“ጃዋር ለምን ከጀርባ ይደበቃል? እኛ እንደ እናንተ ከግብጽ ገንዘብ አናገኝም”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምጽና እንዲነሳ የሚጠይቅ መግለጫ የፊታችን ዓርብ እንዲሰጥ የቀረበው አሳብ ቢያከራክርም አቶ ልደቱ መግለጫው እንደሚሰጥ ገልጸው መግለጫ በተኑ። “ጃዋር ለምን ከጀርባ ይደበቃል? እኛ እንደ እናንተ ከግብጽ ገንዘብ አይሰጠንም” የሚል የከረረ ተቃውሞ ተሰነዘረ። 

በመግለጫቸው “ከጥቂት ቀናት በኋላ የግብረ-ሃይላችን ተዎካዮች ትዕይንተ-ህዝቦቹ መቸ እና እንዴት እንደሚካሄዱ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ለአገርና ለህዝብ ደህንነት ተቆርቋሪ የሆነ ዜጋ የመርሃ-ግብሮቹን ሂደት በአንክሮ እንዲከታተልና ተግባራዊ ተሳትፎ ለማድረግም ከወዲሁ የህሊና ዝግጅት እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን” ይላል አቶ ልደቱ ለአባላቱ የበተኑት መግለጫ ሲጠቃለል። 

አቶ ልደቱ መግለጫውን ረቡዕ ዕለት ከመበተናቸው በፊት ማክሰኞ በተደረገ የአብሮነት ቦርድ አመራር አባላት ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎች ጥያቄ አንስተው ነበር። በስብሰባው ላይ “ለምን ጃዋር ይደበቃል? ለምን ከጀርባ ሆኖ ይሰራል? ለምን ፊት ለፊት በስብሰባ አይገኝም?” የሚል ጥያቄ ከግብረኃይሉ አባላት ጥያቄ መነሳቱን አዲስ ሪፖርተር በማስረጃ አረጋግጣለች።

“እኛ እንደ እናንተ ከግብጽ ገንዘብ አንቀበለም” ያሉት ተሰብሳቢዎቹ፣ “እኛን ፊትለፊት በማድረግ የብሄር ማሟያ ማድረግ ተቀባይነት የለውም” ሲሉ አንዳቸው ለሌላኛው ድጋፍ ሰጥተዋል። 

የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሚባሉት የግብረኃይሉ አባል አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም፣ “ሶስቱ ግሩፖች ናቸው የሚረብሹን” በማለት ድጋፍ ሲሰጡ ተድምተዋል። “ሶስቱ” ያሉት የትግራይ፣ የአማራና ኦሮሞ ብሄር አባላት ሌሎችን እንደ መጠቀሚያ አድርገው በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ማስገባታቸው በመቃወም ድጋፋቸውን ሰጡ። 

ዶክተር ኢሳማኤል ጎርሴ በበኩላቸው “እዚህ የሚደረገው ስበሰባና እዚያ የሚደረገው ስብሰባ ልዩነቱ ምንድን ነው?” በማለት “እኛን እንደ ሶስተኛና ሁለተኛ ደረጃ እንታያለን። ለምን በዚህ መልኩ እንታያለን?” የሚል ጥያቄ አከሉና እንዲህ ያለው ሁለት ቦታ የመጫወት አዝማሚያ ሊቆም እንደሚገባ ጠቆሙ። አዲስ ሪፖርተር የደረሳት መረጃ እንደሚያመልክተው እሳቸው ይህን ሲናገሩ አቶ ኃይለማሪያም፣ የጋምቤላና ደቡብ ተወካይ የተባሉት ድጋፍ ይሰጡ ነበር። አቶ ልደቱ ዝምታን መርጠው ታይተዋል። 

ከጀርባ ሆነው ስብሰባ ያደርጋሉ የተባሉትና ሙሉ በሙሉ በውጭ ኃይሎች የሚደገፉትና የሚታዘዙት አቶ ነዓምን ዘለቀ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ፣ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም፣ እና የትጥቅ ትግሉን በማስተባበር የሚታወቁና አቶ ልደቱ አያሌው እንደሆኑ መረጃውን ያላኩት አመልክተዋል። 

አብሮነት በይፋ ባቋቋመው ግብርኃይል ውስጥ የብሄር ኮታ ስብጥር ለማሟላት የተካተቱት እንደሚሉት ከላይ የተዘረዘሩት ተሰብሳቢዎች ናቸው መመሪያ እኡየተቀበሉ የሚያሰራጩት። ይህ ግብረኃይል ለስም የተቋቋመ ነው። እኩል ሚና እንደሌላቸው ያመለከቱት ክፍሎች እንዳሉት የአለመግባባቱ መነሻም “ሚዲያ ላይ ውጡና መግለጫ ስጡ” መባሉ ላይ ነው። አደባባይ ወጥተው መግለጫ እንዲሰጡ ታስበው የተመለመሉ እንደሚመስላቸው ጠቅሰው ተቃውሞ ያሰሙት እነዚሁ የግብረኃይሉ አባላት በማክረራቸው አቶ ልደቱ መካከል ሲገቡ መርጃው ያሳያል። 

“እኔ፣ ነዓምንና አባይ እናነጋግረዋለን። ሃሙስ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ይመጣል” ሲል አቶ ልደቱ ጃዋርን በቡድን ለማነጋገር መፍትሄ ማስቀመጡን አስታወቀ። “ጃዋርም ፊት ለፊት ወጥቶ መግለጫ መስጠት አለበት” በሚል የቀረበውን የሌሎቹን ጥያቄ ማላሽ ለመስጠት ለሃሙስ የተቀጠረው ስብሰባ በስምምነት ከተቋጨ አቶ ልደቱ ቀደም ብለው ባሰራጩት መግለጫ መሰረት ዓርብ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። 

ሃሙስ በጋዜጣዊ መግለጫው ይዘት ላይም ውይይት የሚደረግ ሲሆን፣ መግለጫው በዋናነት ይህንን መንግስት እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል፣ የጠመንጃ ትግል ላይ ያሉትን እንዴት መደገፍ እንደሚቻልና በመላው አገሪቱ አመጽ እንዲቀጣጠል ስለማድረግ መሆኑ ታውቋል። 

ጃዋርም ሆነ ሌሎች የኦሮሞ ተወላጆች ከአብሮነት ጋር መጀመሪያ ሲታዩ ክፉኛ ተቃውሞ ተሰንዝሮባቸው ስለነበር ወዲያውኑ አብሮነትን ተለይተው በሲያትል ተመሳሳይ ሕዝብረት አቋቁመው፣ አብሮነትን ሙሉ በሙሉ ጥለው መውጥታቸው የሚታወስ ነው። የቀሩት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ብቻ ቢሆኑም እሳቸውም “መንገድም ይደክማል” በማለት ደብዳቤ ጽፈው ከአብሮነት መለየታቸውን፣ ይህንንም ያደረጉት ሌላ ኦሮሞ ብቻ የሚሳተፍበትና ሌሎች ብሔሮችን በስራቸው የሚያሳትፍ አዲስ አብሮነትን የሚመስል ማህበር ለማቋቋም እንደሆነ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። 

ከወራት ቆይታ በኃላ የትህነግና የሻዕቢያ ህብረት ገሃድ እየመጣ ሲሄድ፣ አቶ ጃዋር በመላው ኢትዮጵያ አመጽ ለማቀጣጠል በተቋቋመው አዲስ ከአብሮነት ውስጥ በተወለደው ግብረኃይል ውስጥ በስራ አስፈጻሚነት መመረጡ ተሰማ። 

አዲስ ሪፖርተር የስብሰባውን ቪዲዮ ይፋ በማድረግ በወቅቱ ዜናውን ስትዘግብ በተመሳሳይ ጃዋር ተቃውሞ ስለገጠመው “ከእነዚህ ጋር መስራት አይቻልም” በሚል ግብረኃይሉን እንደተወው አስታወቀ። ስብሰባ መገነቱን ብቻ ሳይሆን ስልክ የአቶ ልደቱን ስልክ ማንሳት አቆመ። 

አቶ ልደቱ ጃዋር ስልክ እንደማያነሳለት ጠቅሶ በስብሰባው ላይ ባስታወቀው መሰረት የትህነግ ተወካይ የሆኑ አንድ አባል እንዲያናግሩት ተደረገ። አዲስ ሪፖርተር ይህንን ዘገባ በዝርዝር ከሳምንት በሁዋላ አቅርባው እንደነበር አይዘነጋም። 

ጃዋር በስብሰባው መሳተፉን ያቁም እንጂ ከአቶ ነዓምን ጋር ቅርብ ሆኖ መስራቱን የግብረኃይሉ አባላት ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቀው ነበር። “ለምን ተደብቆ ከጀርባ ከሻዕቢያ ወኪሎች ጋር ይሰራል” የሚሉት የግብረኃይሉ አባላት፣ ከዛሬው የኃሃሙሱ ስብሰባ በኃላ አቋም ሊይዙ እንደሚችሉ አመልክተዋል። 

በተያዘው ዕቅድ መሰረት፣ በአሜሪካና አውሮፓ ታላላቅ ሰልፎችን ለማድረግ፣ በመላው አገሪቱ ህዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት ጥሪ ማድረግን ያካተተውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የሚቀመጡትን ለመወሰን ዛሬ ኀሙስ በዋሽንግቶን ሰዓት ረፋዱ ላይ በአራት ሰዓት ጃዋር ባለበት ስብሰባ ይካሄዳል። ጃዋር በስብሰባው ላይ ከተገኘ የሚይዘው የኦሮሚያን ክልል ስለሚሆን ክልሉን አመጽ እንዲንጠው ዓርብ በገሃድ ጥሪ ያቀርባል። አዲስ ሪፖርተር ዝርዝሩን በመያዝ ተጨማሪ መረጃ ታቀርባለች።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ከድጡ ወደ ማጡ – የሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት ስጋት እና ተጠባቂው የቀጣናው መናወጥ

አዲስ ሪፖርተር - ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ሰሞኑን ባወጣው...

በሱዳን ጦርነት ብሄራዊ ጥቅሙን አሳልፎ እየሰጠ ያለው ደናቁርት “ኢትዮጵያዊ ሊሕቅ” እና ተጨባጩ እውነታ

እነ ጀዋር መሃመድ እና መሰሎቹ የድንቁርና ጌቶች  መሃመድ ዳጋሎ...

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ መምጣት የቀይ ባህርን ጉዳይ ወደ ፍጻሜ እየመራው ስለመሆኑ ማሳያ

ከኤርዶጋን ጉብኝት ማግስት የእስራኤል ፕሬዝድንት ወደ አዲስ አባባ እንዳሚመጡ...