ሕዝቡ ከአሁኑ በኋላ ሕዝቡ ወደ ቀደመው መንገድ በኃይል አይገባም። ጦርነት እንዳለ ቢረዳም አልፈራም። የሚችለውን ለማድረግ በራሱ መንገድ ተደራጅቷል። በሌላም በኩል ለትግራይ ኃይሎች የሚሰሩ አሉ፤ ታዛቢዎች እንደሚሉት በሰላማዊ መንገድ በባህላዊና በአገር ወግ መሰረት ችግሩ እኒፈታ እየመከሩ ነው። ይህ ካልሆነና አሁን በከበባ የተያዘው የጦርነት ጅማሮ ሙሉ በሙሉ ከፈነዳ በራያ አቅጣቻም ስለሚነሳ አደጋው የከፋ እንደሚሆን እየተገለጸ ነው።
አዲስ ሪፖርተር – ይፋ በተደረገው አዲስ ሹመት መሰረት፣ የአርሚ 50 አዛዥ ወዲ ኤምባቲ የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ በመሆን ሌተናል ታደሰ ወረደን ተክተዋል። ታደሰ ወረደ ከትግራይ ርዕሰ መስተዳድርነታቸው በተጨማሪ ይዘውት የነበረውን የጸጥታ ጉዳይ ኃላፊነት የተነጠቁት አዲስ ለሚጀመረው ኦፕሬሽን ሊታመኑ ባለመቻላቸው እንደሆነ ተመልክቷል። የደቡብ ግንባር አዛዥ ዮሐንስ መዲድ የትግራይ ሰራዊት ዘመቻ ኃላፊ፣ ማሾ በየነ የመረጃ እንዲሁም፣ ምግበይ የስልጠና ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
አራቱንም ቁልፍ ወታደራዊ ሹመት ለአደዋ ተወላጆች መሰጠቱን የተሿሚዎቹን የትውልድ ሃረግ የሚያውቁ አስታውቀዋል። ሹም ሽሩን ተከትሎ በጠለምት በኩል ጦርነት ተጀምሯል ። ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከፋኖ ጋር ጥምረት በመፈጠር ትህነግ የውጊያ አቅሙን ማሳደጉን ደጋፊ የሆኑ የመገናኛ ዘዴዎች አስቀድመው ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል።
ፋኖ፣ ሱዳን፣ ሻዕቢያና ትህነግ በጋራ ኢትዮጵያን ለመውጋት የደረሱበትን ስምምነት “ትግሉ ተጠልፏል” በማለት ወደ ሰላማዊ መንገድ የተመለሱ የፋኖ አመራሮች መናገራቸው ይታወሳል።
በሪፖርተር ጋዜጣ የወልቃይት አስተዳደር እንዲፈርስ መንግስት አቋም መያዙን እንዲናገር ከተደረገ በሁዋላ ዜናው በከፍተኛ ደረጃ ለቅስቀሳ እንዲውል ተደረገ። በአካባቢው ያለውን ነዋሪ ተስፋ ለማስቆረጥ ሰፊ የቅሰቀሳና የፕሮፓጋንዳ ስራ ከተሰራ በሁዋላ በሽሬ ያሉ እናቶች “እናመሰግናለን ሽሬ፣ በቀጣይ ሳምንት ምዕራብ እንገናኝ” በሚል ሲያዜሙ፣ ሲጨፍሩና ታጣቂዎችን ሲያበረታቱ የሚያሳይ ቪዲዮ ይፋ ሆነ።
ጄኔራል ምግበይ “በሚቀጥለው ሳምንት ወልቃይትን እንይዛለን” ባሉ በሳምንት ልዩነት እንደተባለው ጦርነት ተቀሰቀሰ። አርሚ 11 በትናንትናው ዕለት በማይ ዳጉሽ አቅጣጫ ወደ ምስራቅ ጠለምት ዲማ ከተማ ለመግባት 30 ኪሎሜትር ርቀት ድረስ ተጠጋ። ይህ ኃይሉን አጠናክሮ የተከዜ በረሃን አቋርጦ የተጠጋው ኃይል ከመከላከያ ሰራዊት የመከላከል እርምጃ እንደተወሰደበት የወርዳው አስተዳደር ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቋል።
በትናትናው የዜና ዕወጃችን እንደተገለጸው ሁለት አዛዦችና የጦር መሳሪያዎች የተያዙ ሲሆን፣ የተገደሉና የቆሰሉ በርካታ መሆናቸው ታውቋል። ከመከላከያ የመከላከል እርምጃ በሁዋላ የአርሚ 11 ኃይል ወደ መጣበት መመለሱ ታውቋል። የምስራቅ ጠለምት ወረዳ አመራር እንዳሉት፣ አሁን ላይ 30 ጉዊላ፣ በሚባልና ደገብራይ በሚባሉ ቦታዎች ቅርብ ርቀት ላይ ያለው የትህነግ ኃይል ለጊዜው ውጊያ ቢያቆምም ኃይሉን አሰብስቦ ዳግም በሌሎች አቅጣጫዎችም ጭምር ጦርነቱን በማስፋት የመቀጠል ዕቅድ እንዳለ መረጃ እንዳላቸው አመልክተዋል።
የተከዜን በረሃ አቋርጠው የማዕከል ከተሞችን ለመያዝ አቅደው በሁለት አቅጣጫ ውጊያ የከፈቱት የትህነግ ኃይሎች፣ የማይጠብሪን መንገድ መቁረጣቸው ተሰምቷል። ጦርነቱን የሚመራው የአገር መከላከያ በመሆኑ ብዙ መረጃዎች መስጠት ባይቻልም፣ የማይጠብሪ መንገድ የተቆረጠው ጠለምትን በመገደብ ስትራቴጂካል ጥቅም እናገኛለን ብለው በማሰባቸው እንደሆነ ተመልክቷል።
በትናትናው ዕለት በአገር መከላከያ የመከላከል እርምጃ ወደ መጣበት ከተመለሰው ኃይል ውስጥ አብዛኞቹ የማይጠብሪ ተወላጆች በመሆናቸው እየከዱ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እያመሩ መሆኑ ተሰምቷል። በዚሁ ሳቢያ ከሽሬ ወደ ማይጠብሪ የሚሄደውን መንገድ ትህነግ እንደዘጋው የአካባቢው የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ አስታውቋል።
አርሚዎች የተደራጁት በአካባቢ ተወላጆች በመሆኑ፣ ካለፈው ጦርነት ጠባሳ የተነሳ መዋጋት የማይፈልጉ እየሸሹ ወደቤታቸው መግባት አሁን አሁን የተለመደ እንደሆነ እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ። ወደ ቤታቸው የማይገቡት ደግሞ የትግራይ ሰላም ኃይሎችን ይቀላቀላሉ። ጦርነቱ ትናንት ተጀምሮ እንደቆመ ቢገልጽም የትህነግና የፋኖ ደጋፊዎች የአርሚ 11 ኃይሎች ወደ ምስራቅና ምዕራብ ጠለምት እየተጠጉ መሆናቸውን እያስታወቁ ነው።
ሰፊ መሬት በመቆጣጠር ከፋኖና መለያ ልብሳቸውን ከቀየሩ የሻዕቢያ ኃይሎች ጋር በመሆኑ ጥቃታቸውን ማጠናከራቸውን እነዚሁ ወገኖች እየገለጹ ነው። ከሁሉም ወገን የሚወጡ መረጃዎች በሚታወቁ በገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጫ አልተሰጠጠባቸውም። ትህነግም በሚታወቁ የማህበራዊ ገጾቹ የገለጸው ነገር የለም።
በሌላ ተመሳሳይ የጦርነት ዜና ሱዳን የነበረውና ከሻዕቢያ ጋር በይፋ ወታደራዊ ጥምረት መፈጸሙ በመረጃ ይፋ የሆነበት አርሚ 70 ሺረረና መሰፈራቸው ታውቋል።
ይህ በሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ሺረርና የሰፈረው ኃይል ከፋኖ የአካባቢው ኃይል ጋር ግንባር ገጥሟል። የአካባቢው የመረጃ ሰዎች እንዳሉት የካቲት 11 ቀንን በወልቃይት ለማክበር ከፋኖ ጋር የጥምር ጥቃት ለመሰንዘርና፣ እነሱን ተከትሎ የሻዕቢያ ኃይል ሙሉ ደጋፍ ለመስጠት ቦታ ይዘዋል።
የወልቃይት ዞን ስለጉዳዩ የሚያውቀው እንዳለ ከአዲስ ሪፖርተር ለቀረበለት ጥያቄ “እኛ ጋር ምንም የለም። ሁሌም ዝግጁ ነን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የአገር መከላከያ ድንበር አካባቢ በመሆኑ ሰፊ ዝግጅት እንዳለ ያመለከቱት እንደሚሉት የትህነግ፣ ፋኖና ሻዕቢያ ኃይሎች በወልቃይት አቅጣጫ ከመጡ ሙሉ የተከዜ ኃይል፣ መከላከያና ራሱን ያደራጀው ሕዝብ ይሆናል ያሉትን ርምጃ ይጀመራሉ።
ይህ በንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ መሪ ዘመነ ካሴ በኤርትራ ከፍስሃ ማንጁስ ጋር ከተገናኑ በሁዋላ የደረሱበት ስምምነት ታውቋል። በኦምሃጀር በተደረገ የጋራ ውይይት ትህነግ ለፋኖ ሎጂስቲክ፣ በጦርነት ለሚጎዱ የሕክምና፣ የጦር ሜዳ የወጊያ ታክቲክ ንድፍ ድጋፍ፣ በሚደረገበት አግባብ ዝርዝር ስምምነት አድርገዋል።
ቀደም ሲል ትህነግ ሕዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍ ሲያደርግ እንደነበረው ፋኖም በመከላከያ ሰራዊት መለያ ዩኒፎርም ከባድ ወንጀሎችን እየፈጸመ ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳ የሚያስችል ፕሮፓጋንዳ እንዲሰራ ስትራቴጂ ተነድፎለታል። ፋኖ በዚሁ ዕቅድ መሰረት የተሰጠውን ሲተገብር የትህነግና የሻዕቢያ ተባባሪ ሚዲያዎች ይህንኑ በማስተጋባት ሕዝብ እንዲነሳና እንዲማረር ቅሰቀሳ እንድሚያደርጉ ቃል ተገብቷል።
በቅርቡ እነ አቶ ነዓምን የመሰረቱት ኢትዮጵያን በህዝባዊ እምቢተኛነት የማነሳሳትና የማተራመስ ዕቅድ ለፋኖ በተቀረጸው ስትራቴጂ መሰረት የሚፈጸሙ ከባድ ወንጀሎችን በማሰራጨት፣ በማራባትና፣ በማግን የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲሰራ ከስምምነት መደረሱን በዙም የተደረገውን ስብሰባ ዋቢ አድርገን ማቅረባችን አይዘነጋም። አድማጮቻችን የጦርነት ውሎ ዘገባዎችን በአዲስ ሪፖርተር የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾቻቸን የከተሉ። የዩቲዩብ ገጻችንን ላይክና ሼር ታድርጉ።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






