር አታሎናል። ጃዋር ከሰውነት እንዲወጡ ያደረጋቸው ነበሩ። ዛሬ ላይ ሆነን በከተማችን የሆነውን ስናስበው እንዝናለን። አብረውን ከኖሩ፣ ከሚወዱን፣ ከተዋለድናቸው ጋር ጦርነት እንድንገባ ተደርገን ክፉ ተግባር ተፈጽሟል። ያ የስህተት ዘመን አይደገምም። የሆነው ሁሉ ዛሬ ላይ ሲታሰብ አሳፋሪም አሳዛኝም ነው። የተሰማንን ስሜት በተከታታይ እንጽፋለን። ድጋሚ አንታለለም። የአማራ ወጣቶች ከእኛ ተማሩ። ሻሸመኔ ወድማ ነበር። አልተጠቀምንም። እኛን ያሳሳተው ጃዋር ዛሬ ወደ እናነት ዞሯላ። የፋኖ አመራሮች ጃዋር ነው መመሪያ የሚሰጠው ብለው ሲናገሩ ስንሰማ የዚህ ሰውዬ ማረፊያ የትም ነው አለን፤ ምክንያቱም ኦሮሞ ዞር በል ብሎታልና፤ ትናንት ስላልውም ሆነ ስለፈጸመው አንዳች ቁጭት የማይሰማው ጃዋር ፋልጎቱን ለማሳካት ሁሉንም ያደረጋል ”
ነጻ አስተያየት በጃዋር ተታለናል የሚሉ የሻሸመኔ ልጆችን ስሜትና በውቅቱ ሆኖ የነበረውን ጸያፍ ተግባራት ለሌሎች ለማስተማር በተከታታይ የበኩላችንን እንላለን። የጽሁፉ አዘጋጆች በሻሸመኔ በመምህርነት የምናገለግል ሁለት ጓደኛሞች ነን
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ “የአማራ ብሔርተኝነት ማነሳሳታችን ትልቁ ስኬታችን ነው”፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የምርጫውን ቀመር (ካልኩሌሽን ሠርቼዋለሁ)፣ ቁርአን ይዤ ዐቢይን ጅማ ላይ እንዳይመረጥ አደርገዋለሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት ነው ያለው – የዐቢይ እና የቄሮ መንግሥት፣ እኔ ከታሰርሁ ኦሮሚያ ድብልቅልቁ ይወጣል፣ የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ፣ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከትህነግ ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ እጅግ በርካቶች በግፍ እንዲጨፈጨፉ ያስደረገው የመለስ ዜናዊ አድናቂ ጃዋር አሁን ደግሞ “አልጸጸትም” የሚል መጽሐፍ በሁለት ቋንቋዎች በማውጣት “ጥሞናውን” ሰብሮ በግልጽ ተግብጽ ኤጀንትነቱን እያስመሰከረ ነው፤
ሲጀመር ጃዋር ለመጽሐፉ “አልጸጸትም” የሚል ርዕስ የመረጥበትን ምክንያት በወጉ ሊሞግቱት በሚችሉ ወገኖች ፊት ቀርቦ አልተናዘዘም። በባህሪው በሚነዳቸው ሚዲያዎች እየከፈለ በሚያስተዳድራቸው ባሮቹ ፊት እንጂ ሌሎች ዘነዳ ቀርቦ መተንፈስ የማይወደውና የሚፈራው ጃዋር ሚዲያ ላይ ያለው ጮሌነት ስለሚታውቀ “ለምን አፍንጫህን ይዘው እሚጠይቁህ ዘነዳ አልሄድክም” አይባልምና እንተወወ።
በከፍተኛ ደረጃ ተከታዮችና አባላቱን አስከትሎ፣ ከመንግሥት ባልተናነሰ በይፋ አገር ቤት ተቀምጦ ሲመራው የነበረውን ትግል ወደ አሰበበት የሥልጣን ማማ ላይ ሳያደርስ መቅረቱና የሠራውን ወንጀል እንደ ጽድቅ በመቁጠር ለመጽሐፉ “አልጸጸትም” የሚል ስም እንደሰጠ ይታመናል። በዚህ ምክንያት ጃዋር የፈጸመውንና ያስፈጸመውን ያደፈ ታሪኩን ወደኋላ መለስ ብሎ መመለከት አስፈላጊ ይሆናል። ለሱ ኩራት፣ ጽድቅና የማይጸጸትበት ገድሉ፣ የሌሎችን አንገት ያስደፋ፣ሕይወት ያስገበረ፣ ያፈናቀለ፣ ያሸማቀቀ፣ ንበታት አልባ ያደረገ እጅግ አሳፋሪ ታሪኩን ዳግም መቃኘት አግባብ የሚሆነው አሁን ላይ ከአቶ ነዓምን ዘለቀ ጋር ተዳብሎ ከሻዕቢያ የተሰጠውን ተልዕኮና ተሸክሞ የግብጽ ኤጀንትነቱን በገሃድ ሲያሳይ “አንተ ህሊና ሞራል የነጠፈብህ የርህራሄ መካን ብትሆንም፣ እኛ ህሊናም ሞራልም አለንና አንረሳም፤” ማለት አስፈላጊ ለማለት ነው። ዓቅም ሰጥቷችሁ የጃዋርን በከበሩ ሰዎች ደም የተጻፈ መጽሐፍ ላነበባችሁ ይህንን አጭር የግርጌ ማስታወሻ ተጋበሁ፤
ጃዋር የሚዲያ ሰው ነው፤ ትምህርቱም ሚዲያን የተመለከተ ነው፤ ስለዚህ በተቻለ መጠን ሚዲያው ላይ አለሁ በማለት መወያያ አጀንዳ መሆን የሁልጊዜ ምኞቱ ብቻ ሳይሆን ማስረጃ ሊጠቀስበት የሚችል ተግባሩም ጭምር ነው። የO-Pride አዘጋጅና የአልጃዚራ ዘጋቢ ከነበረው መሐመድ አዴሞ (Pride የሚለው ቃል ለግብረሰዶማውያን የሚውል ቃል በሆነበት ዘመን) ጋር ወዳጅነት የጀመረው ጃዋር ወደ ሚዲያ ለመምጣት የቻለው መሐመድ አዴሞ ከአልጃዚራ ጋር ያለውን ትሥሥር በመጠቀም ነበር። በዚህም ያለማቋረጥ “ተንታኝ” እየተባለ አልጃዚራን ቤቱ አደረገው። ቁማሩን ተጫወተበት። በኤጀንትነት የሚያገለግላቸው ምስሪዎች እጃቸው ረጅም በመሆኑ በዛም በዚህም እያለ አልጃዚራን ደነሰበት። ይህ ሁሉ ሲሆን ያልገባቸው “ጃዋርን አሳብ አለው” እያሉ ሲያጨበጭቡ የገባቸው ከጅምሩ ነከሱት።

በቀጣይ አንድ የኦሮሞ ሚዲያ እናቋቁም የሚለውን የሌሎችን ሃሳብ እንደ ጊንጥ ተጣበቀበት፤ ከዚያም ወደ ራሱ ጠልፎና እነ መሐመድ አዴሞ ተጠቅሞ “Oromo First” የሚል ዘመቻ በተለይ በሰሜን አሜሪካ በማካሄድ እጅግ በርካታ ብር በመሰብሰብ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ የተባለ ሚዲያ ከፈተ። ሰይፈ ነበልባሎች ፊት ሲነሱት በሌላኛው ጓሮ ኦ ኤም ኤንን ከፍቶ የፈጸመው ተገባሩ ለጃዋር ጠላቶች ብቻ ሳይሆን ለደጋፊቹም አስደንጋጭ የሆነ ተግባር ሆነ፤ አብረውት ሚዲያውን የከፈቱትን ቀስ በቀስ መነጠራቸውና ሚዲያውን የግሉ ንብረት አደረገው። ከዚያ አልፎም ሠራተኞቹን በሙሉ ቁጥጥር ሥር በማዋል፣ ስልካቸውን ጠልፎ በማዳመጥ፣ ምሥጢራቸውን እንደ ማስረጃ በመያዝ የግሉ ሎሌ አደረጋቸው።
ለግሉ መጥለፍና መጠቀም ካልቻለ ጃዋር ትግል በማበላሸት የሚወዳደረው የለም። “ድምጻችን ይሰማ” የሚለውንና በኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ አስደናቂ የሆነ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት የነበረውን የሙስሊም እንቅስቃሴ ያከሸፈው ጃዋር ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህ በብዙ መስዋዕትነት ቀስ እያለ የክርስቲያኑን ሕዝብ ድጋፍ እያገኘ የመጣና የመሠረተው መስተጋብር (ኔትዎርክ) እጅግ አስደናቂ የነበረ ትግል ጃዋር የሜንጫ ፖለቲካ ሰንቅሮበት ከጥቅም ውጪ አደረገው። ሙስሊም ወገኖች የተነሱበት ሰላማዊ አጀንዳ በላው።
ጃዋር ከሚዲያ ምሥረታ በፊት ከተወናቸው ቀዳሚው የድምጻችን ይሰማ የሙስሊም እንቅስቃሴን መቀላቀል ነው። ሙስሊምም ኦሮሞም ስለሆነ እንቅስቃሴውን መቀላቀል አልከበደውም። እንደ አሁኑ ቆዳው አልተላጠም ነበርና አሳታቸው።ዓላማው ሙስሊሙን የለውጥ እንቅስቃሴ ለውጤት ማድረስ ሳይሆን ትግሉን ቀልብሶ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ነበርና በማህበራዊ ሚዲያና በተሸወዱት ዘንዳ እነሱን ታኮ ነገሰበት።

እንዲህ ያለውን መስተጋብር ሲመኝ የነበረው ጃዋር ሙስሊሙን ያገዘ መስሎ እንቅስቃሴውን ተቀላቀለና ትልቅ ፋዎል ሠራ። የዛሬ አስራ ሁለት ዓመት አካባቢ ፈርስት ሒጅራ በጠራው ትልቅ ስብሰባ ላይ ጃዋር እሱ ባደገበት ቦታ ሙስሊም ያልሆነ በሜንጫ አንገቱ ይቀነጠስ እንደነበር በመናገር ተመሳሳይ ጥሪ አሁንም እንዲደረግ አወጀ። በውጤቱም የሙስሊም ትግል ቀዝቃዛ ውሃ ተደፋበት፤ ታላላቅ የሙስሊም መሪዎች እጅግ አዘኑ፤ አሁን ስም ጠቅሶ መናገሩ ባያስፈልግም በሚዲያ ላይ ያልወጣ ብዙ ነቀፋ አወረዱበት።
ጃዋር ግን ይህንን ከመናገሩ በፊት በዚያን ወቅት በየሚዲያው እየወጣ ትግሉ የሙስሊም ብቻ ሳይሆን የኦሮሞም ነው በማለት የክርስቲያን ኦሮሞዎችን ድጋፍ ለማግኘት ሲታትር ነበር። እንዲያውም ኦሮሞ እስከ ጎንደር ድረስ ነው ያለው፤ ሙስሊምም እንደዚያው፤ ስለዚህ የጎሣና የሃይማኖቱን ጥምረት ማፋፋም ያስፈልጋል ሲል በስፋት ተሰምቷል። አስልቶ በዋጠውና ብር በገፍ ባመረተበት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ በኩል “ደጋፊ ለማግኘት የብሔርና የሃይማኖት ቅሰቀሳ ተመራጭ ነው” ሲል አምልጦት ይሁን አውቆ በራሱ ላይ በቁሙ ተናዟል። ይህንኑ አባባሉን አዲስ አበባ ተቀምጠው ሃብትና ንብረቱን የሚያስተዳድሩ የሚዲያ አሸርጋጆች፣ በያዟቸው ባለስልጣናትና በሚያስተዳድሯቸው የጃዋርና የኔትወርኩ ንብረቶች /ወደፊት በስፋት ይቀርባል/ ፈራንካ እየዘሩ ያስተጋቡለት ጀመር።
ኢህአዴግ ምርጫ ሊያደርግና መሪ ሊሾም ባለበት ወቅት ላይ ዐቢይ አህመድ እንደሚመረጥ ግልጽ እየሆነ ሲመጣ ጃዋር ባይሳካለትም በዐቢይ ምትክ ለማ መገርሳ እንዲመረጥ ትልቅ ውስወሳ በሚዲያው አድርጓል። እንዲያውም በዚያን ወቀት በኦ.ኤም.ኤን. ላይ ከሕዝቅኤል ገቢሳ ጋር ሆኖ የፓርላማው ሕግ ተቀይሮ ለማ ከክልል ተመራጭነት ወደ ፌደራል ፓርላማ እንዲገባ መደረግ አለበት ብለው ብዙ ጥረት አድርገው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ለማን አንግሶ ለመጋለብ!!
ለውጥ መጥቶ ጃዋር ወደ አገር ሲመለስ ዋነኛ ዓላማው በወቅቱ አዲሱ አረጋ ይዞት የነበረውን የኦሮሚያ ገጠር አደረጃጀት ዋና ቢሮ መምራት ነበር። ዓላማው የገባቸው የኦህዴድ ሰዎች ሥልጣኑን ሲነፍጉት ነቀለ። በከፈተው ሚዲያና ይዞት በገባው ግማሽ ቢሊዮን ብር በርካታ የአገር ውስጥ የሚዲያ ቡድኖች ፈለፈለ። እነዚህም በአማርኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ፣ በአገው፣ ወዘተ የሚዘግቡና በእርሱ ድጎማ የሚደረግላቸው ነበሩ። እነዚህ አማራ ክልልን የሚበጣጥሱና ሲዳማን የሚበልቱ ነቀርሳ ሚዲያዎች ሲከፈቱ በዓላማ ነበር።

ጃዋር አልሞና አስቦ በከፈታቸው የሚዲያ አውታሮች የሚረጨው መርዝ ኢትዮጵያን አፈናት። ምድሪቱ በዘር ፖለቲካ ጦዘች። ሰዓት እየከፋፈለ አንዴ ቅማንት ሌላ ጊዜ ደግሞ ኤጀቶ እያለ አገርና ሕዝብን አወከ። የሲዳማ በደል እንዲወራ ያደርግና ሲዳማዎችን ከወላይታዎች ጋር ያባላ ጀመር። ከዚህ ሌላ ያለማቋረጥ ስለ አገውና ቅማንት ሕዝብ እንዲወራ፣ አጀንዳ እንዲሆን፣ ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን በኦኤምኤን እንዲሰራጭ እረፍት እስኪያጣ ደከመ። ከሚሴ ገብቶም ሁከት ነዛና አብረው ለዘመናት የኖሩ ወገኖችን እሳትና ጭድ አድርጎ አጫረሳቸው።
በአንድ ወቅት አገር ቤት የገባ ሰሞን በራሱ ሚዲያ ቀርቦ ስለ ለውጡ ብዙ ከተናገረ በኋላ በቀጣይ ስለሚሆነው ወይም መሆን ስለሚገባው ነገር የተናገረውን አሁን ደግሞ ቢሰማው ራሱ ጃዋር ይደነቃል። ቃል በቃል ያለው “አሁን ዐቢይ የሚመራው የሽግግር መንግሥት ነው … ማንም ያለ ምርጫ በሽግግር መንግሥት ስም ሥልጣን በአቋራጭ መሞከር አይችልም” ነበር ያለው።
ይህንን ሲል የነበረው ጃዋር ወዲያውኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት እንዳለ ሲናገር ቆየ፤ አንዱ አራት ኪሎ ያለው ሲሆን 2ኛው ደግሞ የቄሮ መንግሥት እንደሆነ አስታውቆ ራሱን ሾመ። የመደበኛው መሪ ዐቢይ ከሆነ የቄሮው ደግሞ ራሱ መሆኑ ነው። በዚሁ ጊዜ “ብንፈልግ አራት ኪሎን መቆጣጠር አያቅተንም” ሲል በገሃድ ገለጸ።

በዚህ ልክ የሥልጣን ጥማቱን በአደባባይ ሲናገር የነበረው ጃዋር የመጨረሻ የሚባለውን መተግበር ግድ ሲሆንበት በቅድሚያ የፖለቲካ ድርጅት መቀላቀል አስፈላጊ መሆኑን በመረዳቱ መረራ ጉዲናን ከነፓርቲው በበቀለ ገርባ አሻሻጭነት ጠቀም ባለ ብር ገዛው። በቆሎ ለሁለት እየጋጡ “ዛሬ አይንና ናጫ ሆነው ሊለያዩ፣ፍቅር እስከ ቀራኒዮ፣ ድል እስከ አራት ኪሎ” ተባብለው በስፖርቱ ቋንቋ ለጠቅላይ ተጫወተበት። ቀጥሎም የኦሮሞ ፓርቲዎች ውኅደት ብሎ የዳውድ ኢብሣን ኦነግ፣ የከማል ገልቹን ፓርቲ፣ የገዛውን ከኦፌኮንና ስምንት የሚደርሱ ድርጅቶች ለመጠቅለል ሌላ ድራማ ተወነ። “ጋዲሳ ኦሮሞ” ብሎ ለማን በመያዝ በሰራው ቀመር መሰረት ዳውድ የጥምረቱ መሪ ተብሎ አሾመ። የፊርማ ሥነሥርዓት ተደረገና አስጨበጨበ። ዳውድ ዲስኩር ሰጡ። በነጋታው ግን ጃዋር ዳውድን “እውነት መሰለህንዴ?” ማለት ሲጀምር ነገሩ የገባው ከማል ገልቹ ከውህደቱ ወጣ፣ በዚያው ሁሉም ጉዳይ ከጃዋር ዕቅድ ቀድሞ ፈራረሰ።
ጃዋር እየተገለባበጠ ያደረገው ሙከራው ሁሉ የእንቧይ ካብ እየሆነበት ሲመጣ የመጨረሻ መጨረሻውን ውሳኔ መተግበር ግድ ሆነበት። ሥልጣን እንዳሰበው በቀላሉ የሚያዝ እንዳልሆነ እንዲያውም በጣም እየራቀው እንደመጣ ሲያይ ኦፐሬሽን ሃጫሉን ተገበረ። ሃጫሉ ኦኤምኤን ላይ ወጥቶ የተናገረው እሱ ባልገመተው መንገድ ቀለበት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርገው ነበር። የሃጫሉ መገደል የሚቀሰቅሰው ቁጣ ለጃዋር የአራት ኪሎን በር ወለል ብሎ የተከፈተ እንዲመስለው አደረገ። ሃጫሉ ከተገደለ በኋላ በአስከሬኑ ላይ የተፈጸመው ድራማ እና ፖለቲካ ያለ ቅንብር፣ ያለ ዕቅድ ነው የሆነው የሚለውን የሚያምን የጃዋርን ማንነት የማያውቅ ወይም ፖለቲካ ያልገባው ነው። በተለይ ከግድያው በኋላ ጃዋር የያዛችውን ይዞ ቀጣና በመከፋፈል ሃዘን የደረሰባቸውን ቤተሰቦች አይን ባወጣ ደረጃ ሲያከናውን የነበረው ሁሉ ዛሬ ላይ ሲታሰብ ክብረ ነክነቱ ሰማይ ጠቀስ ነው። ለጃዋር እንዲህ ያለው ተግባር ጌጡ ነውና ዛሬም ድረስ ሳያፍር በዚሁ ምስኪን ፎቶና ስም ሊቆምር ይወዳል።
በወቅቱ በየቀጠና በተሰጠ ስምሪት አዲስ አበባ እንድትበጠበጥ የደረሰውን አስደንጋጭ ሃዘን ተንተርሶ ጃዋር ያዘጋጀው የትርምስ ሴራ ዕልቂት እንዲነሳ፣ አገሪቷ እንድትናወጥ በማድረግ የፈጸመው ተግባር ቢሳካ እሳቱ ዛሬ ድረስ የሚንቦገቦግ በሆነ ነበር። እዚህ ላይ አስተዋይ የሆኑት የሃጫሉ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማዶችና መላው የአምቦ ሕዝብ አንድ ቀን ታሪካቸው በወርቃማ ቀለም ይቀባል።

ከሃጫሉ ግድያ በፊት የቁማሩ ካርድ እያለቀበት ሲመጣ ጃዋር አንድ ድራማ ተውኖ ነበር። የኦሮሞ ወጣቶች እንዲነሱ ታፍኛለሁ፣ ታግቻለሁ፣ ብሎ አገር በማናወጥ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ፤ ንብረት ያወደመ እጅግ አሰቃቂ የግፍ ድራማ ተጫውቷል። ግን መንግሥትን ገልብጦ ሥልጣን ማማ ላይ መውጣት አልተሳካም። ይልቁኑ ከዚያች ቀን ጀምሮ በሩቅ ሸብ የተደረገበት ገመድ ጠበቀ። ገመዷ ጠብቃ ሳለ በሃጫሉ አስከሬን ሥር ቁማር ፈጸመ። አስከሬን ከቤተሰብ ነጥቆና አስነጥቆ በበር ከጀርባ ካሰለፋቸው ጋላቢዎች ጋር ሆኖ አዲስ አበባን በነውጥ ሊያበራይ የያዘው ዕቅድ እንደ ጭስ ተነነበት። የጠበቀውም ገመድ አነቀውና “ብዙ ዓመት ሳወራ ኖርኩ። እስኪ ላዳምጥ ብዬ ዝም ብዬ ተቀመጥኩ” ብሎ የሚናገር እንደበተ ልስልስ ሆኖ የወጣበት ማረሚያ ቤት ገባ።
ማረሚያ ቤት ሆኖ ሲሰራ የከረመውን ሴራ ወደፊት የምንመለስበት ቢሆንም፣ ለአሁኑ ማጠቃለያ ያህል ጃዋር እስር ቤት “ተቀየርኩ” ካለና ራሱን ኃይማኖተኛ ለማስመሰል ሃጂ ማድረጉን ካስታወቀ በሁዋላ፣ ሲሽኮረመም ቆይቶ በግፍና በንጹሃን ደም የተጨማለቀውን ማንነቱ “አልጸጸትም” በሚል ደምደም በሚል መጽሃፍ አጅሎ “አንብቡልኝ” አለ። ታዬ ደንደአ ጃዋርን እግር በእግር እየተከታተለ ሲከተከተው በነበረበት ወቅት፣ “የደም አበላ” ብሎት እንደ ነበር ማንሳት አግባብ ይሆናል።
ተጨልፎ በማያልቀው የጃዋር ግፍ፣ በሚጮሁ ንጹሃን ደምና ነብስ የተሞላውን መጸሐፍ በ“አልጸጸትም” ከፍኖ ሲያቀርብ አለማፈሩ ሞራል አልባና ርህራሄ የሚባል የነፍስያ ሚዛን የነጠፈበት ወፈፌ በመሆኑ ነው። ይህ የርህራሄ እንጥፍጣፊ የሌለው ወሮ በላ ከላይ በተባለው መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ነግሶ ስንቱን ይዞ እንደጠፋ ቤት ይቁጠረው። ከቅርብ ወራት ጀምሮ ከሻዕቢያ ዋና ወኪል ነአምን ዘለቀ ጋር ሆኖ የግብጽ ኤጀንትነቱን ይፋ በማውጣት በመናበብ ዘመቻ ጀምሯል። ይህ ደምና ግፍ የማይጠግብ የሉሲፈር ሽንት ኦሮሞ አልሰማም ሲለው፣ ከነአምን ጋር ሆኖ በሻዕቢያ በኩል የአማራ ክልል ቀውስን ሊደንስበት እየተንደረደር ነው። “ኦሮሞ ዞር በል” ሲል በመንዝ ካርድ “አንደኛ ኦሮሞነት” እያለ ሲዛበትበት በነበረው አማራ የአራት ኪሎ ጉዞ ሙከራ ላይ ነው። ይቀጥላል።
በጃዋር ተታለን የነበርን የሻሸመኔ ልጆች ነን
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






