አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — አማራ ክልል የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲጀመር ከኤርትራ አስራ አንድ አመራሮች ተለከውላቸው እንደነበር የፋኖ የመረጃ ኃላፊዎች አስታወቁ። አሁን ላይ ፋኖ ወደ ዘረፋ፣ እርስ በርስ መበላላት፣ የተቀየረ መሆኑን አመልክተው ድርጅቱ መርህ አልባ ሆኖ መፍረሱን አመልክተዋል። የመታገያ ምክንያት በማጣት ተበታትኖ በየጫካው በዘረፋ ላይ የተሰማራ የወንበዴዎች ስብስብ መሆኑን ያመለከቱት አቶ መስፍን አባተ ናቸው።
በኢህአዴግ ዘመን የመረጃና ደሕንነት መኮንንና ኃላፊ የነበሩ፣ ወደ ጫካ ከገቡ በኋላ የአፋህድ ሰብሳቢና የመረጃ ኃላፊ የነበሩት አቶ መስፍን፣ “አሁን ላይ እንኳን ጽምዶ አንድ ፋኖ የለም። አፋብን የህወሃት ተላላኪ እንጂ ድርጅት አይደለም። ጎንደርና ሸዋ አያውቀውም። እናት ጭስ አጭሳ እንጀራ መጋገር አቁማለች፣ ጭስ ካየ እንጀራ የሚዘርፍ ሽፍታ ነው” ብለዋል።
አቶ ጌታቸው የሚመሩትን የቀድሞውን ደህንነት በኃላፊነት ሲመሩ የነበሩት አቶ መስፍን፣ “አውቃለሁ” ሲሉ ያጋለጡት ሚስጥር በዋናነት ህዝብ ለማነሳሳት ግድያ፣ አፈና እንደሚፈጸም አመልክተዋል።
አሁን ላይ ነባሩ የፋኖ አባላትና አመራሮች ወደ ሰላም መንገድ መመለሳቸውን ያመለከቱት አቶ መስፍን፣ ሰዎች እንዴት ይገደሉ እንደነበር፣ ለምንና እና እንዴት እንደሚገደሉ፣ ከተገደሉ በኋላ ለዚሁ ተግባር እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ ባደራጇቸው ሚዲያዎች ፕሮፓጋንዳ እንደሚሰራ አመልክተዋል።
ጎጃም ቀጣና እነ ዘመን የአማራ ሳይሆን የሻዕቢያና የህወሃትን አጀንዳ የተሸከሙ በመሆናቸው ከድርጅቱ እንዲሰናበቱ መወሰኑን አመልክተዋል።
አቶ ትንግርቱ ገብረጻድቅ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ እያሉ የአቶ ጌታቸው ኤጀንት ሆነው እንደሚሰሩ ያመለከቱት አቶ ያረጋል አያና ትንግርቱ በጅግጅጋና መላው ሶማሌ ክልል የሚኖሩ አማራዎችን በፋኖ አደረጃጀት ስር ለማደረጃት ይሰሩ እንደነበር አጋልተዋል። አቶ ትንግርቱ አሁን ላይ ውጭ ሆነው አማራውን ለማስጨረስ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ያሉትን የክልሉን ተወላጅ “አማራ ነው፣ ፋኖ ነው” በሚል ቅስቀሳ ለማስጨረስ ከሚሰሩት መካከል አንዱ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ነግዴዎች፣ በመዋቅር ውስጥ ያሉ፣ ወያኔና ሻዕቢያ በጋራ አማራን አልቃሽ በማድረግ ሸኔና ኦነግን ገዳይ በማድረግ ጫካ የመግቢያ አጀንዳ መፈጠሩን አቶ መስፍን በደህንነት ውስጥ እያሉ ከሚያውቁት ስምሪት ጋር አያይዘው አመልክተዋል። አማራን ብሄርተኛ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተወጠነው ውጥን ለማራመድ ህወሃት ጠፍጥፎ የሰራቸውን በማሰማራቱ እና መሪ በመደረጋቸው እንዲነጠሉ መደረጉን አመልክተዋል።
ሰኔ 2016 ዓ.ም እነ ዘመነ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አመራሮችን በመያዝ እነ ዘመነ ምሬ፣ ሄኖክ ኪዳኔ፣ ዘመን ወደ ድርጅቱ አመራር እንዳይሆኑ ምደረጉን አቶ መስፍን አስታውቀዋል። እነዚህ ሰዎች መቼ ነድተመረመሩ
ዘመነ ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ኢህአዴግ ሆኖ መመልመሉን የሚያውቁ መሆኑን አቶ መስፍን አስታውቀዋል። ከዩኒቨርስቲ ሲወጣ የአማራ ክልል ወጣቶች አመራር ሆነ። የግንቦት ሰባት እንቅስቃሴ ሳይሰፋ ለመመከት አቶ በረከት “ትግሉን በራሳችን ሰዎች እንቆጣጠር” በማለት ከሜቴክ በባለሃብት ስም ገንዘብ እንዲወጣ ተደርጎ ወደ ኤርትራ ሄደ። ዘመነ የወጣቶች መሪ በመሆኑ ግንቦት ሰባት “የከዳ” በሚል ተቀበለው።
ፋኖ በተፈለገው መሰረት ውጤት ሊያስገኝ ባለመቻሉ ሻለቃ ዳዊትና አቶ አንዳርጋቸው “የአማራ አንድነት አመቻች” ተብለው በሻዕቢያ ተሹመው መጡ። ወዲያ “የአማራ መታገያ ሰነድ፣ አማራነት” የሚል ማኒፌስቶ አዘጋጁ። ጽሁፉን ያዘጋጁት የሻዕቢያና የህወሃት የፕሮፓጋንዳ ክፍሎች በመሆናቸው “አንቀበልም አልን” ያሉት አቶ መስፍን “ማኒፌስቶው በመላው አገሪቱ ተበትሎ የሚኖር ህዝብን ‘አማራ’ ብለው አገርና መቀመጫ አልባ ለማድረግ የተወጠነው ውጥን ከሸፈ” ብለዋል።
“የፋኖ የእንጀራ ዘረፋ እና ጭስ መሸሸግ”
ፋኖ ለዓመታት ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ ብሎ ጫካ ቢመሽግም የተደበቀበት ህዝብ እሱን መሸከም ከብዶት ብሶት ማሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። በሚዲያ የተገነባው የፕሮፖጋንዳ ፋኖ እና መሬት ላይ ያለው ፋኖ ልዩነት ሰፊ ሆኗል ሲል የቀድሞ የአማራ ፋኖ ጎጃም አደረጃጀት መረጃ ሀላፊ ገለጸ።
አማራ ለአመታት በደል ከፈፀመበት ድርጅት ጋር ሽርክና ለመፍጠር መሞከሩ በራሱ ቆሜለታለሁ ላለው ህዝብ ያለውን ንቀት የሚያሳይ እና የአማራን ህዝብ እርስት ለማስወሰድ የተደረገ ህገወጥ ስምምነት ነው ያሉት አቶ ያረጋል የፋኖ ስብስብ ምንም አይነት የህዝብ ድጋፍ የሌለው እና ተቆጣጠርነው ባላቸው የአማራ ክልል ቦታዎች በዝርፊያና በእገታ ህዝቡን እያማረረ ነው። እናቶች ሞሰባቸውን ከፋኖ ዝርፊያ ለማዳን እንጀራቸውን ጭሱ እንዳይታይ በሌሊት እየጋገሩ ባሉበት ሁኔታ ይህ ታጣቂ ሀይል የዕለት ጉርሱን በውንብድና እየሞላ እንዳለ ማሳያ ነው።
ይህ የተደራጀው ፀረ ሰላም ፀረ ህዝብ ስብስብ ትናንት እንደነበረው ከአማራ ገበሬ እንጀራ እየተሰጠው ሳይሆን በር እየተዘጋበት እና ቤት እየገለበጠ እየገባ የምስኪኑን ህዝብ ጓዳ እየበዘበዘ ይገኛል። ለ3 አመታት ህፃናትን ከትምህርት ከትምህርት ገበታቸው ያራቀው የፋኖ አደረጃጀት አንድን ትውልድ ለማጥቃት ከዕውቀት ደጅ በማራቅ በድንቁርና ለማኖር ከበላዮቹ የተሰጠውን ትዕዛዥ ለማስፈፀም ቢሞክርም ህዝቡ ግን አሻፈረኝ በማለት በ2019 ዓ.፤ም የመማር ማስተማር ስራው እንደሚጀመር ድርጅቱ በመግለጫው ከሰሞኑ አስታውቋል።
ጌታቸው አሰፋ ያሰማራቸው “የቁራ ጫሂ ፈረሶች “ እውነታ
በጌታቸው አሰፋ ይዘወር የነበረው ENN ቴሌቪዥን በለውጡ ማግስት በጀቱ ታግቶ እንዲዘጋ መወሰኑን የቀድሞ የአፋህድ የመረጃና ደህንነት መኮንን እና የፋኖ ሰብሳቢ መስፍን አባተ ከኤን ቢ ሲ ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውቀዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ጣቢያው የተቋቋመበትን ዓላማ በመገንዘብ ከለውጡ በኋላ እንዲዘጋ ተደርጓል።
ጌታቸው አሰፋ ወደ ግብፅ በመሄድ ሥልጠና ወስዶ ከተመለሰ በኋላ ኢኤን ኤን ማቋቋሙንም ገልጸዋል። በጣቢያው ይሰሩ የነበሩ አካላትም ከተዘጋ በኋላ ወደ ተለያዩ አገራት በመበተን በኢትዮጵያ ላይ አሉታዊ ዘመቻ እያካሄዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
እንደ አቶ መስፍን ገለጻ እነዚህ አካላት በአማራነት ስም የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም የሚያካሂዱት ዘመቻ ከማንነትና ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚጣጣም እንዳልሆነ ተናግረዋል። ኢኤንኤን መፍረስ በኃላ ወደ ተለያዩ ሀገራት የተበተኑት የጌታቸው አሰፋ ምልምሎች አውሮፓ፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ በመቀመጥ የግብፅን አጀንዳ እየተቀበሉ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ስራቸውን በሚዲያ እየሰሩ ይገኛሉ።
በመሆኑም የአማራነትን ስም በመጠቀም የሚቀርቡ መልዕክቶች በማን እንደሚመሩና ለምን ዓላማ እንደሚውሉ በጥንቃቄ መመርመር እንደሚገባ የፋኖ አመራሮች ጠቁመዋል። “የነቃ ትውልድ በአልነቃ ባንዳ አይሸወድም” በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ፋኖ ትናንት የነበረው የህዝብ ድጋፍ ዛሬ የለውም
ፋኖ ለአመታት ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ ብሎ ጫካ ቢመሽግም የተደበቀበት ህዝብ እሱን መሸከም ከብዶት ብሶት ማሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። በሚዲያ የተገነባው የፕሮፖጋንዳ ፋኖ እና መሬት ላይ ያለው ፋኖ ልዩነት ሰፊ ሆኗል ሲል የቀድሞ የአማራ ፋኖ ጎጃም አደረጃጀት መረጃ ሀላፊ ገለጸ።
አማራ ለአመታት በደል ከፈፀመበት ድርጅት ጋር ሽርክና ለመፍጠር መሞከሩ በራሱ ቆሜለታለሁ ላለው ህዝብ ያለውን ንቀት የሚያሳይ እና የአማራን ህዝብ እርስት ለማስወሰድ የተደረገ ህገወጥ ስምምነት ነው ያሉት አቶ ያረጋል የፋኖ ስብስብ ምንም አይነት የህዝብ ድጋፍ የሌለው እና ተቆጣጠርነው ባላቸው የአማራ ክልል ቦታዎች በዝርፊያና በእገታ ህዝቡን እያማረረ ነው።
ይህ የተደራጀው ፀረ ሰላም ፀረ ህዝብ ስብስብ ትናንት እንደነበረው ከአማራ ገበሬ እንጀራ እየተሰጠው ሳይሆን በር እየተዘጋበት እና ቤት እየገለበጠ እየገባ የምስኪኑን ህዝብ ጓዳ እየበዘበዘ ይገኛል። ለ3 አመታት ህፃናትን ከትምህርት ከትምህርት ገበታቸው ያራቀው የፋኖ አደረጃጀት አንድን ትውልድ ለማጥቃት ከዕውቀት ደጅ በማራቅ በድንቁርና ለማኖር ከበላዮቹ የተሰጠውን ትዕዛዥ ለማስፈፀም ቢሞክርም ህዝቡ ግን አሻፈረኝ በማለት በ2019 ዓ.፤ም የመማር ማስተማር ስራው እንደሚጀመር ድርጅቱ በመግለጫው ከሰሞኑ አስታውቋል።
የዳውድ ኢብሳ አጃቢ የነበረው እና በጌታቸው አሰፋ የተመለመለው ጃልማሮ እውነተኛ ማንነት
ዳውድ ኢብሳን እንዲሰልል በህወሓት ሰዎች ተመልምሎ ሲሰራ የቆየውና ትግረኛ ቋንቋን በደንብ መናገር የሚችለው ቅጥረኛው ጃልማሮ በአቦይ ስብሃት አቀባበል ተደርጎለት ወለጋ ጫካ የገባው የወያኔን ኢትዮዺያን የማፈራረስ እቅድ ለማሳካት ነበር። ለኦሮሞ እታገላለሁ ይበል እንጂ ኦሮሞን የማይወክል ለኦሮሞ መብት የማይታገል የህወሓት አሻንጉሊት እንደሆነ በዚህ ቪዲዮ ላይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






