ኤርትራ ለህወሃት ቁልፍ ሰዎች አጭር ቀነ ገደብ ያለው የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለመስጠት የወሰነችውን ውሳኔ መልሳ መያዟ ተሰማ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኤርትራ መንግስት ለህወሃት አመራሮችና ከፈተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎች ለመስጠት አስተላልፎት የነበረውን ውሳኔ መያዙ ተሰማ። ውሳኔው የተያዘው አሜሪካ ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማሸማገል የጀመረችውና ኤርትራ ላይ ያሳደረችው ጫና ተከትሎ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በፕሪቶሪያው የሰላም አማራጭ ስምምነት መሰረት ውድቅ የተደርገውን ምርጫ ወደ ኋላ ተመልሶ ህጋዊ በማድረግ የጊዜያዊ አስተዳደሩን በማፍረስ ስልጣን የጭበጠው በእነ ዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን፣ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲሰራላቸው ኤርትራ የተስማማችው ጽምዶ መመስረቱን ተከትሎ እንደነበር ዜናውን ያጋሩን አመ፤ልክተዋል።

በስምምነቱ መሰረት የዚሁ ቡድን ቁልፍ ባለስልጣናትና ውስን የጦረ መሪዎች የኤርትራ ዜጋ ሆነው የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲዘጋጅላቸው ስምምነት ላይ የደረሰው ሁልወቱ አካላት “ጽምዶ” የሚባለውን ጥምረት ሲፈጥሩ ነበር። እንደ ዜናው ሰዎች ከሆነ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር የጀመረችው አዲስ ወዳጅነት ኤርትራ ላይ የሚጥለው ገደብ አለ። ከገደቦቹ መካከል በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት ነው። በዚሁ መሰረት አሁን ላይ ጽምዶ እየፈረሰና ኤርትራ እጆን እየሳበች እንደሆነ የሚያመለክቱት ወገኖች፣ የኤርትራ አቋም የተቀየረው ይህንኑን ተከትሎ ነው።

ኢትዮጵያና ኤርትራን ከሌሎች ወዳጅ አገሮች ጋር በመሆን ወደ ማግባባቱ እየደረሰች ያለችው አሜሪካ ለህወሃት ኃይሎች “ጦርነት እንዳታስቡ” በሚል ማስጠንቀቋን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። በዚሁ ማስጠንቀቂያ ወደ ጦርነት የሚገቡ ከሆነ ማዕቀብ እንደሚከተላቸውም አሜሪካ በግልጽ መቀለ በተገኙ ከፈተኛ የጦር አዛዦችና ዲፕሎማቶች አስታውቃ ነበር። ከተጠቀሱት ማዕቀቦች መካከል የሃብት እና የጉዞ እግድ የመጀመሪያዎቹ በመሆናቸው፣ ኤርትራ እዚህ ጉዳይ ውስጥ ገብታ ተባባሪ ልትሆን አትችልም።

አሁን ላይ በሚወጡ መረጃዎች ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማግባባት የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ የህወሃት ኃይሎች ከውስጥ ከገጠማቸው ተቃውሞና የዲፕሎማሲ ውድቀት ጋር ተዳምሮ ምን ስልት ሊከተሉ እንደሚችሉ ለጊዜው አልታውቀም። ይሁን እንጂ ቡድኑ ከመንግስት ጋር ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ እንደሆነ አስታውቋል። መንግስት እንድተለመደው ዝምታን መርጧል። ከአሜሪካ ጋር ትልቅ የተባሉ ስትራቴጂካል ስምምነት መስማማቱ ላይ ትኩረት ሰጥትቶ እየሰራ ነው። ይህን ተከትሎ በትግራይ ባለው ቡድን ላይ ምን ጫና ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ባይቻልም፣ ማዕቀድ እንደሚደረግ ፍንጭ እየተሰማ ነው።

የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ ሰዎች በሄዱበት ሀገር በቁጥጥር ስር የመዋል ወይም የመከሰስ ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በወንጀል ወይም በተለያዩ ጉዳዮች የሚፈለጉ አመራሮች ካሉ የህግ ከለላ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ከዛም በላይ በሀገራት መካከል በሚያደርገው ጉዞ እንደ ተራ መንገደኛ ጥብቅ ፍተሻና እንግልት አይገጥመውም። ይህም አመራሮቹ በተለያዩ ሀገራት በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ እና የቪዛ ሂደቶች እንዲቀሉላቸው ያደርጋል።

የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት፣ ግለሰቦቹ በኤርትራ መንግስት ጥበቃና እውቅና ስር መሆናቸውን ያሳያል። ይህም ከሌሎች ወገኖች ሊሰነዘርባቸው የሚችልን ጥቃት ወይም ተፅዕኖ ለመቀነስ ይረዳል። የህወሃት ቁልፍ አመራሮቹ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ውጭ አማራጭ የዲፕሎማሲ መስመር እንዲኖራቸው ከማሰብ ቢሆንም አሁን ላይ ይህ መቆሙን የዜናው ምንጮች አመልክተዋል። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ከባለስልጣናቱ ቤተሰብ ባገኘው መረጃ እንዳለው ይህ የኤርትራ ውሳኔ ክፉና ስጋት ፈጥሯል። ነገ ከነገ ወዲያ የተለያዩ እርምጃዎች ላለመወሰዱ ምንም ማረጋገጫ የለም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አሜሪካ እና ከኢትዮጵያ ጋር “ቋሚ ማዕቀፍ” የተባለ ስምምነት ተፈራረሙ፤

ዲስ ሪፖርተር - የአሜርካና የኢትዮጵያ አዲሱ ስምምነት "ቋሚ ማዕቀፍ"...

በግብጽ አስተባባሪነት ከሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ሱዳን ጋር ጥምረት የፈጠሩ በዲሲና ሎንዶን [ዳስ ይጥላሉ] ተባለ፤

“አሳቡ አገዛዙን ማውገዝ፣ ሕዝብን በጋራ ማነሳሳት እና አመጽ ማቀጣጠል...

የአመጽ አደራጅ ግብርኃይል በአብይ አህመድ ጉዳይ ተለያየ፤ “ግምት ውስጥ ገብተናል፤ ሚዛን እንጠብቅ”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - “በምንም ይሁን በምን ምርጫ መደረግ...