ጃዋር መሃመድ በውክልና የሚመራው ደም አፋሳሽ የአመፅ ጥሪ መግለጫ ማክሰኞ እንደሚሰጥ ታወቀ፤ “ሽፋኑ እምቢተኛነትና ሰላማዊ ትግል ነው” ተብሏል

Date:

አዲስ ሪፖርተር-  ጃዋር መሃመድ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ አቆጣጠር ረፋድ 4:00 ላይ በኢትዮጵያ፣ በተለይም በኦሮሚያ ክልል አዲስ የሕዝባዊ አመፅ እንዲቀሰቀስ ጥሪ ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ታወቀ።መግጫውን አቶ ልደቱ አያሌው በንባብ ይጀምሩታል። “ውጭ አገር ተቀምጠው አገር የማናወጥ ጥሪ ውስጥ አሉበት መባላችን ሃሰት ነው” ሲሉ ስማቸው ከአመጹ ጋር የተነሳ ፓርቲዎች ተግባሩን እንደሚያወግዙ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

አዲስ ሪፓርተር ከዲሲ የደረሳት መረጃ አጣቅሳ መግለጫው ዓርብ እንደሚሰጥ አመልክታ ነበር፤ ይሁን እንጂ ጃዋር መሐመድ በማክሰኞው ስብሰባ ባለመገኘቱና ፊት ለፊት ለመታየት የኦሮሞ ማህበረሰብን በመፍራቱ ሳቢያ በተፈጠረ ክርከር ማክሰኞ ዕለት የተደረገው ስብሰባ ለሃሙስ እንዲተላለፍ ተደርጎ ነበር።

ባለፈው ማክሰኞ “እናንት ከግብጽ ገንዘብ ትወስዳላችሁ። እኛ የለንበትም። ጃዋር ለምን በጓሮ ሆኖ ይሰራል። የግብረኃይሉ አባል እስከሆነ ድረስ በፊት ለፊት መግለጫው ላይ ሊገኝ ይገባዋል” በሚል ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። በዚሁ “እኛን እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ በማየት መጠቀም ይቁም” ሲሉ የአነስተኛ ክልል ተወካዮች ባሰሙት ቅሬታ መሰረት ቅሬታ መሰረት ጃዋርን በማነጋገር ሃሙስ ሌላ ስብሰባ ለማድረግ ቀጠሮ ተያዞ ነበር። እዚህ ላይ ዝርዝሩን ያንብቡ፤

በቀጠሮው መሰረት ጃዋር ሃሙስ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ፣ አቶ ልደቱ ያዘጋጀውን መግለጫ “እኔ በንግሊዝኛ አዘጋጀዋለሁ” ካለ በሁዋላ ለማክሰኞ በተያዘው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቶ ልደቱ የሚያነቡትን የዕለቱን የአመጽ ጥሪ ተንተርሶ ማብራሪያ እንደሚሰጥ አስታውቆ “ጉዞ አለብኝ” በማለት ከስብሰባው ወጥቷል። በዚሁ 30 ደቂቃ በፈጀ ስብሰባ ጃዋር አምስት ደቂቃ ብቻ ቆይቶ ጥያቄ ሲቀርበለት ሳይመልስ ተሰናብቷል።

የአብሮነት ሰብሳቢ አቶ ልደቱ ያደራጁት ይህ አመጽና ሰላማዊ ሰልፍ የሚያዘጋጅ ሰባት አባላት ያሉት ግብረኃይል፣ ከጀርባው በሀገር ውስጥ የትጥቅ ትግል እያካሄዱ ያሉ ቡድኖችን የሚደግፉና የሚያደራጁ እንደሚመሩት መረጃ አስደግፈው ተሰብሳቢዎቹ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል። እነዚሁ ወገኖች ደጋጋመው እንዳሉትና በአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ እንደተዘገበው እነሱ የተካተቱበት ግብረኃይል “በሰላማዊ ትግል ሽፋን አመጽን የሚደራጅ ቡድን ነው፤ዓላማው የትጥቅ ትግሉን በአመጽ ማገዝ ነው”

ከጀርባ ሆነው ከሻዕቢያና ከሌሎች የውጭ ኃይሎች ጋር ወኪል ሆነው የሚሰሩት አቶ ነዓምን እና አቶ ጃዋርን ጨምሮ አቶ ገዱ፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል፣ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም  እንዲሁም በሚዲያ አስተባባሪነት ስም የሚነቀሳቀሱ በመናበብ የሚመሩት ይህ ስብስብ የሚሳካለት ከሆነ ”በሰላማዊ ፖለቲካ እና በትጥቅ ትግል መካከል ያለውን የልዩነት መስመር የሚያደበዝዝ፣ በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ከዚህ ቀደም የታዩትን ዓይነት ደም አፋሳሽ ውጤት የሚያስከትል፣ አደገኛ ልምምድ የሚያስተምርና ጠባሳው የማይረሳ አሳዛኝ አሻራ ጥሎ የሚያልፍ እንደሆነ መረጃውን የሰሙ አስተያየት እየሰጡ ነው።  

በርካታ የዩቲዩብ ሚዲያዎች ይቀባበሉታል ተብሎ ዕቅድና በጀት የተያዘለት ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ ጃዋር መሃመድ ወደ ቀድሞው የ”አክቲቪዝም” እና የተቃውሞ አስተባባሪነት ሚና እየተመለሰ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ አሁን ላይ አብረውት የማይሰሩት ባልደረቦቹ አመልክተዋል።

ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት፣ ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የለውጥ ኃይል ባመቻቸው መዋቅር መሰረት በጃዋር መሃመድ አማካኝነት የሚተላለፉ ጥሪዎች በኦሮሚያና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የሕዝብ እንቅስቃሴን የመፍጠር አቅም እንደነበራቸው የሚያስታውሱ “ምን ሊፈጠር ነው ደግሞ” በሚል ስጋት ገብቷቸዋል።

“ጃዋር ያንን ወቅት በችኩልነትና ራሱ ብቻ በሚያውቀው ጉዳይ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። በሂደቱ ውስጥ ቢያንስ ይህ ትውልድ ሊረሳው የማይችል ሞት፣ ውድመት፣ ወንጀልና ክፋት በመፈጸሙ ጃዋር ወደፊት መምጣቱ ስጋት ሊሆን አይችልም” የሚሉ “በዘራቸው ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ፣ ንብረታቸውን የከሰሩ፣ በገነቡት ቤት መኖር የተከለከሉ፣ ዘር ቆጥራችሁ ትዳር አፍርሱ የተባሉ ወዘተ ጃዋርን ሊቀበሉት አይችሉምና ዘመቻው እዚህ ላይ ይከስራል” ሲሉ ስጋት እንደምያገባቸው ያመለከቱ አሉ።

እነዚህ ወገኖች በወላይታና ሲዳማ መካከል የተከሰተውን ዕልቂት፣ በሻሸመኔ ዝዋይ፣አርሲና መቂ የደረሰውን ዘኛኝ ግድያ፣ ዘረፋና ውድመት፣ እንዲሁን በተለያዩ ጊዜያት ዘርን ለይቶ ለተከሰቱ ግጭቶችና ራሱ “ተክብቤያለሁ” በማለት ባስተላለፈው ጥሪ ለደርሰው ጉዳት በአደባባይ ተጠያቂ የሚደርገው ጃዋር ዳግም አመጽ አስተባባሪ ሆኖ መመረጡ እንቆቅልሽ የሆነባቸውም ጥቂት አይደሉም።

“ቅድሚያ ኦሮሞ” በሚል ኢትዮጵያን እንደ ቅኝ ገዢ አገር፣ አማራን ደግሞ እንደ ቅኝ ገዚ ሕዝብ በመቁጠር በሚዲያዎቹ ክፋት ሲያስታጥቅና ሲያመርት የነበረን ወንጀለኛ በምን ሂሳብ ዳግም ወደፊት የሰላማዊ ትግል አስተባባሪ አድርገው ሊያመጡ እንደቻሉ ግልጽ አይደለም” ሲሊ የግብረኃይሉ አባል ለአዲስ ሪፖርተር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ከግራኝ መሐመድ በኃላ ተጸዕኖ ፈጣሪ ሰው እኔ ነኝ” በማለት ቦሌ ተከራይቶት በነበረው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሲናገር ይሰሙ የነበሩ እንደሚሉት፣ ጃዋር ያንን ጊዜ አባክኗል። ያንን ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበረበትን አጋጣሚ አበላሽቶ ዳግም መሳሪያ ካነገቡ ኃይሎች ጋር መቀናጀቱ ሰፊ ድጋፍ ሲሰጠው ከነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ጋር ጭራሹኑ እንደሚያቆራርጠው መረዳት አለመቻሉ ግራ አጋብቶኛል” የሚሉት እኚሁ የግብረኃይሉ አባል፣ እሳቸው ባላቸው ግንኙነት ኦሮሚያ ላይ በፍጹም ሰሚ እንደማያገኝ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። ተመሳሳይ አስተያየት የሚሰጡ “ጃዋር ከግብጽ ጋር የገባው ኮንትራትና ያበላሸው ዕድል የፈጠረበት ዕልህ እዚህ ጣጣ ውስጥ እንደከተተው ጥርጥር የለውም” ብለዋል።

እንቅስቃሴው የማይንቁ “በሀገሪቱ ካለችበት የቀጠናው የፖለቲካ ትኩሳት አንጻርና የአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ውጥረቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሸጋግረው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ጀዋር መሃመድ ከዚህ ቀደም በ”ሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት” ስም ያደረጋቸው ቅስቀሳዎች በተግባር ሲተረጎሙ ከፍተኛ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት አስከትለዋል። በተለይም በብሔር ማንነት ላይ ያተኮሩ ግጭቶች እንዲቀሰቀሱና በዜጎች መካከል መጠራጠር እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የጀዋር ጥሪዎች የነበራቸው ሚና ቀላል አልነበረም። ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር የሚደረጉ ግጭቶችም ለብዙ ወጣቶች መሰዋትነትና ለሀገር ሰላም መታወክ ምክንያት ሆነው ማለፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ መግለጫ፣ መንግሥት ካለበት የሰላም ድርድር ጥረትና የፀጥታ ማስከበር ጫና ጋር ተዳምሮ ትልቅ ፈተና ሊሆን ይችላል። ጃዋር መሃመድና አጋሮቹ “ሕዝባዊ አመፅ” ብለው የሰየሙት እንቅስቃሴ፣ በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር አንድ ላይ መሆኑ፣ ሰላማዊ ተቃውሞን ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት የመቀየር እድሉ ሰፊ ነው። ይህም በሲቪል ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ከማባባሱ ባለፈ፣ የሀገሪቱን አንድነትና መረጋጋት ይበልጥ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ስጋታቸውን የሚገልጹ አሉ።

ከዚህ በተጨማሪ፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ጥሪ የሚሰጡት ምላሽ ለእንቅስቃሴው ስኬት ወይም ውድቀት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። በዲያስፖራው የሚደገፉ የፖለቲካ ግፊቶች በሀገር ውስጥ ባለው መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ያላቸው ግንኙነት ብዙ ጊዜ ለውይይት የሚቀርብ ቢሆንም፣ አሁን የታቀደው ግንኙነት ግን ቀጥተኛና የተቀናጀ መልክ ያለው መሆኑ ሁኔታውን የተለየ ያደርገዋል። ይህ ሁኔታ የውጭ ሀይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ አጀንዳቸውን ማራመድ እንዲችሉ ታቅዶ የተሰራ በመሆኑ ጉዳዩን መመርመር እንደሚገባ ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል።

የጃዋር መሃመድ የተለመደው የጥፋት መንገድ ሃገሪቱ አንድናቷን ጠብቃ ሉእላዊ የባህር በር እና ሌሎች ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር  ጥረት በምታደርግበት ወቅት የአመፅ ጥሪ መጠራቱ አሁን የውጭ ሃይሎች የዲያስፓራውን ፓለቲካ እንደሚዘውሩት አመላካች እንደሆነ አካሄዱን ከጅምሩ የሚከታተሉ እየገለጹ ነው።  የፖለቲካ ልሂቃንና የሚመለከታቸው አካላት ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ሁኔታዎችን መርመር እንዳለባቸውም እያሳሰቡ ነው። የትጥቅ ትግልና ሕዝባዊ አመፅን በማቀናጀት የሚደረጉ ጥሪዎች የሚያስከትሉት ውጤት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን ካለፉት ዓመታት ትምህርት መውሰድ ለሀገር ዘላቂ ሰላም ወሳኝ መሆኑን እነዚህ ወገኖች አሳስበዋል።

“በኦሮሚያ ትራክተር፣ ኮምባይነር፣ የውሃ መሳቢያ ሞተር፣ አውድሞ የሚጨፍር፣ ፋብሪካ አቃጥሎ የሚሞቅ ቄሮ የለም” በማለት መግለጫው ዓርብ እንደሚሰጥ በዘገብንብት ዘገባ ማስታውቃችን አይዘነጋም፣ ከቄሮ አደረጃጀት ጋር ቅርበት ያላቸው “የሚሆነውን አብረን እናያለን”

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ከድጡ ወደ ማጡ – የሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት ስጋት እና ተጠባቂው የቀጣናው መናወጥ

አዲስ ሪፖርተር - ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ሰሞኑን ባወጣው...

በሱዳን ጦርነት ብሄራዊ ጥቅሙን አሳልፎ እየሰጠ ያለው ደናቁርት “ኢትዮጵያዊ ሊሕቅ” እና ተጨባጩ እውነታ

እነ ጀዋር መሃመድ እና መሰሎቹ የድንቁርና ጌቶች  መሃመድ ዳጋሎ...

“ጃዋር ለምን ከጀርባ ይደበቃል? እኛ እንደ እናንተ ከግብጽ ገንዘብ አናገኝም”

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምጽና እንዲነሳ የሚጠይቅ መግለጫ...

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ መምጣት የቀይ ባህርን ጉዳይ ወደ ፍጻሜ እየመራው ስለመሆኑ ማሳያ

ከኤርዶጋን ጉብኝት ማግስት የእስራኤል ፕሬዝድንት ወደ አዲስ አባባ እንዳሚመጡ...