ኢትዮጵያን ረፍት የመንሳቱ ዘመቻ በኃይማኖት፣ በጎሳ ግጭት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ተባለ፤ ሻዕቢያ ባልተለመደ መልኩ “ተወረርኩ” እያለ ነው፤ መንግስት ጸጥ ብሏል 

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | ኢትዮጵያን ረፍት ለመንሳት የተቀነባበሩ የተለያዩ እቅዶች እፈረሱ መሆኑ ተመለከተ። የአገር መከላከያ ኃይል በባድመ አቅጣጫ ጨመሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከናወኑ የጸጥታና የሰላም ማስከበር ሥራዎች ማጠናከሩ ተሰምቷል። ይህንን ተከትሎ በትግራይ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በአማራ ክልሎች በታጣቂ ቡድኖች ላይ እርምጃ መወሰዱንና በርካታ ታጣቂዎች እጃቸውን መስጠታቸው ሲሰማ፣ የኤርትራ መንግስት “ተውረርኩ” በማለት ድምጹን እያሰማ ነው። መንግስት “ጸጥ ብሏል”፤ ተሽከርካሪዎች ተያዙ።

የኤርትራ መንግሥት በባድመ አቅጣጫ ጥቃት እንደተፈጸመበት በመግለጽ ተከታታይ መግለጫዎችን ማውጣቱንና ሰልፎችን ማስተባበሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ይፋዊ ምላሽ ከመስጠት መቆጠቡ፣ በዲፕሎማሲና በወታደራዊ ስትራቴጂ ባለሙያዎች ዘንድ የተለያየ አስተያየት እየጸማበት ነው። አንዳንዶች «ሆን ተብሎ የተመረጠ ስትራቴጂካዊ ዝምታ (Strategic Silence)» ነው ሲሉ። ከፊሎች “ለአሉባልታ የሚዳርግ” ሲሉ መንግስት ዝምታውን መስበር እንዳለበት ይናገራሉ። 

የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የደኅንነት ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ መንግሥታት በድንበርና በሉዓላዊነት ጉዳዮች ላይ ለሚቀርቡ ክሶች ፈጣን የቃላት ምላሽ የማይሰጡባቸው በርካታ ስልቶችና ምክንያቶች አሉዋቸው።

ባለሙያዎቹ በዋናነት ከሚያነሷቸው ነጥቦች መካከል ምላሽ መስተት «የተቃራኒን አጀንዳ ያለመቀበል» ስልት አንዱ አካል ነው። አንድ አካል መግለጫ ሲያወጣ ወይም ሰልፍ ሲጠራ ዋናው ዓላማው ተቃራኒውን ወገን ወደ ቃላት ጦርነት በማስገባት ዓለም አቀፍ ትኩረት መሳብ ወይም የውስጥ ፖለቲካዊ ትኩሳቱን ማሞቅ ሊሆን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ። በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ በመስጠት ለክሱ ዕውቅና ከመስጠት ይልቅ፣ ዝምታን በመምረጥ ቅስቀሳው እንዲቀዘቅዝ የማድረግ አካሄድን መከተሉን ባለሙያዎቹ ይጠቁማሉ።

በሌላ በኩል የወታደራዊ ስትራቴጂ ባለሙያዎች ጉዳዩን «ከመረጃ የበላይነትና ከአፈጻጸም ሚስጥራዊነት» ጋር ያያይዙታል። በቀጠናው ያለውን ወታደራዊ አሰላለፍና የጸጥታ እንቅስቃሴ በይፋዊ መግለጫ መዘርዘር ለተጋጣሚ ወገን መረጃ እንደመስጠት ስለሚቆጠር፣ የመከላከያና የደኅንነት ተቋማት በመግለጫ ከመመላለስ ይልቅ በመሬት ላይ በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ ብቻ ማተኮርን እንደሚመርጡ ባለሙያዎቹ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ወገን አካሄድም ይህንን እንደሚመስል አስረድተዋል። 

የዲፕሎማሲ ምንጮች በበኩላቸው፣ በድንበር አካባቢ የሚነሱ አለመግባባቶች ዓለም አቀፍ ሕግና ዲፕሎማሲያዊ ውትወታ ስለሚያስከትሉ፣ መንግሥታት በሚዲያ ከመወዛገብ ይልቅ በዝግ በር (Back-channel) ወይም በቀጠናዊ አደራዳሪዎች በኩል መልዕክት መለዋወጥን የተሻለ አማራጭ አድርገው እንደሚወስዱም ይገልጻሉ። ከምንም በላይ በርካቶችን እያስደነቀ ያለው ግን በተዘጋ በር፣ አንደበቱን ዘግቶ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎች አካላት አሳቡን ሲሸጥ የነበረው ሻዕቢያ በዚህ ደረጃ ድምጹን ዕለት ዕለት ማሰማቱ ነው።

የማጥራትና የጸጥታ ማስከበር ስራዎች 

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከናወኑ የጸጥታና የሰላም ማስከበር ሥራዎች መጠናከራቸውን ተከትሎ በትግራይ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በአማራ ክልሎች በታጣቂ ቡድኖች ላይ እርምጃ መወሰዱንና በርካታ ታጣቂዎች እጃቸውን መስጠታቸው ተመለከተ። 

በማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞኖች በተደረገ ሰፊ አሰሳ በተምቤን አባራ አካባቢ ግጭት ለመቀስቀስ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 13 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የአካባቢው የጸጥታ መዋቅር አካላት አስታውቀዋል። እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዋላነህ በተባለ ሥፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙና በቢያራ አዲ አርቃይ፣ ባድመ መስመር የመከላከያ ሠራዊት እንቅስቃሴና የ24 ሰዓት ቅኝት መጠናከሩ እነዚህ ክፍሎች አመልክተዋል። 

የዜና ምንጮቹ እንዳሉት ሕወሓት በሃይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት በማቀነባበር ሃይማኖታዊ ግጭት ለመቀስቀስ እየሞከረ ቅሰቀሳ እያደረገ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከወዲሁ አሳስበዋል። ህወሃት በደቡብ ግንባር የጀመረው ጦርነት የተጠበቀውን ውጤት ባለማምጣቱ፣ የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ በጋራ መድረክ ስበሰባዎች ላይ አቋም መያዙን አዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪውን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም። 

በዚሁ ዕቅድ መሰረት የተቀነባበሩ ጥቃቶች በሰላማዊ ዜጎች ላይ መፈጸሙን፣ ጥቃቱን መንግስት እንደፈጸመው ተደርጎ በመናበብ ሰፊ ሽፋን እየተሰጠ ባለበት ወቅት ኦነግ ሸኔ ጥቃቱን እንደፈጸመ አምኖ ኃላፊነት መውሰዱ “የተለፋበትን ሁሉ አበላሸው፣ የህልውና ስጋት ከፈጠረው ህብረት መወገድ አለበት” በሚል በተከታታይ በተሰነዘረበት ትችት እና በሻዕቢያ ግምገማ ድርጅቱ መግለጫውን በማብራሪያ ለማስተካከል መሞከሩን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። 

ከትናንት ጀምሮ የወጡ ዜናዎች እንደሚያመለክቱት በምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስልሳ ስምንት የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው ለምዕራብ ዕዝ ጉባ ክፍለ ጦር እጃቸውን መስጠታቸው ተዘግቧል። በተመሳሳይ በመተማ አቅጣጫ በሱዳን ኃይሎችና በታጣቂ ቡድኖች ተቀናጅቶ ተከፍቶ ነበር የተባለ ጥቃት መክሸፉንና የድንበር ቁጥጥሩ መጠናከሩን ዘገባው ጠቁሟል። በሱዳን ኃይሎች የተሞከረው ጥቃት ከከሸፈ በኋላ የጄኔራል አልቡርሃን ጦር “ተደበደብኩ” በማለት መግለጫ አሰራጭቷል። የጄኔራሉ ኃይሎች “ጽምዶ” በሚባለው ህብረት ውስጥ በአባልነት ያሉበት በመሆኑ ይታወሳል። ጥምረቱም የተቋቋመው በሱዳን ነው።

በአማራ ክልል በቡሬ ዙሪያ ወረዳ በተወሰደ የተቀናጀ እርምጃ የሻለቃ አዛዥን ጨምሮ ወደ 15 የሚጠጉ የታጣቂ ቡድን አባላት መደምሰሳቸውና ሌሎች መማረካቸው ተነግሯል። በተጨማሪም በመርሳ ወልዲያ መስመር በሲቪል ተሽከርካሪ ላይ በሞባይል የሚፈነዳ ፈንጂ ለማጥመድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰዱ ታውቋል። በተወሰደው ርምጃ የደረሰውን ጉዳት ያላብራሩት ክፍሎች ሙከራው “ሽብር ነው” ብለዋል።

በሌላ የአሰሳ ዜና ህወሃት በየአካባቢው የደበቃቸው ተሽከርካሪዎች በጥቆማና በአሰሳ እየተገኙ ነው። ከሰሞኑም ህገ ወጡ ህወሃት በየጫካው ማለትም በትግራይ ዞን ማዕከላዊ ዞን ናዴር ወረዳ በወርኢ በርሃ አጎራባች ተረገይና ዕንዳ ስላሴ ቀበሌዎች ከህዝብ ዘርፎ ደብቋቸው የነበሩ 08 ተሽከርካሪዎች ተገኘተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related