አዲስ ሪፖርተር፣ አዲስ አበባ — የሕወሓት ሰራዊት አዛዦች ከፌዴራል መንግሥት ጋር አዲስ ጦርነት ከተጀመረ ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንደሚችል ህወሃትን ተቃውመው አዲስ አበባ የሚገኙ ከፍተኛ የጦር መኮንን ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቁ። ክረምቱን ሲጠብቁ የነበሩ የህወሃት አመራሮች ጦርነት ያልከፈቱት በዚሁ መነሻ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የህወሃት ሰራዊት አዛዦች ከፌዴራል መንግሥት ጋር አዲስ ጦርነት ከተጀመረ ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል በሚል ስጋት ውጊያ ላለመጀመር መስማማታቸውን ለአዲስ ሪፖርተር የገለጹት መኮንኑ፣ ይህንን ያሉት ሰሞኑን ህወሃት ባካሄደው ስብሰባ በዚህ ጉዳይ ላይ የደረሰበትን ግምገማ መንሻ አስድረገው ነው።
የአርሚ አዛዥ የተባሉ ሰሞኑን ባካሄዱት የወቅታዊ ቁመና ግምገማ ጦርነት ማካሄደ የሚቻልበትን አገባብ አንስተው ነበር። የግመገማውን ውጤት እንደሰሙ የገለጹት መኮንኑ፣ የህወሃት አመራሮች እና የአርሚ አዛዦች “ሕዝባዊ አንድነታችን ተሸርሽሯል” ብለዋል። የሰራዊቱ የመዋጋት ፍላጎት መላላት፣ የሞራልም ውድቀት አሳሳቢ መሆኑን በግልጽ አንስተው የተናገሩ እንዳሉት፣ በሸረሪና ግንባር የተማረከው የተዋጊ ቁጥር፣ ህይወታቸው ያለፈና የቆሰሉት ብዛት ወደ ሌላ ጦርነት ለመሸጋገር የማያስችል አማራጭ እንደሌለ አመልካች ነው። መረጃውን አካፍለውን አስተያየት የሰጡት መኮንኑ “የሸረሪን ጦርነት እንደ ማሳያ በማንሳት፣ አዲስ ጦርነት ከመጀመር ይልቅ በመከላከል ላይ ብቻ በማተኮር ግጭት በማራባት ለድርድር ጫና እናድርግ የሚል ዕቅድ ይዘዋል። የት እንደሚያደርስ አላውቅም” ብለዋል።
በሃራ መሬት ያሉት የሰላም ኃይሎች መሪ የጄኔራል ገብረ እግዚአብሔር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ከስድስት መቶ በላይ ተዋጊዎች በመከላከያ ሰራዊት እጅ መሆናቸውን ጠቅሰው “በሸረሪና ግንባር የነበረው ኃይል ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል” በማለት የጉዳቱን መጠን መናገራቸውን ጠቅሰን መገባችን ይታወሳል።
ሰሞኑን በህወሃት አመራሮች መሪነት በተካሄደው ግምገማ መሰል ውይይት ላይ የተያዘውን አቋም አስመልክቶ የደረሳቸውን መረጃ በማታቀስ መኮንኑ እንዳሉት አመራሮቹ “ጦርነት ከተነሳ አብዛኛው ታጣቂ እና የውጊያ ቁልፍ የሆኑት የመካከለኛ ደረጃ አመራሮች የመዋጋት ፍላጎት ስለሌላቸው ወዲያውኑ ይፈርሳሉ። ሸሽተው እጃቸውን ለመንግሥት ይሰጣሉ በሚል መደምደማቸው አግባብ ነው። ችግሩ ያለው ከድምዳሜያቸው በመነሳት ምፍትሄውን አለማስቀመጣቸው ነው” በማለት ሰዎቹ “ጦርነት ይብቃ” የማለት አቅም ስለሌላቸው፣ ወቅቱንም ለመረዳት ዝግ በመሆናቸው የሚሆነውን መጠባበቅ እንደሚገባ አመልክተዋል። በአሳቸው እምነት የትግራይ መልክ በዚህ እንደማይቀጥልም አመልክተዋል።
አብዛኞቹ ታጣቂዎች በግድ የታፈሱ፣ ወደ ቤታቸው መመለስ የሚፈልጉ እና ጦርነቱ በቃን ያሉ በመሆናቸው፣ ከጥቂት የድርጅቱ ታማኞች ውጭ አብዛኛው ኃይል እጁን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑ የተለያዩ ሚዲያዎችና የቀድሞ የህወሃት ቀንደኛ ደጋፊዎች የነበሩ ሚዲያዎች ማስታወቅ ከጀመሩ ቆይተዋል።
በአሁኑ ወቅት ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ሸሽቶ እንዳይወጣ በታማኝ ኃይሎች እየተጠበቀ እንደሚገኝ የጠቀሱት አካላት፣ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አፍርሶ ስልጣን የተቆታጠረው ቡድኑ አሁን እያደረገ ያለው ስልታዊ እንቅስቃሴ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለድርድር የሚያስቀምጠውን ግርግር ከመፍጠር የዘለለ አይደለም። በጽምዶ ስም የተለያዩ የታጠቁ ኃይሎችን ሰብስቦ በገሃድ አዋጅ ለማወጅ መቀለ የሚደርገው ሽርጉድ፣ መንግስት ለህወሃት እውቅና እንዲሰጥ ለማስገደድ የሚደረግ መሆኑን ያመለከቱት አካላት “በሰሞኑ ግምገማ መሰል ውይይት ጽምዶ በታሰበው መነገድ አለመሄዱን፣ ሻዕቢያ የሚጠበቀውን የተዋጊ ድጋፍ አለማድረጉ፣ የፋኖ ድጋፍም እስርስ በርሳቸው መከፋፈላቸው ሳንካ እንዳጋጠመው በመጥቀስ የስጋት ትንተናውን አቅርቧል።
ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ መረጃዎች ለአዲስ ሪፖርተር የሰጡት እኚሁ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ፣ “ህወሃት ግጭት ይፈጥራል እንጂ ውጊያ አያነሳም” ሲሉ ከስድስት ወራት በፊት መናገራቸው አስታውሰው እንዳሉት አሁን እዛም እዚህም የሚታየው መንፈራገጥ የዚሁ ውጤት መሆኑን፣ የድርድር መድረክ እንዲካሄድ ሲጠየቅ “እውቅና ይሰጠኝ፣ ምዕራብ ትግራይ ይመለስ፣ ተፈናቃዮች ይመለሱ፣ በጀት ይለቀቅልኝ፣” ወዘተ የሚሉ የተለመዱ የማደናገሪያ ጥያቄዎች ማንሳቱ ከላይ የተገለጸው መረጃ ማጠናከሪያ እንደሆነ አመልክተዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለው እንቅስቃሴ፣ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ወታደራዊ አዛዦች የወደፊት እጣፈንታቸውን በሚመለከት ትልቅ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መሆናቸውን የሚያመለከቱ እንደሚሉት፣ ከፍተኛ አመራሩ ከመቼውም በላይ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውንም አመልክተዋል።
ከዚሁ ጭነቀት ጋር በተያያዘ ለዶክተር ደብረጽዮን ጽህፈት ቤት ሰራተኞችና የተለያዩ ኃላፊዎች ” ከከተማ በመውጣት ወደ በረሃ ልንሄድ ስለምንችል የመድሃኔት፣ የስንቅና የመሳሰሉት አስፈላጊ ዝግጅት እንዲደረግ” በሚል መመሪያ መተላለፉን ዜናውን የሰሙ መዘገባቸው አይዘነጋም። እነዚህ ወገኖች “በትግሪኛ ፉከራ፣ በእንግሊዘኛ ልመና፣ በአማርኛ አንድነት” በማለት መግለጫ የሚያወታው ይህ ቡድን የተሰባበረ አቋም ላይ ቢሆንም ትኩረት እንደሚያሻው ይገልጻሉ።
ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን እየደገሰ ያለው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ይሁንታ እንደሌለው የሚናገሩ እንደሚሉት፣ ይህ ቡድን የትግራይን እና መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ ከጦርነት ወደ ጦርነት እያሸጋገረ የሚኖርበት ዘመን ማብቃት አለበት።
ካለፉት ስህተቶቹ ያልተማረው ሕገወጡ ቡድን የትግራይ ክልል ወጣቶችና ታዳጊዎችን ወደ እሳት ለመማገድ የሚችለውን በሙሉ እያደረገ መሆኑን የሚገልጹት የስምረት ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሕወሓት ቡድንና በሻዕቢያ ጥምረት የትግራይን ሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ የጦርነት እንቅስቃሴ በሕዝቡ ላይ ሥጋት መደቀኑን አስታውቀዋል።
የሻዕቢያ ኃይሎች በአካባቢው የሚያደርጉት ጣልቃ-ገብነትና ከፖለቲካዊ ሁነቶች ጀርባ የሚሠሩት ሴራ በሕዝቡ ደኅንነትና በአካባቢው ሰላም ላይ ከባድ አደጋ መደቀኑን ፕሮፌሰሩ አመልክተዋ። በተለይም ከዚህ ቀደም የነበሩ ታሪካዊ ክስተቶችንና ልምዶችን በመጠቀም በክልሉ የራሱን ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎት ለመጫን እየሠራ ይገኛል። አካሄዱ በሕዝቡ መካከል መከፋፈልን ከመፍጠሩ ባሻገር የቀጣናውን ዘላቂ ሰላም የሚፈታተን እንደሆነ ገልጸዋል።
ቡድኑ በፈጠረው ተጽዕኖ ምክንያት የትግራይ ሕዝብና የክልሉ ታጣቂ ኃይል የሕይወት መሥዋዕትነት እንዲከፍል፣ ለሰላም እጦትና ለንብረት ውድመት እንዲሁም ለከባድ የደኅንነትና የኢኮኖሚ ጫና መዳረጉን ያስረዱት ፕሮፌሰር ክንደያ፤ ቡድኑ የሻዕቢያን ዕቅድ ለማሳካት ቀን ከሌት እየሠራ በመሆኑና ይህንን ተልዕኮ ለማፍረስና የዓለም ማኅበረሰብ እንዲያውቀው ለማድረግ ተደራጅቶ መታገል ያስፈልጋል።
ሕዝቡ ከምንም በላይ ሰላምን፣ መረጋጋትንና የሉዓላዊነቱን መከበር የሚሻ መሆኑን በመግለጽ፤ በአካባቢው ያሉ አካላት ወደ እውነተኛ የሰላም መንገድ ካልተመለሱ የቀጣናው ቀውስ የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል በመገንዘብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል ብርጋዴር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር በየነ (ወዲ እንጥሩ) ሕወሓት ጦርነትን የመረጠው ሰላም ቢሰፍን መጠየቄ አይቀርም ከሚል ስጋትና በባሕሪው ያለጦርነት መኖር ስለማይችል መሆኑን ጠቁመዋል።
ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ጦርነት የመረጠው አቅዶበት ሳይሆን ማመዛዘን ባለመቻሉና ሰላም ቢሰፍን ተጠያቂ እሆናለሁ የሚል ሥጋት ስላለበት ሕዝቡን ለዳግም እልቂት እያዘጋጀው ይገኛል። በስሙ “13ኛ አሃዱ” በመባል የሚታወቀው የቡድኑ የጦር ኃይል በቅርቡ በእግር እየተጓዘ በወጋበት ወቅት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበትና በአሁኑ ወቅት ፈርሶ ጥቂት አባላቱ ብቻ መቅረታቸውን መጠቆማቸው አይዘነጋም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






