አዲስ ሪፖርተር – በአገር ቤት ሕዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት የተደራጀው ግብረ ኃይል በስጋት መነሻ ከፍተኛ ጭቅጭቅ አንስተው እንደነበር ተደመጠ። አቶ ነዓምን ዘለቀ የሚመሩት ይህ ግብርኃይል ባለፈው ሰኞ ባደረገው ስብሰባ ጠንካራ ጭቅጭቅ የተነሳው የቀድሞ የህወሃት ስራ አስፈጻሚና መስራች የነበሩት ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን ባነሱት ኃሳብ ላይ በመንተራስ ነው። ኢንጂነር ሙሉጌታ ዘለቀ “ከማን ጋር እንደምንዋጋ አላወቅንም” ሲሉ ተደምጠዋል።
“የኢትዮጵያና የአሜሪካ አዲሱ ግንኙነት አደገኛ ነው” በማለት የጀመሩት ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን “የኢትዮጵያ የድህንነት ኃላፊው አቶ ሬድዋን ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር ተነጋግረዋል፤ ይህ ከባድ ጉዳይ ነው” በማለት ሊለተል የሚችለውንም ጣጣ በስጋት ገልጸዋል።
የኢትዮጲያና የአሜሪካ ስትራቴጂካል ስምምንነት አደገኛ መሆኑን ያመለከቱት ኢንጂነር ግደይ፣ “በከፍተኛ ደረጃ የሚነቀሳቀሱ ፖለቲከኞችን አሳልፎ መስጠት ሊከተል ይቻላል” ሲሉ ተደምጠዋል።
የየዕለቱን የግብርኃይሉን ስብሰባ የሚዘገበው የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ እንዳለው ተቀማጭነታቸው ኖርዌይ የሆነው ኢንጂነር ግደይ፣ “ከደህንነት አንጻር የተደረገውን ውይይት ባለን መዋቅር እያጠራነው ነው። እስከዛው ኝ ጥንቃቄ ያሻል” ብለዋል።
ከግብረኃይሉ ውስጥ ሶስት ሰዎች ሱዳን ከርመው መመለሳቸውን ስም ጠቅሰው መርጃውን ለተባባሪያችን የሰጡት የግብረኃይሉ አባል፣ “ከውስጣችን የግብረኃይሉን አካሄድ የማያውቁ አሉ፤ አካሄዱና ዓላማው ሌላ ነሆኑ የገባቸው ደንግጠዋል” ብለዋል። ይህንንም ሲያስረዱ ኤንጂነር ሙሉጌታ ያነሱትን ተናግረዋል።
ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን ተከትሎ “ምንም ችግር የለውም” በማለት አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም ሲናገሩ ኤንጂነር ሙሉጌታ በቁጣ “ከማን ጋር እንደምንዋጋ የገባን አይመስለኝም። ሁልጊዜ እያጣጣልን የምናየው ጉዳይ እየቀጋን ነው” ሲሉ አቶ ያሬድን ገሰጹዋቸው።
“በትክክለኛ መንገድ ላይ አይደለንም። ከማን ጋር እንደምንዋጋ አናውቅም። ጥናት አዘጋጅቼ አቀርባለሁ። ነገሮች እኛ እንደምናያቸው አይደሉም። ጉዳዩ በጣም ያስፈራል” በማለት ኤንጂነር ሙሉጌታ ቆጣ ብለው መናገራቸውን ያመለከቱት የስብሰባው ተካፋዮች፣ ይህ ሁሉ ሲባል አቶ ነዓምን እንደወትሯቸው ጣልቃ እየገቡ አስተያየት አልሰጡም።
ከኤርትራ ጋር እንደተጀመረ የሚነገርለት የስምምነት አግባብ እና አሜሪካና ኢትዮጵያ በመከላከያ፣ በድህንነት፣ በኢኮኖሚና በቀይ ባህር ዙሪያ ያደረጉት ስምምነትና፣ አሜሪካ ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪቃ አንከር ማድረጓ ይዞት የሚመጣው ጣጣ የተወሳሰበ የሆነው ከግብረኃይሉ ውስጥ ሱዳን የሚመላለሱ መኖራቸውም ጭምር ነው።
አልቡርሃን በሽብር የፈረጀውችው አሜሪካ ወደ ሱዳን የሚያመሩትን፣ ለነሱ ድጋፍ የሚያደርጉትንና የሚዲያ ድጋፍ የሚሰጡትን በህግ ልትጠይቅ እንደምትችል በግል የግብረኃይሉ አባላት መወያየታቸውን የዲሲ ዘጋቡ አስታውቋል።
ቀደም ሲል ከዚሁ ከሽብር ጋር በተያያዘ ፍርሃቻ በሎንዶንና በአሜሪካ ይካሄዳል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቀር መወሰኑን ያስታወሱት የዜናው ባለቤቶች “የአማራ ተወካይ ነን” የሚሉት የእነ አቶ ነዓአምንን “አብረን እንሰለፍ” ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት ከዚሁ ስጋት በመነሳትም ጭምር እንደሚሆን አመልክተዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






