በጋምቤላ ከሚሊዮን በላይ ስደተኞች አስቸኳይ ዓለም ዓቀፍ ድጋፍ ተጠየቀላቸው፤ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ስጋት ሆነዋል

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ክፍል በምትገኘውና የብዙ ስደተኞች መጠለያ በሆነችው ጋምቤላ ክልል እጅግ ከፍተኛ የሆነ የመሰረታዊ ፍላጎቶች እጥረት እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ የሃሰተኛ መረጃዎች መበራከት በስደተኞች ላይ ያለውን ሁኔታ ይበልጥ እያባባሰውና ውጥረቱን እየጨመረው መሆኑ ተሰማ። ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያሰራጩት ሃሰተኛ ዘገባም አሳሳቢ ነው ተብሏል፤

የኢትዮጵያ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (RRS)፣ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ለመርዳት ተቸግራለች።
ተቋማቱ እንዳሉት እንደ ምግብ፣ ውሃ እና የጤና አገልግሎት ያሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል በቂ የገንዘብ ድጋፍ አጥረት አለ። አክለውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ካልተገኘ፣ እነዚህ ወሳኝ አገልግሎቶች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሊቋረጡ እንደሚችሉ አስጠንቀቀዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛውን ከፍተኛ የስደተኞች ቁጥር የምታስተናግድ ሀገር ነች። ብዙዎቹ ስደተኞች በጦርነት ምክንያት ከሱዳን እና ከደቡብ ሱዳን እንዲሁም በድርቅ ምክንያት ከሶማሊያ የሚመጡ ስደተኞች ናቸው።
ሰብአዊ ድርጅቶች በ2025 የአስቸኳይ ጊዜ አቅርቦቶችን በ70 በመቶ ለመቀነስ ተገደዋል። በጥቅምት ወር የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለ780,000 ስደተኞች የሚሰጠውን የምግብ ድርሻ ወደ 40 በመቶ ዝቅ ያደረገ ሲሆን ይህም በቀን አንድ ሰው ከ1,000 ካሎሪ በታች ብቻ እንዲያገኝ ማደረጉን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
በአሁኑ ወቅት ሙሉ የምግብ ድርሻ የሚያገኙት 70,000 አዲስ የገቡ ስደተኞች ብቻ ናቸው። በዚህም ምክንያት በስደተኞች መጠለያ ውስጥ የምግብ እጥረት ከ15 በመቶ በላይ የጨመረ ሲሆን፣ ከአንድ ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የሞት መጠን ወደ 4.7 በመቶ እንዳሻቀበ ትመልክቷል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን “ሀብታችን ተሟጦ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል፤ በአስተናጋጅ ማህበረሰቡ ላይ ያለው ጫናም ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ እየሆነ ነው” ብለዋል። የUNHCR ተወካይ አይሳቱ ኤም ንድዬ በበኩላቸው፣ “አሁን የሚወሰዱት ውሳኔዎች የኢትዮጵያ የስደተኞች ድጋፍ ስርዓት ይፈርሳል ወይስ አገግሞ ይቀጥላል የሚለውን ይወስናሉ ” ብለዋል

የውሃ እና የትምህርት አገልግሎቶችም አደጋ ላይ ናቸው። ስደተኞች በቀን የሚያገኙት የውሃ መጠን ከ12-14 ሊትር ብቻ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ አምስት ሊትር ዝቅ ብሏል። ለ110,000 ህጻናት አገልግሎት የሚሰጡ የ57 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጀት አልቋል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (December 31, 2025) ይዘጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም ህጻናትን ለአካለ መጠን ላልደረሰ ጋብቻ፣ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚያጋልጣቸው ከሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል።

በጋምቤላ ክልል ያለው ባልረገበት በአሁኑ ሰዓት ስደተኞች ወንጀል እንደሚፈጽሙ፣ የጸጥታ ችግር እንደሚፈጥሩ ወይም ያለአግባብ ሀብት እንደሚጠቀሙ የሚገልጹ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት እየተሰራጩ ይገኛሉ። የምግብ እና ሌሎች አገልግሎቶች ውስን በሆኑበት በዚህ ወቅት፣ እነዚህ መረጃዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ፍርሃትና ውጥረትን እየጨመሩ ነው። በአስተናጋጅ ማህበረሰቡ እና በስደተኞች መካከል በቅርቡ የተከሰቱ ግጭቶች አካባቢውን ይበልጥ ያልተረጋጋ አድርገውታል። በመሆኑም UNHCR የረዳት ሰራተኞችን እና የነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል በጋምቤላ የምግብ እና የውሃ እደላን ለጊዜው አቁሟል።

ሰብአዊ ድርጅቶች ለጋምቤላ አስቸኳይ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን፣ ውስን የሆኑ ሀብቶች እና ሀሰተኛ መረጃዎች ተዳምረው ወደ ግጭት ሊመሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። RRS፣ UNHCR እና WFP በጋራ በሰጡት መግለጫ “ኢትዮጵያ ለስደተኞች በሯን ክፍት አድርጋ ቆይታለች፣ ነገር ግን ይህንን ብቻዋን መወጣት አትችልም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎችን ህይወት ለመታደግ እና ሰላምን ለማስፈን አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ አጥብቀው አሳስበዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...